ወደ ዕብራውያን 1

AMHNIVአማርኛ14 ጥቅሶች2:25 አዳምጥ
አዳምጥ 2:25 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በተለያየ ጊዜና በልዩ ልዩ መንገድ በነቢያት በኩል ለአባቶቻችን ተናግሮ፣

2በዚህ መጨረሻ ዘመን ግን ሁሉን ወራሽ ባደረገውና ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ለእኛ ተናገረን።

3እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅና የባሕርዩ ትክክለኛ ምሳሌ ሆኖ፣ በኀያል ቃሉ ሁሉን ደግፎ ይዞአል፤ የኀጢአት መንጻት ካስገኘ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።

4ስለዚህ የወረሰው ስም ከመላእክት ስም እንደሚበልጥ ሁሉ፣ እርሱም ከመላእክት እጅግ የላቀ ሆኖአል።

5እግዚአብሔር፣ “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፤” ወይስ ደግሞ፣ “እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል” ያለው ከመላእክት ከቶ ለማን ነው?

6ደግሞም እግዚአብሔር በኵሩን ወደ ዓለም ሲያስገባ፣ “የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ ይስገዱለት” ይላል።

7ስለ መላእክትም ሲናገር፣ “መላእክቱን ነፋሳት፣ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል ያደርጋል” ይላል።

8ስለ ልጁ ግን እንዲህ ይላል፤ “አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤ ጽድቅም የመንግሥትህ በትር ይሆናል፤

9ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃን ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከባልንጀሮችህ በላይ አስቀመጠህ፣ የደስታንም ዘይት ቀባህ።”

10ደግሞም እንዲህ ይላል፤ “ጌታ ሆይ፤ አንተ በመጀመሪያ የምድርን መሠረት አኖርህ፤ ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው።

11እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤

12እንደ መጐናጸፊያ ትጠቀልላቸዋለህ፤ እንደ ልብስም ይለወጣሉ። አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤ ዘመንህም ፍጻሜ የለውም።”

13እግዚአብሔር፣ “ጠላቶችህን የእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ፣ በቀኜ ተቀመጥ” ያለው ከመላእክት ከቶ ለማን ነው?

14መላእክት ሁሉ መዳንን የሚወርሱትን ለማገልገል የሚላኩ አገልጋይ መናፍስት አይደሉምን?

ማብራሪያ

1:1-3 እግዚአብሔር ለጥንት ሕዝቡ በተለያዩ ጊዜያት፣ በተከታታይ ትውልዶች ውስጥ፣ እናም እርሱ በተመለከተው መልኩ በተለያየ መንገድ ተናገረ፤ አንዳንዴ በቀጥታ በመናገር፣ አንዳንዴ በሕልሞች፣ አንዳንዴ በራእዮች፣ አንዳንዴም በመለኮታዊ ተጽዕኖ በነቢያት አእምሮ ላይ። የወንጌል መገለጥ ግን ከቀደሙት ይበልጣል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር በልጁ አማካይነት የገለጠው ነው። የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስን ኃይል፣ ጥበብና በጎነት ስንመለከት፣ የአብን ኃይል፣ ጥበብና በጎነት እንመለከታለን (ዮሐ 14:7)፤ የመለኮት ሙላትም በምሳሌ ወይም በምልክት ሳይሆን፣ በእርሱ ዘንድ በእውነት ያድራል። ሰው በወደቀ ጊዜ፣ ዓለም በእግዚአብሔር ቁጣና እርግማን ሥር እየፈራረሰ በነበረበት ወቅት፣ የእግዚአብሔር ልጅ የቤዛነትን ሥራ በመውሰድ፣ በሁሉን ቻይ ኃይሉና በጎነቱ አጸናው። ከክርስቶስ ስብዕናና ከአገልግሎቱ ክብር በመነሳት፣ ወደ ጸጋው ክብር እንሻገራለን። የእርሱ ስብዕናና ተፈጥሮ ክብር፣ ለመከራዎቹ እንዲህ ያለ ብቃት ሰጠው፤ ይህም በሰዎች ኃጢአት ምክንያት ወሰን የለሽ ጉዳትና ውርደት ለደረሰበት ለእግዚአብሔር ክብር ሙሉ በሙሉ ማስተሰረያ ሆነ። እግዚአብሔር በብዙ መንገዶች፣ እናም እንዲህ በሚጨምር ግልጽነት፣ ለወደቅን እኛ ኃጢአተኞች ስለ ድነት ተናግሮናልና ፈጽሞ በቂ ምስጋና ልናቀርብለት አንችልም። እርሱ ራሱ ከኃጢአታችን ያነጻን ዘንድ ያደረገው፣ ከኛ ከሁሉ የላቀ የአድናቆት፣ የምስጋናና የውዳሴ ኃይላችን በላይ የሆነ የፍቅር ተአምር ነው።

1:4-14 ብዙ አይሁድ መላእክት የሕግንና የመለኮታዊውን ፈቃድ ሌሎችንም ዜናዎች በአገልግሎታቸው በኩል ስላደረሱላቸው፣ በእነሱ ላይ አጉል እምነትና ጣዖታዊ አክብሮት ነበራቸው። በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል አስታራቂዎች አድርገው ይመለከቷቸው ነበር፤ አንዳንዶችም ሃይማኖታዊ አክብሮት ወይም አምልኮ እስከ መስጠት ደርሰው ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6