ትንቢተ ሕዝቅኤል 9

AMHEVGአማርኛ11 ጥቅሶች2:26 አዳምጥ
አዳምጥ 2:26 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እርሱም፦ እያንዳንዳቸው የሚያጠፋ መሣሪያን በእጃቸው ይዘው ከተማይቱን የሚቀሥፉ ይቅረቡ፡ ብሎ በታላቅ ድምፅ በጆሮዬ ጮኸ።

2እነሆም፥ እያንዳንዳቸው አጥፊውን መሣሪያ በእጃቸው ይዘው ስድስት ሰዎች ወደ ሰሜን ከሚመለከተው ከላይኛው በር መንገድ መጡ፤ በመካከላቸውም የበፍታ ልብስ የለበሰ የጸሐፊም ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘ አንድ ሰው ነበረ። እነርሱም ገብተው በናሱ መሠዊያ አጠገብ ቆሙ።

3የእስራኤልም አምላክ ክብር በበላዩ ከነበረበት ኪሩብ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መድረክ ሄዶ ነበር፤ በፍታም የለበሰውን የጸሐፊውንም ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘውን ሰው ጠራ።

4እግዚአብሔርም፦ በከተማይቱ በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ርኵሰት ሁሉ በሚያለቅሱና በሚተክዙ ሰዎች ግምባር ላይ ምልክት ጻፍ፡ አለው።

5እኔም እየሰማሁ ለሌሎቹ፦ እርሱን ተከትላችሁ በከተማይቱ መካከል እለፉ፥ ግደሉም፤ ዓይናችሁ አይራራ አትዘኑም፤

6ሽማግሌውንና ጐበዙን ቈንጆይቱንም ሕፃናቶቹንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፤ በመቅደሴም ጀምሩ፡ አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ።

7እርሱም፦ ቤቱን አርክሱ፥ በተገደሉትም ሰዎች አደባባዮችን ሙሉ፤ ውጡ፡ አላቸው። እነርሱም ወጥተው በከተማይቱ ገደሉ።

8ሲገድሉም እኔ ብቻዬን ቀርቼ ሳለሁ በግምባሬ ተደፍቼ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! መዓትህን በኢየሩሳሌም ላይ ስታፈስስ የእስራኤልን ቅሬታ ሁሉ ታጠፋለህን? ብዬ ጮኽሁ።

9እርሱም፦ የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ኃጢአት እጅግ በዝቶአል ምድሪቱም ደም፥ ከተማይቱም ዓመፅን ተሞልታለች፤ እነርሱም፦ እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአታል፥ እግዚአብሔርም አያይም፡ ብለዋል።

10እኔም ደግሞ በዓይኔ አልራራም አላዝንምም፥ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ፡ አለኝ።

11እነሆም፥ በፍታ የለበሰው የቀለም ቀንድም በወገቡ የያዘው ሰው፦ ያዘዝኸኝን አድርጌአለሁ፡ ብሎ በቃሉ መለሰ።

ማብራሪያ

9:1-4 አማላጅ፥ ታላቅ ሊቀ ካህናት መኖሩ ለምእመናን ታላቅ መጽናኛ ነው፤ እርሱም በሰማይ ድርሻ ያለው ሲሆን፥ ምድር ላይ ያሉ ቅዱሳን ደግሞ በእርሱ ድርሻ አላቸው፤ ይህም በአጥፊዎችና በጥፋቶች መካከል ሳሉ እንኳን ነው። ከታቦቱ በላይ የነበረው የመለኮታዊ ክብር መገለጥ ወደ ደጃፉ መዛወሩ ጌታ የምሕረቱን ዙፋን ሊተውና በሕዝቡ ላይ ፍርድ ሊፈርድ እንደሆነ ያመለክታል። የሚድነው የዚህ ቅሬታ ልዩ መለያ በኢየሩሳሌም ባሉት ርኵሰቶች የተነሳ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር የሚያቃስቱና የሚያለቅሱ መሆናቸው…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Then I heard him call out in a loud voice, “Bring the guards of the city here, each with a weapon in his hand.” English BCV ኣብ ኣእዛነይ ከዓ፥ እቶም ነታ ኸተማ ዝቐፅዑ፥ ነፍሲ ወከፎም ነቲ ዘጥፍአሉ ኣፅዋር ኣብ ኢዱ ሒዙ ይቕረብ፥ እናበለ ዓው ኢሉ ድምፂ ኣስምዐ። ትግርኛ GAZBIB Kana booddee inni sagalee guddaadhaan,“Warri mandarattii adaban hundinuu adduma addaan mi'a waraanaa harkatti qabatanii… Afaan Oromoo BCV GIZ ወከልሐ በዓቢይ ቃል ውስተ እዝንየ፡ ወይቤ፦ አልፀቀ መቅሠፍትየ በዛ ሀገር ወለኵሎሙ ጕድብ ውስተ እደዊሆሙ በዘይሤርዎሙ። giz GAZGAZ Kana booddee inni sagalee guddaadhaan,“Warri mandarattii adaban hundinuu adduma addaan mi'a waraanaa harkatti qabatanii… Afaan Oromoo BCV aksum ኣብ ኣእዛነይ ከዓ፥ እቶም ነታ ኸተማ ዝቐፅዑ፥ ነፍሲ ወከፎም ነቲ ዘጥፍአሉ ኣፅዋር ኣብ ኢዱ ሒዙ ይቕረብ፥ እናበለ ዓው ኢሉ ድምፂ ኣስምዐ። ትግርኛ AMHNIV ከዚያም እኔ እየሰማሁ ከፍ ባለ ድምፅ፣ “እያንዳንዳቸው በእጃቸው የጦር መሣሪያ የያዙ፣ ከተማዪቱን የሚቀጡ ወደዚህ ይምጡ” ብሎ ከፍ ባለ ድምፅ ጮኸ። አማርኛ SWAHSUV Kisha akalia kwa sauti kuu masikioni mwangu, akisema, Waamuru wale wanaousimamia mji wakaribie, kila mmoja na awe na ki… Kiswahili