ትንቢተ ሕዝቅኤል 5

AMHEVGአማርኛ17 ጥቅሶች3:27 አዳምጥ
አዳምጥ 3:27 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የተሳለን ጐራዴ ውሰድ፥ እንደ ጢም መላጫ ወደ አንተ ትወስደዋለህ፥ ራስህንና ጢምህንም ትላጭበታለህ፤ ሚዛንንም ውሰድ ጠጕሩንም ትከፋፍላለህ።

2የመከበብም ወራት በተፈጸመ ጊዜ በከተማይቱ መካከል ሢሶውን በእሳት ታቃጥላለህ፤ ሢሶውንም ወስደህ ዙሪያውን በጐራዴ ትመታለህ፥ ሢሶውንም ወደ ነፋስ ትበትናለህ እኔም በኋላቸው ጐራዴ እመዝዛለሁ።

3ከዚያም በጥቂቱ ውሰድ በመጐናጸፊያህም ጫፍ ቋጥራቸው።

4ከእነርሱም ደግሞ ወስደህ በእሳት ውስጥ ትጥላለህ በእሳትም ታቃጥላቸዋለህ፤ ከዚያም በእስራኤል ቤት ሁሉ ላይ እሳት ትወጣለች።

5ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህች ኢየሩሳሌም ናት፤ በአሕዛብም መካከል አድርጌአታለሁ፥ አገሮችም በዙሪያዋ አሉ።

6እርስዋም ከአሕዛብ ይልቅ ፍርዴን በኃጢአት ለወጠች በዙሪያዋም ካሉ አገሮች ሁሉ ይልቅ ትእዛዜን ተላለፈች፤ ፍርዴን ጥለዋልና፥ በትእዛዜም አልሄዱምና።

7ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዙሪያችሁ ላሉት አሕዛብ ሰበብ ሆናችኋልና፥ በትእዛዜም አልሄዳችሁምና፥ ፍርዴንም አልጠበቃችሁምና፥ በዙሪያችሁም እንዳሉ እንደ አሕዛብ ፍርድ እንኳ አላደረጋችሁምና

8ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እኔ ራሴ በአንቺ ላይ ነኝ፥ አሕዛብም እያዩ ፍርድን በመካከልሽ አደርጋለሁ።

9ስለ ርኵሰትሽም ሁሉ ያልሠራሁትን እርሱንም የሚመስል ደግሞ የማልሠራውን ነገር እሠራብሻለሁ።

10ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፤ ፍርድንም አደርግብሻለሁ ከአንቺም የቀረውን ሁሉ ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናለሁ።

11ስለዚህ፥ እኔ ሕያው ነኝና በእድፍሽና በርኵሰትሽ መቅደሴን ስላረከስሽ፥ ስለዚህ በእውነት እኔ አሳንስሻለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ዓይኔም አይራራም እኔም አላዝንም።

12ከአንቺም ሢሶው በቸነፈር ይሞታል፥ በመካከልሽም በራብ ያልቃል፤ ሢሶውም በዙሪያሽ በሰይፍ ይወድቃል፤ ሢሶውንም ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናለሁ በኋላቸውም ሰይፍ እመዝዛለሁ።

13ቍጣዬም ይፈጸማል መዓቴንም እጨርሳለሁ እጽናናማለሁ፥ መዓቴንም በፈጸምሁባቸው ጊዜ እኔ እግዚአብሔር በቅንዓቴ እንደ ተናገርሁ ያውቃሉ።

14በዙሪያሽም ባሉ በአሕዛብ መካከል በሚያልፉም ሁሉ ፊት ባድማና መሰደቢያ አደርግሻለሁ።

15በቍጣና በመዓት፥ በመዓትም ዘለፋ ፍርድን ባደረግሁብሽ ጊዜ በዙሪያሽ ላሉ አሕዛብ መሰደቢያና መተረቻ፥ ተግሣጽና መደነቂያ ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።

16ለማጥፋትም የሆነውን፥ አጠፋችሁም ዘንድ የምሰድደውን የራብ ፍላጻ በላያችሁ በሰደድሁ ጊዜ፥ ራብን እጨምርባችኋለሁ፥ የእንጀራችሁንም በትር እሰብራለሁ።

17ራብንና ክፉዎችን አራዊት እሰድድባችኋለሁ፥ ልጆቻችሁንም ያጠፋሉ፤ ቸነፈርና ደምም በአንቺ ዘንድ ያልፋሉ፤ ሰይፍንም አመጣብሻለሁ። እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።

ማብራሪያ

5:1-4 ነቢዩ የራሱን ፀጉርና ፂሙን መላጨት አለበት፣ ይህም እግዚአብሔር ያንን ሕዝብ ሙሉ በሙሉ እንደጣለውና እንደተወው ያመለክታል። አንዱ ክፍል በከተማዋ መካከል በእሳት መቃጠል አለበት፤ ይህም እጅግ ብዙዎች በረሃብና በቸነፈር እንደሚጠፉ ያመለክታል። ሌላኛው ክፍል ቁራጭ ቁራጭ ተደርጎ እንዲበተን ነበር፤ ይህም በሰይፍ የሞቱትን ብዙዎችን ይወክላል። ሌላኛው ክፍል በነፋስ መበተን ነበረበት፤ ይህም አንዳንዶች በድል አድራጊው ምድር እንደሚማረኩ፣ ሌሎች ደግሞ ለመጠለያ ወደ ጎረቤት አገሮች እንደሚሸሹ…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV “Now, son of man, take a sharp sword and use it as a barber's razor to shave your head and your beard. Then take a set … English BCV “ንስኻ ድማ፥ ኣታ ወዲ ሰብ፥ ከም መላፀ ላፃዪ ዝበለ በሊሕ ሰይፊ ውሰድ እሞ፥ ርእስኻን ጭሕምኻን ተላፀየሉ፤ ሚዛን ወሲድካውን ነቲ ፀጕሪ ምቐሎ። ትግርኛ GAZBIB Ammas Waaqayyo,“Yaa mucaa namaa! Ati billaa qara qabeessa fudhadhuutii akka qarabaatti ittiin mataa kee fi areeda kee h… Afaan Oromoo BCV GIZ ወአንተ ወልደ ዕጓለ እመሕያው ንሣእ ለከ ኲናት በሊሕ ዘይበልሕ እምላጼ ቀራፂ፡ ተሣየጥ ለከ ወተላፀይ ባቲ ርእስከ ወጽሕመከ፡ ወትነሥእ ለከ እብነ መዳልወ ወትደልዎ ወትከፍሎሙ። giz GAZGAZ Ammas Waaqayyo,“Yaa mucaa namaa! Ati billaa qara qabeessa fudhadhuutii akka qarabaatti ittiin mataa kee fi areeda kee h… Afaan Oromoo BCV aksum “ንስኻ ድማ፥ ኣታ ወዲ ሰብ፥ ከም መላፀ ላፃዪ ዝበለ በሊሕ ሰይፊ ውሰድ እሞ፥ ርእስኻን ጭሕምኻን ተላፀየሉ፤ ሚዛን ወሲድካውን ነቲ ፀጕሪ ምቐሎ። ትግርኛ AMHNIV “አንተም፤ የሰው ልጅ ሆይ፤ የተሳለ ሰይፍ ወስደህ እንደ ጢም መላጫ ጠጒርህንና ጢምህን ተላጭበት፤ ጠጒሩንም በሚዛን ከፋፍል። አማርኛ SWAHSUV Nawe, mwanadamu, ujipatie upanga mkali, kama wembe wa kinyozi ujipatie, ukaupitishe juu ya kichwa chako na ndevu zako; … Kiswahili