ወደ ዕብራውያን 7

AMHNIVአማርኛ28 ጥቅሶች4:36 አዳምጥ
አዳምጥ 4:36 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ይህ መልከጼዴቅ የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበር፤ እርሱም አብርሃም ነገሥታትን ድል አድርጎ ሲመለስ አግኝቶት ባረከው፤

2አብርሃምም ከሁሉ ነገር ዓሥራት አውጥቶ ሰጠው። በመጀመሪያ ስሙ “የጽድቅ ንጉሥ” ማለት ነው፤ ኋላም ደግሞ “የሳሌም ንጉሥ” ማለትም “የሰላም ንጉሥ ማለት” ነው።

3አባትና እናት ወይም የትውልድ ሐረግ የለውም፤ ለዘመኑ መጀመሪያ፣ ለሕይወቱም ፍጻሜ የለውም፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ልጅ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።

4እስቲ እርሱ የቱን ያህል ታላቅ እንደሆነ ዐስቡ፤ ርእሰ አበው የሆነው አብርሃም እንኳ ካገኘው ምርኮ ዓሥራት አውጥቶ ሰጠው።

5ክህነት የተሰጣቸው የሌዊ ልጆች ምንም እንኳ ወንድሞቻቸው የአብርሃም ዘሮች ቢሆኑም፣ ከሕዝቡ ማለት ከገዛ ወንድሞቻቸው ዓሥራት እንዲቀበሉ ሕጉ ያዛል።

6ይህ ግን ትውልዱ ከሌዊ ወገን አይደለም፤ ይሁን እንጂ ከአብርሃም ዓሥራት ተቀበለ፤ የተስፋ ቃል የተቀበለውንም ባረከው።

7ትንሹ በትልቁ እንደሚባረክ ጥርጥር የለውም።

8በአንድ በኩል ዓሥራት የሚቀበሉት ሟች ሰዎች ናቸው፤ በሌላ በኩል ግን ሕያው ሆኖ እንደሚኖር የተመሰከረለት ይቀበላል።

9እንዲያውም ዓሥራት የሚቀበለው ሌዊ፣ ራሱ በአብርሃም በኩል ዓሥራት ከፍሎአል ማለት ይቻላል፤

10ምክንያቱም መልከጼዴቅ አብርሃምን ባገኘው ጊዜ፣ ሌዊ ገና በአባቱ በአብርሃም አብራክ ነበር።

11ፍጹምነት የተገኘውና ሕጉ ለሕዝቡ የተሰጠው በሌዊ ክህነት መሠረት ቢሆን ኖሮ፣ እንደ አሮን ሳይሆን እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ያለው ሌላ ካህን መምጣቱ ለምን አስፈለገ?

12የክህነት ለውጥ ካለ ሕጉም ሊለወጥ ግድ ነውና።

13ይህ ሁሉ የተነገረለት እርሱ ከሌላ ነገድ ነው፤ ከዚያም ነገድ በመሠዊያ ያገለገለ ማንም የለም።

14ጌታችን ከይሁዳ ነገድ እንደ መጣ ግልጽ ነውና፤ ሙሴ ስለ ካህናት ሲናገር ይህን ነገድ አስመልክቶ የተናገረው ምንም ነገር የለም።

15እንደ መልከጼዴቅ ያለ ሌላ ካህን ቢነሣ ግን እኛ የተናገርነው ይበልጥ ግልጽ ይሆናል፤

16እርሱ ካህን የሆነው በማይጠፋ የሕይወት ኀይል መሠረት እንጂ፣ እንደ ትውልዱ የሕግ ሥርዐት አይደለም፤

17እንዲህ ተብሎ ተመስክሮለታል፤ “እንደ መልከጼዴቅ ሹመት፣ አንተ ለዘላለም ካህን ነህ።”

18የቀድሞው ትእዛዝ ደካማና የማይጠቅም በመሆኑ ተሽሮአል፤

19ሕጉ ማንንም ፍጹም ሊያደርግ ስለማይችል ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት የተሻለ ተስፋ መጥቶአል።

20ይህ ያለ መሐላ አልሆነም፤ ሌሎች ካህናት የሆኑት ያለ መሐላ ነው፤

21እርሱ ግን ካህን የሆነው በመሐላ ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮለታል፤ “ጌታ ማለ፤ ዐሳቡንም አይለውጥም፤ ‘አንተ ለዘላለም ካህን ነህ።’ ”

22ከዚህ መሐላ የተነሣ፣ ኢየሱስ ለተሻለ ኪዳን ዋስ ሆኖአል።

23በአገልግሎታቸው እንዳይቀጥሉ ሞት ስለ ከለከላቸው፣ የቀድሞዎቹ ካህናት ቍጥራቸው ብዙ ነበር፤

24ኢየሱስ ግን ለዘላለም የሚኖር በመሆኑ፣ ክህነቱ የማይሻር ነው።

25ስለዚህ ስለ እነርሱ እየማለደ ሁል ጊዜ በሕይወት ስለሚኖር፣ በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።

26እንግዲህ ለእኛ የሚያስፈልገን፣ ቅዱስ፣ ነቀፋ የሌለበት፣ ንጹሕ፣ ከኀጢአተኞች የተለየና ከሰማያት በላይ የከበረ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ነው።

27እርሱም እንደ ሌሎቹ ሊቃነ ካህናት፣ መጀመሪያ ስለ ራሱ ኀጢአት ከዚያም ስለ ሕዝቡ ኀጢአት በየቀኑ መሥዋዕት ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ራሱን በሰጠ ጊዜ፣ ስለ ኀጢአታቸው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሥዋዕት አቅርቦአልና።

28ሕጉ ደካማ የሆኑትን ሰዎች ሊቃነ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፤ ከሕግ በኋላ የመጣው መሐላ ግን ለዘላለም ፍጹም የሆነውን ልጅ ሾሞአል።

ማብራሪያ

፯፡፩-፫ መልከ ጼዴቅ ሎጥን ከማዳን ሲመለስ አብርሃምን ተገናኘው። ስሙ፣ የጽድቅ ንጉሥ የሚለው፣ ለባሕርዩም ተስማሚ እንደሆነ ጥርጥር የለውም፤ ይህም እርሱን የመሲሑና የመንግሥቱ ምሳሌ አደረገው። የከተማው ስም ሰላምን ያመለክታል፤ እርሱም እንደ ሰላም ንጉሥ፣ የሰላም አለቃ የሆነውን ክርስቶስን፣ የእግዚአብሔርና የሰዎች ታላቅ አስታራቂ ምሳሌ ሆነ። ስለ ሕይወቱ መጀመሪያም ሆነ መጨረሻ ምንም አልተመዘገበም፤ በዚህም ምክንያት ሕልውናው ከዘላለም እስከ ዘላለም የሆነውን፣ እንዲሁም በክህነቱ ከርሱ በፊት የነበረው ማንም ያልነበረውንና ከርሱም በኋላ የሚመጣ ማንም የሌለውን የእግዚአብሔርን ልጅ ምሳሌ ሆነ። የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሁሉ ታላቁን የጽድቅና የሰላም ንጉሥ፣ የከበረውን ሊቀ ካህናችንንና አዳኛችንን ያከብራል፤ እሱን በመረመርነው ቁጥርም፣ የኢየሱስ ምስክርነት የትንቢት መንፈስ እንደሆነ ይበልጥ እርግጠኞች እንሆናለን።

፯፥፬-፲ በኋላ የሚገለጥና መልከጼዴቅ ምሳሌው የሆነለት ያ ሊቀ ካህን ከሌዋውያን ካህናት እጅግ የላቀ መሆን አለበት። የአብርሃምን ታላቅ ክብርና ደስታ ልብ በሉ፤ ይኸውም እርሱ ተስፋዎች የነበሩት መሆኑን። በእውነት ባለጠጋና ደስተኛ የሆነው ሰው፣ የአሁኑንም ሕይወት የሚመጣውንም ሕይወት የሚመለከቱ ተስፋዎች ያሉት ነው። ይህ ክብር ጌታ ኢየሱስን ለሚቀበሉ ሁሉ ነው። በመንፈሳዊ ትግላችን በቃሉና በኃይሉ በመታመን፣ ድላችንን ለጸጋው በመስጠት፣ እንዲሁም በመንገዳችን ሁሉ እርሱ እንዲያገኘንና እንዲባርከን በመፈለግ እንገስግስ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን የሆነ ይህ መልከ ጼዴቅ አብርሃም ነገሥታትን ገድሎ ሲመለስ ከእርሱ ጋር ተገናኝቶ ባረከው፤ አማርኛ ENGNIV This Melchizedek was king of Salem and priest of God Most High. He met Abraham returning from the defeat of the kings a… English BCV መልከ ፄዴቅ፥ ናይ ሳሌም ንጉስን፥ ናይ ልዑል እግዚኣብሄር ካህንን ነበረ። ኣብርሃም ነቶም ነገስታት ስዒሩ ኽምለስ እንተሎ፥ መልከ ፄዴቅ ተቐቢሉ ባረኾ። ትግርኛ GAZBIB Malkiisedeq kun mootii Saalem, luba Waaqayyoo isa hundumaa gara irraa jiruu ture; gaaf tokko Abrahaam mootota tokko ruk… Afaan Oromoo BCV GIZ ወመልከ ጼዴቅሰ ንጉሠ ሳሌም ካህኑ ለእግዚአብሔር ልዑል ውእቱ ዘመጽአ ወተራከቦ ለአብርሃም አመ ተመይጠ እምኀበ ተቃተሎሙ ለነገሥት ወባረኮሂ። giz GAZGAZ Malkiisedeq kun mootii Saalem, luba Waaqayyoo isa hundumaa gara irraa jiruu ture; gaaf tokko Abrahaam mootota tokko ruk… Afaan Oromoo BCV aksum መልከ ፄዴቅ፥ ናይ ሳሌም ንጉስን፥ ናይ ልዑል እግዚኣብሄር ካህንን ነበረ። ኣብርሃም ነቶም ነገስታት ስዒሩ ኽምለስ እንተሎ፥ መልከ ፄዴቅ ተቐቢሉ ባረኾ። ትግርኛ SWAHSUV Kwa maana Melkizedeki huyo, mfalme wa Salemu, kuhani wa Mungu aliye juu, aliyekutana na Ibrahimu alipokuwa akirudi kati… Kiswahili