ወደ ዕብራውያን 12

AMHNIVአማርኛ29 ጥቅሶች5:10 አዳምጥ
አዳምጥ 5:10 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እንግዲህ እነዚህን የመሳሰሉ ብዙ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፣ ሸክም የሚሆንብንን ሁሉ፣ በቀላሉም ተብትቦ የሚይዘንን ኀጢአት አስወግደን በፊታችን ያለውን ሩጫ በጽናት እንሩጥ።

2የእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፣ የመስቀሉንም ውርደት ንቆ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል።

3እንግዲህ ዝላችሁ ተስፋ እንዳትቈርጡ፣ ከኀጢአተኞች የደረሰበትን እንዲህ ያለውን ተቃውሞ የታገሠውን እርሱን ዐስቡ።

4ከኀጢአት ጋር ስትታገሉ ገና ደማችሁን እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም።

5ልጆች እንደመሆናችሁ እንዲህ በማለት የተናገራችሁን ማበረታቻ ቃልም ረስታችኋል፦ “ልጄ ሆይ፤ የጌታን ቅጣት አታቃል፤ በሚገሥጽህም ጊዜ ተስፋ አትቍረጥ፤

6ምክንያቱም ጌታ የሚወደውን ይገሥጻል፤ እንደ ልጅ የሚቀበለውንም ይቀጣል።”

7እግዚአብሔር እንደ ልጆቹ ይዞአችኋልና የተግሣጽን ምክር ታገሡ፤ ለመሆኑ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው?

8ልጆች ሁሉ በሚቀጡበት ቅጣት ተካፋይ ካልሆናችሁ፣ ዲቃሎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም።

9ከዚህም በላይ፣ እኛ ሁላችን የሚቀጡን ምድራዊ አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር። ታዲያ ለመናፍስት አባት እንዴት አብልጠን በመገዛት በሕይወት አንኖርም?

10አባቶቻችን መልካም መስሎ እንደ ታያቸው ለጥቂት ጊዜ ይቀጡን ነበር፤ እግዚአብሔር ግን የቅድስናው ተካፋዮች እንድንሆን ለእኛ ጥቅም ሲል ይቀጣናል።

11ቅጣት ሁሉ በወቅቱ የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፤ በኋላ ግን ለለመዱት ሰዎች የጽድቅና የሰላም ፍሬ ያስገኝላቸዋል።

12ስለዚህ የዛለውን ክንዳችሁንና የደከመውን ጒልበታችሁን አበርቱ።

13ዐንካሳው እንዲፈወስ እንጂ የባሰውኑ እንዳያነክስ “ለእግራችሁ ቀና መንገድ አብጁ።”

14ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር የሚቻላችሁን ሁሉ አድርጉ፤ ለመቀደስም ፈልጉ፤ ያለ ቅድስና ማንም ጌታን ማየት አይችልም፤

15ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጐድልበት ደግሞም መራራ ሥር በቅሎ ችግር እንዳያስከትልና ብዙዎችን እንዳይበክል ተጠንቀቁ።

16ለአንድ ጊዜ መብል ሲል ብኵርናውን እንደ ሸጠው እንደ ዔሳው ማንም ሴሰኛ ወይም እግዚአብሔርን የማያከብር ሆኖ እንዳይገኝ ተጠንቀቁ።

17በኋላም ይህንኑ በረከት ሊወርስ በፈለገ ጊዜ፣ እንደ ተከለከለ ታውቃላችሁ፤ በረከቱን በእንባ ተግቶ ቢፈልግም መልሶ ሊያገኘው አልቻለም።

18ሊዳሰስ ወደሚችለውና በእሳት ወደሚቃጠለው ተራራ፣ ወደ ጨለማው፣ ወደ ጭጋጉና ወደ ዐውሎ ነፋሱ አልደረሳችሁም፤

19ወደ መለከት ድምፅ፣ ወይም ቃልን ወደ ሚያሰማ ድምፅ አልመጣችሁም፤ የሰሙትም ሌላ ቃል ተጨምሮ እንዳይናገራቸው ለመኑ።

20ምክንያቱም “እንስሳ እንኳ ተራራውን ቢነካ፣ በድንጋይ ተወግሮ ይሙት” የሚለውን ትእዛዝ መሸከም አልቻሉም።

21በዚያ ይታይ የነበረውም ሁኔታ እጅግ አስፈሪ ነበርና፣ ሙሴ “በፍርሀት ተንቀጠቀጥሁ” አለ።

22እናንተ ግን ወደ ጽዮን ተራራ፣ ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም፣ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ መጥታችኋል፤ በደስታ ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፣

23ስማቸው በሰማይ ወደ ተጻፈው ወደ በኵራት ማኅበር ቀርባችኋል፤ የሁሉ ዳኛ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር፣ ፍጹምነትን ወዳገኙት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፣

24የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ፣ እንዲሁም ከአቤል ደም የተሻለ ቃል ወደሚናገረው ወደ ተረጨው ደም ደርሳችኋል።

25የሚናገረውን እርሱን እምቢ እንዳትሉት ተጠንቀቁ። እነዚያ ከምድር ሆኖ ሲያስጠነ ቅቃቸው የነበረውን እምቢ ባሉ ጊዜ ካላመለጡ፣ እኛ ከሰማይ የመጣው ሲያስጠነቅ ቀን ከእርሱ ብንርቅ እንዴት ልናመልጥ እንችላለን?

26በዚያን ጊዜ ድምፁ ያናወጠው ምድርን ነበር፤ አሁን ግን፣ “ምድርን ብቻ ሳይሆን፣ ሰማያትንም አንድ ጊዜ ደግሜ አናውጣለሁ” ብሎ ቃል ገብቶአል።

27አንድ ጊዜ “ደግሜ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የማይናወጡት ጸንተው ይኖሩ ዘንድ፣ የሚናወጡት ይኸውም የተፈጠሩት የሚወገዱ መሆናቸውን ነው።

28ስለዚህ ከቶ የማይናወጥ መንግሥት ስለምንቀበል እግዚአብሔርን እናመስግን፤ ደግሞም ደስ በሚያሰኘው መንገድ በአክብሮትና በፍርሀት እናምልከው፤

29አምላካችን የሚያጠፋ እሳት ነውና።

ማብራሪያ

ዕብራውያን 12:1-11። በክርስቶስ የጸና የእምነት መታዘዝ ለዕብራውያን የተዘጋጀላቸው ሩጫ ነበር፤ በዚህም የክብርን አክሊል ወይ ማሸነፍ፣ አለዚያም የዘላለም መከራን ዕድላቸው ማድረግ ነበረባቸው፤ ይህ ሩጫ ለእኛም በእኛም ፊት ቀርቧል። በቀላሉ የምትይዘንን ኃጢአት ስንረዳ፣ ከልማድ፣ ከዕድሜ ወይም ከአካባቢያዊ ሁኔታዎች የተነሳ እኛ በቀላሉ የምንሳሳትን ወይም ይበልጥ ተጋላጭ የምንሆንባትን ኃጢአት እንደሆነች መገንዘብ ይገባናል። ይህ እጅግ አስፈላጊ የሆነ ምክር ነው፤ ምክንያቱም የአንድ ሰው ተወዳጅ ኃጢአት፣ ምንም ይሁን ምን፣ ያልተገራ ሆኖ እስከቀጠለ ድረስ፣ ለመሮጥ ያለውን እያንዳንዱን ተነሳሽነት ስለሚያስወግድ እና ለእያንዳንዱ ተስፋ መቁረጥ ኃይል ስለሚሰጥ፣ የክርስቲያንነትን ሩጫ እንዳይሮጥ ይከለክለዋል።

በልባቸው ደክመውና ድካም ሲሰማቸው፣ ቅዱስ ኢየሱስ ከዘላለም መከራ ሊያድናቸው እንደተሰቃየ ያስታውሱ። ኢየሱስን በትኩረት በመመልከት፣ ሐሳቦቻቸው ቅዱስ ስሜቶችን ያጠናክራሉ፣ ሥጋዊ ምኞቶቻቸውንም ያስገዛሉ። እንግዲያውስ ብዙ ጊዜ እርሱን እናስበው። ትናንሽ መከራዎቻችን ከስቃዩ ወይም ከሚገባን ቅጣት አንጻር ምንድን ናቸው? ከሌሎች ብዙዎች መከራ አንጻር ምን ያህል ናቸው? አማኞች በመከራና በስቃይ ውስጥ የመድከም እና የመዝለፍለፍ ዝንባሌ አላቸው፤ ይህ የጸጋ አለፍጽምና እና የኃጢአት ቅሪቶች ውጤት ነው። ክርስቲያኖች በፈተናዎቻቸው ውስጥ ልባቸው ሊደክም አይገባም። ጠላቶቻቸውና አሳዳጆቻቸው ስቃይን ለማምጣት መሳሪያ ቢሆኑም እንኳ፣ እነዚህ መለኮታዊ ቅጣቶች ናቸው፤ ሰማያዊ አባታቸው በሁሉም ነገር ውስጥ እጁ አለበት፣ እናም በሁሉም ነገር የጥበቡን ዓላማ ያሳካል።

መከራዎችን ቀላል አድርገው ሊመለከቱ ወይም በውስጣቸው ስሜት አልባ ሊሆኑ አይገባም፤ ምክንያቱም እነሱ የእግዚአብሔር እጅና በትር ናቸው፣ ለኃጢአትም የሚሰጣቸው ተግሣጾች ናቸው። በፈተናዎች ውስጥ ተስፋ ቆርጠው ሊሰምጡ፣ ሊያጕረመርሙ ወይም ሊበሳጩ አይገባም፤ ነገር ግን በእምነትና በትዕግሥት ሊጸኑ ይገባል። እግዚአብሔር ሌሎችን በኃጢአታቸው ብቻቸውን ሊተዋቸው ይችላል፣ ነገር ግን በገዛ ልጆቹ ውስጥ ያለውን ኃጢአት ያርማል። በዚህም እንደ አባት ይሠራል። ምድራዊ ወላጆቻችን አንዳንድ ጊዜ ሥነ ምግባራችንን ለማረም ከማሰብ ይልቅ ፍላጎታቸውን ለማርካት ሊቀጡን ይችላሉ። ነገር ግን የነፍሳችን አባት ልጆቹን በገዛ ፈቃዱ ፈጽሞ አያሳዝንም ወይም አያሠቃይም። ሁልጊዜም ለጥቅማችን ነው። እዚህ ያለን ሕይወታችን በሙሉ የልጅነት ሁኔታ ሲሆን፣ በመንፈሳዊ ነገሮች ረገድም ፍጽምና የጎደለው ነው፤ ስለዚህ የዚህን ዓይነት ሁኔታ ተግሣጽ መቀበል አለብን። ወደ ፍጹም ሁኔታ ስንመጣ፣ እግዚአብሔር አሁን ለሚቀጣን ነገር ሁሉ ሙሉ በሙሉ እንስማማለን። የእግዚአብሔር እርማት የፍርድ ውግዘት አይደለም፤ ቅጣቱ በትዕግሥት ሊታገሥ ይችላል፣ ቅድስናንም በእጅጉ ያበረታታል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በ… አማርኛ ENGNIV Therefore, since we are surrounded by such a great cloud of witnesses, let us throw off everything that hinders and the… English BCV ምእንቲ እዙይ ንሕናውን ክንድዙይ ዝኣኽሉ መሰኻኽር፥ ከም ደመና ኸቢቦምና ስለ ዘለዉ፥ ንዅሉ እቲ ዝኸብደናን ዝጠብቀናን ሓጢኣት ኣርሒቕና፥ በቲ ኣብ ቅድሜና ተዳልዩልና ዘሎ መቀዳደሚ፥ ብትዕግ… ትግርኛ GAZBIB Egaa nuyi dhuga-baatota akka duumessaa lafa uffisan naannoo keenyaa qabna; kanaafis kottaa wanta ba'aa nutti ta'u hundu… Afaan Oromoo BCV GIZ ወበእንተ ዝንቱ ንሕነኒ እለ ብነ እሙንቱ ሰማዕት ኵሎሙ ዘየዐውዱነ ከመ ደመና ንግድፍ እምላዕሌነ ኵሎ ክበደ ወሁከተ ኀጢአት ወንሩጽ በትዕግሥት ኀበ ዘጽኑሕ ለነ ተስፋነ ዘሃይማኖት። giz GAZGAZ Egaa nuyi dhuga-baatota akka duumessaa lafa uffisan naannoo keenyaa qabna; kanaafis kottaa wanta ba'aa nutti ta'u hundu… Afaan Oromoo BCV aksum ምእንቲ እዙይ ንሕናውን ክንድዙይ ዝኣኽሉ መሰኻኽር፥ ከም ደመና ኸቢቦምና ስለ ዘለዉ፥ ንዅሉ እቲ ዝኸብደናን ዝጠብቀናን ሓጢኣት ኣርሒቕና፥ በቲ ኣብ ቅድሜና ተዳልዩልና ዘሎ መቀዳደሚ፥ ብትዕግ… ትግርኛ SWAHSUV Basi na sisi pia, kwa kuwa tunazungukwa na wingu kubwa la mashahidi namna hii, na tuweke kando kila mzigo mzito, na dha… Kiswahili