ትንቢተ ሆሴዕ 12

AMHEVGአማርኛ14 ጥቅሶች2:12 አዳምጥ
አዳምጥ 2:12 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ኤፍሬም ነፋስን ይበላል፥ የምሥራቅንም ነፋስ ይከተላል፤ ሁልጊዜም ሐሰትንና ተንኰልን ያበዛል፤ ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፥ ወደ ግብፅም ዘይት ይወስዳሉ።

2እግዚአብሔርም ደግሞ ከይሁዳ ጋር ክርክር አለው፥ ያዕቆብንም እንደ መንገዱ ይቀጣል፤ እንደ ሥራውም ይመልስለታል።

3በማኅፀን ውስጥ ወንድሙን በተረከዙ ያዘው፥ በጕልማስነቱም ጊዜ ከአምላክ ጋር ታገለ፤

4ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ፤ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው፥ በዚያም ከእኛ ጋር ተነጋገረ።

5እርሱም የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው፤ የመታሰቢያው ስም እግዚአብሔር ነው።

6ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤ ምሕረትንና ፍርድን ጠብቅ፥ ዘወትርም በአምላክህ ታመን።

7ከከነዓን ወገን ነው፤ በእጁ የተንኰል ሚዛን አለ፥ ሽንገላንም ይወድዳል።

8ኤፍሬምም፦ “ባለ ጠጋ ሆኜአለሁ፥ ሀብትንም አግኝቻለሁ፥ በድካሜም ሁሉ ኃጢአት የሚሆን በደል አይገኝብኝም፡” አለ።

9እኔም ከግብፅ ጀምሬ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ፤ እንደ ዓመት በዓል ቀን እንደ ገና በድንኳን እንድትኖር አደርግሃለሁ።

10ለነቢያትም ተናግሬአለሁ፥ ራእይንም አብዝቻለሁ፤ በነቢያትም እጅ ምሳሌዎችን አውጥቻለሁ።

11ኃጢአት በገለዓድ አለ፤ ፈጽመው ከንቱ ናቸው፤ ወይፈኖች በጌልገላ ይሠዋሉ፥ መሠዊያዎቻቸውም በእርሻ ትልም ላይ የድንጋይ ክምር ይሆናሉ።

12ያዕቆብ ወደ ሶርያ አገር ሸሸ፥ እስራኤልም ስለ ሚስት አገለገለ፥ ስለ ሚስትም ጠባቂ ነበረ።

13እግዚአብሔርም በነቢይ እጅ እስራኤልን ከግብፅ አወጣ፥ በነቢይም እጅ ጠበቀው።

14ኤፍሬም አስመርሮ አስቈጣው፤ ስለዚህ ደሙ በላዩ ላይ ነው፤ ጌታውም ስድቡን በራሱ ላይ ይመልሳል።

ማብራሪያ

12:1-6 ኤፍሬም ከእግዚአብሔር ጋር ጠላትነት ሲኖረው ከሰው በሚመጣ እርዳታ በከንቱ ተስፋ ይጠበባል። አይሁድም ከአገራቸው ምርት በተሰጠ ስጦታ ግብፃውያንን ከጎናቸው ለማድረግ በከንቱ አሰቡ። ይሁዳም ደግሞ ቅሬታ ቀርቦበታል። እግዚአብሔር የራሱን ሕዝብ ኃጢአት ያያልና በእርሱም ምክንያት ይጠይቃቸዋል። ያዕቆብ ያደረገውን እና እግዚአብሔር ለእርሱ ያደረገውን እንዲያስታውሱ ይነገራቸዋል። የእርሱ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ላይ የነበረው እምነት ፍርሃቶቹን ሲያሸንፍ፣ ያን ጊዜ በብርቱነቱ ከእግዚአብሔር ጋር ታገለና ቻለ። እርሱ ይሖዋ ነው፤ የነበረው፣ ያለው፣ የሚመጣውም እርሱ ነው። ለአንዱ የእግዚአብሔር መገለጥ የነበረው፣ ለብዙዎች፣ ለሁሉም ትውልዶች የእርሱ መታሰቢያ ነው። እንግዲያስ ከእግዚአብሔር የራቁት ወደ እርሱ ይመለሱ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Ephraim feeds on the wind; he pursues the east wind all day and multiplies lies and violence. He makes a treaty with As… English BCV ኤፍሬም ንፋስ ይምገብ፤ ደድሕሪ ንፋስ ምብራቕ ከዓ ይስዕብ። ኵሉ መዓልቲ ሓሰትን ዓመፅን የብዝሕ። ምስ ኣሶር ቃል ኪዳን ይኣትዉ፤ ናብ ግብፂ ድማ ዘይቲ ይወስዱ። ትግርኛ GAZBIB “Efreem qilleensaa wajjin in oola, guyyaa guutuus qilleensa gara ba'a-biiftuu duukaa in fiiga; soba, humnaan nama irrat… Afaan Oromoo BCV GIZ ኤፍሬምሰ ጋኔን እኩይ ዘይዴግን ክብረ ወኵሎ ኩንቶ ወሐሰተ አብዝኅ፤ ወተካየደ ኪዳነ ምስለ ፋርስ ወየሐውር ግብፀ ከመ ይምህርዎ። giz GAZGAZ “Efreem qilleensaa wajjin in oola, guyyaa guutuus qilleensa gara ba'a-biiftuu duukaa in fiiga; soba, humnaan nama irrat… Afaan Oromoo BCV aksum ኤፍሬም ንፋስ ይምገብ፤ ደድሕሪ ንፋስ ምብራቕ ከዓ ይስዕብ። ኵሉ መዓልቲ ሓሰትን ዓመፅን የብዝሕ። ምስ ኣሶር ቃል ኪዳን ይኣትዉ፤ ናብ ግብፂ ድማ ዘይቲ ይወስዱ። ትግርኛ AMHNIV ኤፍሬም የነፋስ እረኛ ነው፤ ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል፤ ሐሰትንና ዐመፅን ያበዛል። ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋል፤ የወይራ ዘይትንም ወደ ግብፅ ይልካል። አማርኛ SWAHSUV Efraimu hujilisha upepo, na kuandamana na upepo wa mashariki; haachi kuongeza uongo na uharibifu; nao wafanya agano na … Kiswahili