ትንቢተ ሐጌ 1

AMHNIVአማርኛ15 ጥቅሶች3:07 አዳምጥ
አዳምጥ 3:07 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን፣ የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩል ወደ ይሁዳ ገዥ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤልና ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲል መጣ፤

2እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “ይህ ሕዝብ፣ ‘የእግዚአብሔር ቤት የሚሠራበት ጊዜ ገና ነው’ ይላል።”

3የእግዚአብሔርም ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩል እንዲህ ሲል መጣ፤

4“ይህ ቤት ፈርሶ ሳለ፣ እናንተ ራሳችሁ በተዋቡ ቤቶቻችሁ ውስጥ ለመኖር ጊዜው ነውን?”

5ስለዚህ እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “እስቲ መንገዳችሁን ልብ በሉ፤

6ብዙ ዘራችሁ፤ ነገር ግን ያጨዳችሁት ጥቂት ነው፤ በላችሁ ግን አልጠገባችሁም፤ ጠጣችሁ ግን አልረካችሁም፤ ለበሳችሁ ግን አልሞቃችሁም፤ ደመወዝን ተቀበላችሁ፤ ግን በቀዳዳ ኰረጆ የማስቀመጥ ያህል ነው።”

7እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “እስቲ መንገዳችሁን ልብ በሉ፤

8ወደ ተራራ ውጡ፤ ዕንጨት አምጡ፤ ቤቱን ሥሩ፤ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል፤ እከበርበታለሁም” ይላል እግዚአብሔር።

9ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ብዙ ተስፋ አደረጋችሁ፤ ያገኛችሁት ግን ጥቂት ነው፤ ወደ ቤት ያስገባችሁትንም እኔ እፍ አልሁበት፤ ይህ የሆነው ለምን ይመስላችኋል?” የእኔ ቤት ፈርሶ እያለ ሁላችሁም የራሳችሁን ቤት ለመሥራት ስለሮጣችሁ ነው፤

10ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ሰማያት ጠል ከለከሉ፤ ምድርም ፍሬዋን ነሣች።

11እኔም በዕርሻዎችና በተራሮች፣ በእህሉና በአዲሱ ወይን ጠጅ፣ በዘይቱና ምድር በምታፈራው ሁሉ፣ በሰውና በእንስሳ፣ በእጆቻችሁም ሥራ ላይ ድርቅ አመጣሁ።”

12ከዚህ በኋላ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል፣ ሊቀ ካህናቱ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፣ ከምርኮ የተረፉትም ሕዝብ የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ድምፅ፣ የነቢዩንም የሐጌን መልእክት ሰሙ፤ አምላካቸው እግዚአብሔር ልኮታልና። ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ።

13ቀጥሎም የእግዚአብሔር መልእክተኛ ሐጌ፣ ይህን የእግዚአብሔርን መልእክት ለሕዝቡ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ” ይላል እግዚአብሔር።

14ስለዚህ እግዚአብሔር የይሁዳን ገዥ፣ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስ፣ የሊቀ ካህናቱን የኢዮሴዴቅን ልጅ፣ የኢያሱን መንፈስና፣ ከምርኮ የተረፈውን ሕዝብ ሁሉ መንፈስ አነሣሣ፤ እነርሱም መጥተው የአምላካቸውን የእግዚአብሔር ጸባኦት ቤት መሥራት ጀመሩ።

15ይህ የሆነውም ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ በሃያ አራተኛው ቀን ነበር።

ማብራሪያ

1:1-11 ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ በኋላ የአይሁድን ኃጢአት ልብ በሉ። ለእግዚአብሔር የሚያገለግሉ ሰዎች በዐውሎ ነፋስ (ወይም በችግር) ከሥራቸው ሊገፉ ቢችሉም፣ ወደዚያው መመለስ አለባቸው። ቤተ መቅደስ አንሠራም አላሉም፣ ይልቁንም፣ 'ገና አይደለም' አሉ። እንዲሁ ሰዎች ንስሐ አንገባም፣ አንታደስም፣ አምላካዊ ሕይወት አንኖርም አይሉም፤ ይልቁንም፣ 'ገና አይደለም' ይላሉ። እናም በዚህ ምክንያት ወደ ዓለም የተላክንበት ታላቁ ሥራ አልተሠራም። በግዴታችን ውስጥ የሚገጥሙንን ተስፋ አስቆራጭ ነገሮች ከግዴታችን ነጻ የሚያደርጉን ያህል አድርገን በተሳሳተ መንገድ የማሰብ ዝንባሌ በእኛ ዘንድ አለ፤ ሲሆኑ ግን የድፍረታችንንና የእምነታችንን መፈተኛ ብቻ ናቸው። የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ቸል አሉ፤ ይህም ለዓለማዊ ጉዳዮች የበለጠ ጊዜና ገንዘብ እንዲኖራቸው ነበር። ቅጣቱ ከኃጢአቱ ጋር እንዲመጣጠን፣ እነርሱ ቤተ መቅደሱን ባለመሥራት ለመከላከል ያሰቡትን ድህነት፣ እግዚአብሔር ቤተ መቅደሱን ባለመሥራታቸው ምክንያት በእነርሱ ላይ አመጣ። ብዙ መልካም ሥራዎች ታስበው ነበር፣ ግን ሰዎች ተገቢው ጊዜ ገና አልደረሰም ብለው ስላሰቡ አልተሠሩም። በዚህም ምክንያት አማኞች የአገልግሎት ዕድሎችን ያጣሉ፣ ኃጢአተኞችም የነፍሳቸውን ጉዳይ እስከ ዘግይቶ ጊዜ ድረስ ያዘገያሉ። እዚህ እንዳሉት አይሁድ፣ የሚጠፋውን ምግብ ብቻ የምንሠራ ከሆነ፣ የጥረታችንን ፍሬ የማጣት አደጋ ላይ ነን፤ ነገር ግን ለዘላለም ሕይወት ለሚቆየው ምግብ የምንሠራ ከሆነ፣ በጌታ ከንቱ እንደማይሆንብን እርግጠኞች ነን።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በንጉሡ በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ ወደ ይሁዳ አለቃ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤል፥ ወደ ታላቁም ካህን ወ… አማርኛ ENGNIV In the second year of King Darius, on the first day of the sixth month, the word of the Lord came through the prophet H… English BCV ዳርዮስ፥ ኣብ ሜዶን ምስ ነገሰ ኣብ ካልአይቲ ዓመቱ፥ ብቐዳመይቲ መዓልቲ ናይታ ሻድሸይቲ ወርሒ፥ ከምዙይ ዝብል ቃል እግዚኣብሄር፥ ብኢድ ነቢይ ሓጌ ናብ ዘሩባቤል ወዲ ሰላትያል ገዛኢ ይሁዳን… ትግርኛ GAZBIB Daariyos biyya Faares irratti mo'ee waggaa lammaffaatti, waggicha keessaa ji'a ja'affaatti, ji'icha keessaa guyyaa tokk… Afaan Oromoo BCV GIZ በካልእት ዓመተ መንግሥቱ ለዳርዮስ ንጉሥ በሳድስ ወርኅ አመ ሠርቅ ኮነ ቃለ እግዚአብሔር በእደ ሐጌ ነቢይ ወይቤሎ፦ በሎ ለዝሩባቤል ወልደ ሰላትየል ዘሕዝበ ይሁዳ ወለዮሴዕ ወልደ ዮሴዴቅ ካህ… giz GAZGAZ Daariyos biyya Faares irratti mo'ee waggaa lammaffaatti, waggicha keessaa ji'a ja'affaatti, ji'icha keessaa guyyaa tokk… Afaan Oromoo BCV aksum ዳርዮስ፥ ኣብ ሜዶን ምስ ነገሰ ኣብ ካልአይቲ ዓመቱ፥ ብቐዳመይቲ መዓልቲ ናይታ ሻድሸይቲ ወርሒ፥ ከምዙይ ዝብል ቃል እግዚኣብሄር፥ ብኢድ ነቢይ ሓጌ ናብ ዘሩባቤል ወዲ ሰላትያል ገዛኢ ይሁዳን… ትግርኛ SWAHSUV Katika mwaka wa pili wa Dario mfalme, mwezi wa sita, siku ya kwanza ya mwezi, neno la Bwana lilimjia Zerubabeli, mwana … Kiswahili