ትንቢተ ሐጌ 1

AMHEVGአማርኛ14 ጥቅሶች2:51 አዳምጥ
አዳምጥ 2:51 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በንጉሡ በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ ወደ ይሁዳ አለቃ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤል፥ ወደ ታላቁም ካህን ወደ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲል መጣ፦

2“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦ ‘ይህ ሕዝብ፦ ዘመኑ አልደረሰም፥ የእግዚአብሔር ቤት የሚሠራበት ዘመን አልደረሰም፡’ ይላል፡” ብሎ ተናገረ።

3የእግዚአብሔርም ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ እንዲህ ሲል መጣ፦

4“በውኑ ይህ ቤት ፈርሶ ሳለ እናንተ ራሳችሁ በተሸለሙ ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነውን?”

5አሁንም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ።

6ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ፤ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም፤ ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልረካችሁም፤ ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም፤ ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ያደርገው ዘንድ ደመወዙን ተቀበለ።”

7የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ።

8ወደ ተራራው ውጡ፥ እንጨትንም አምጡ፥ ቤቱንም ሥሩ፤ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል፥ እኔም እመሰገናለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።

9“እናንተ ብዙ ነገርን ተስፋ አደረጋችሁ፥ እነሆም፥ ጥቂት ሆነ፤ ወደ ቤትም ባገባችሁት ጊዜ እፍ አልሁበት። ይህ ስለ ምንድር ነው?” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “እናንተ ሁሉ ወደ እየቤታችሁ እየሮጣችሁ የእኔ ቤት ፈርሶ ስለ ተቀመጠ ነው።

10ስለዚህ ሰማያት በላያችሁ ጠልን ከልክለዋል፥ ምድሪቱም ፍሬዋን ከልክላለች።

11እኔም በምድርና በተራሮች፥ በእህልና በወይንም፥ በዘይትና ምድርም በምታበቅለው ላይ፥ በሰዎችና በእንስሶችም ላይ፥ እጅም በሚደክምበት ሁሉ ላይ ድርቅን ጠርቻለሁ።”

12የሰላትያልም ልጅ ዘሩባቤል፥ ታላቁም ካህን የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፥ የቀሩትም ሕዝብ ሁሉ የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ድምፅ የነቢዩንም የሐጌን ቃል፥ አምላካቸው እግዚአብሔር እንደ ላከው ሁሉ ሰሙ፤ ሕዝቡም በእግዚአብሔር ፊት ፈሩ።

13የእግዚአብሔርም መልእክተኛ ሐጌ በእግዚአብሔር መልእክት ሕዝቡን፦ “እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር፡” ብሎ ተናገረ።

14እግዚአብሔርም የይሁዳን አለቃ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስ፥ የታላቁንም ካህን የኢዮሴዴቅን ልጅ የኢያሱን መንፈስ፥ የቀሩትንም ሕዝብ ሁሉ መንፈስ አስነሣ፤ በንጉሡም በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በሀያ አራተኛው ቀን መጡ፥ የአምላካቸውንም የሠራዊትን ጌታ የእግዚአብሔርን ቤት ሠሩ።

ማብራሪያ

1:1-11 ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ በኋላ የአይሁድን ኃጢአት ልብ በሉ። ለእግዚአብሔር የሚያገለግሉ ሰዎች በዐውሎ ነፋስ (ወይም በችግር) ከሥራቸው ሊገፉ ቢችሉም፣ ወደዚያው መመለስ አለባቸው። ቤተ መቅደስ አንሠራም አላሉም፣ ይልቁንም፣ 'ገና አይደለም' አሉ። እንዲሁ ሰዎች ንስሐ አንገባም፣ አንታደስም፣ አምላካዊ ሕይወት አንኖርም አይሉም፤ ይልቁንም፣ 'ገና አይደለም' ይላሉ። እናም በዚህ ምክንያት ወደ ዓለም የተላክንበት ታላቁ ሥራ አልተሠራም። በግዴታችን ውስጥ የሚገጥሙንን ተስፋ አስቆራጭ ነገሮች ከግዴታችን ነጻ የሚያደርጉን ያህል አድርገን በተሳሳተ መንገድ የማሰብ ዝንባሌ በእኛ ዘንድ አለ፤ ሲሆኑ ግን የድፍረታችንንና የእምነታችንን መፈተኛ ብቻ ናቸው። የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ቸል አሉ፤ ይህም ለዓለማዊ ጉዳዮች የበለጠ ጊዜና ገንዘብ እንዲኖራቸው ነበር። ቅጣቱ ከኃጢአቱ ጋር እንዲመጣጠን፣ እነርሱ ቤተ መቅደሱን ባለመሥራት ለመከላከል ያሰቡትን ድህነት፣ እግዚአብሔር ቤተ መቅደሱን ባለመሥራታቸው ምክንያት በእነርሱ ላይ አመጣ። ብዙ መልካም ሥራዎች ታስበው ነበር፣ ግን ሰዎች ተገቢው ጊዜ ገና አልደረሰም ብለው ስላሰቡ አልተሠሩም። በዚህም ምክንያት አማኞች የአገልግሎት ዕድሎችን ያጣሉ፣ ኃጢአተኞችም የነፍሳቸውን ጉዳይ እስከ ዘግይቶ ጊዜ ድረስ ያዘገያሉ። እዚህ እንዳሉት አይሁድ፣ የሚጠፋውን ምግብ ብቻ የምንሠራ ከሆነ፣ የጥረታችንን ፍሬ የማጣት አደጋ ላይ ነን፤ ነገር ግን ለዘላለም ሕይወት ለሚቆየው ምግብ የምንሠራ ከሆነ፣ በጌታ ከንቱ እንደማይሆንብን እርግጠኞች ነን።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV In the second year of King Darius, on the first day of the sixth month, the word of the Lord came through the prophet H… English BCV ዳርዮስ፥ ኣብ ሜዶን ምስ ነገሰ ኣብ ካልአይቲ ዓመቱ፥ ብቐዳመይቲ መዓልቲ ናይታ ሻድሸይቲ ወርሒ፥ ከምዙይ ዝብል ቃል እግዚኣብሄር፥ ብኢድ ነቢይ ሓጌ ናብ ዘሩባቤል ወዲ ሰላትያል ገዛኢ ይሁዳን… ትግርኛ GAZBIB Daariyos biyya Faares irratti mo'ee waggaa lammaffaatti, waggicha keessaa ji'a ja'affaatti, ji'icha keessaa guyyaa tokk… Afaan Oromoo BCV GIZ በካልእት ዓመተ መንግሥቱ ለዳርዮስ ንጉሥ በሳድስ ወርኅ አመ ሠርቅ ኮነ ቃለ እግዚአብሔር በእደ ሐጌ ነቢይ ወይቤሎ፦ በሎ ለዝሩባቤል ወልደ ሰላትየል ዘሕዝበ ይሁዳ ወለዮሴዕ ወልደ ዮሴዴቅ ካህ… giz GAZGAZ Daariyos biyya Faares irratti mo'ee waggaa lammaffaatti, waggicha keessaa ji'a ja'affaatti, ji'icha keessaa guyyaa tokk… Afaan Oromoo BCV aksum ዳርዮስ፥ ኣብ ሜዶን ምስ ነገሰ ኣብ ካልአይቲ ዓመቱ፥ ብቐዳመይቲ መዓልቲ ናይታ ሻድሸይቲ ወርሒ፥ ከምዙይ ዝብል ቃል እግዚኣብሄር፥ ብኢድ ነቢይ ሓጌ ናብ ዘሩባቤል ወዲ ሰላትያል ገዛኢ ይሁዳን… ትግርኛ AMHNIV ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን፣ የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩል ወደ ይሁዳ ገዥ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤልና ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ኢዮሴዴ… አማርኛ SWAHSUV Katika mwaka wa pili wa Dario mfalme, mwezi wa sita, siku ya kwanza ya mwezi, neno la Bwana lilimjia Zerubabeli, mwana … Kiswahili