ትንቢተ ሕዝቅኤል 5

AMHNIVአማርኛ17 ጥቅሶች3:57 አዳምጥ
አዳምጥ 3:57 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“አንተም፤ የሰው ልጅ ሆይ፤ የተሳለ ሰይፍ ወስደህ እንደ ጢም መላጫ ጠጒርህንና ጢምህን ተላጭበት፤ ጠጒሩንም በሚዛን ከፋፍል።

2የከበባው ጊዜ ሲፈጸም የጠጒሩን ሢሶ በከተማው ውስጥ አቃጥለው፤ ሌላውን ሢሶ ጠጒር በከተማዪቱ ዙሪያ ሁሉ በሰይፍ ቈራርጠው፤ የቀረውንም ሢሶ ደግሞ ለነፋስ በትነው፤ እኔም በተመዘዘ ሰይፍ አሳ ድዳቸዋለሁና።

3ደግሞም ከጠጒሮቹ ጥቂት ወስደህ በመጐናጸፊያህ ጫፍ ቋጥር፤

4እንደ ገናም ከእነዚህ ጥቂት ወስደህ እሳት ውስጥ ጨምራቸው፤ አቃጥላቸውም። እሳትም ከዚያ ወጥቶ ወደ እስራኤል ቤት ሁሉ ይሰራጫል።

5“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘አገሮችን በዙሪያዋ ሁሉ አድርጌ፣ በአሕዛብም መካከል ያስቀመጥኋት ኢየሩሳሌም ይህች ናት።

6እርስዋም በዙሪያዋ ካሉት አገሮችና አሕዛብ ይልቅ በሕጌና በሥርዐቴ ላይ በክፋቷ ዐመፀች፤ ሕጌን ጥላለች፤ ሥርዐቴንም አልተከተለችም።”

7“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በዙሪያችሁ ካሉት አሕዛብ ይልቅ ሞገደኞች ሆናችኋል፤ ሥርዐቴን አልተከተላችሁም፤ ለሕጌም አልታዘዛችሁም። በዙሪያችሁ የሚገኙ አሕዛብ የሚጠብቁትን ሕግ እንኳ አልጠበቃችሁም።

8“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እነሆ፤ እኔ ራሴ በአንቺ ላይ ተነሥቻለሁ፤ በአሕዛብም ፊት ፍርድ አመጣብሻለሁ።

9በጸያፍ ተግባርሽ ሁሉ ምክንያት ካሁን ቀደም ያላደረግሁትን፣ ወደ ፊትም የማላደርገውን በአንቺ ላይ አደርጋለሁ።

10ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን፣ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፤ ፍርድንም አመጣብሻለሁ፤ ከአንቺ የተረፉትንም ለነፋስ እበትናለሁ።

11ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ መቅደሴን በረከሱ ምስሎችሽና በጸያፍ ተግባርሽ ሁሉ ስላጐደፍሽ፣ ፊቴን ከአንቺ እመልሳለሁ፤ በርኅራኄ አልመለከትሽም፤ አልምርሽም።

12ከሕዝብሽ ሢሶው በቸነፈር ይሞታል፤ በመካከልሽም በራብ ያልቃል፤ ሌላው ሢሶ ከቅጥርሽ ውጪ በሰይፍ ይወድቃል፤ የቀረውን ሢሶ ደግሞ ለነፋስ እበትናለሁ፤ በተመዘዘም ሰይፍ አሳድደዋለሁ።

13“ከዚያም ቍጣዬ ይበርዳል፤ በእነርሱ ላይ የመጣው መቅሠፍቴ ይመለሳል፤ ስበቀላቸው እረካለሁ፤ በእነርሱም ላይ መዓቴን ካወረድሁ በኋላ፣ እኔ እግዚአብሔር በቅናት እንደ ተናገርሁ ያውቃሉ።

14“በዙሪያሽ ባሉ አሕዛብ መካከል፤ በአጠገብሽም በሚያልፉ ሁሉ ፊት ባድማና መሳለቂያ አደርግሻለሁ።

15በቍጣና በመዓት፣ እንዲሁም በጭካኔ ፍርድ በማመጣብሽ ጊዜ፣ በዙሪያሽ ባሉ አሕዛብ ዘንድ የመሣቂያና የመሣለቂያ፣ የተግሣጽና የማስደንገጫ ምልክት ትሆኛለሽ። እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።

16የሚገድለውንና አጥፊ የሆነውን የራብ ፍላጻ በእናንተ ላይ በምወረውርበት ጊዜ በእርግጥ ላጠፋችሁ እሰድዳለሁ። በራብ ላይ ራብ አመጣባችኋለሁ፤ የምግብ ምንጫችሁንም አደርቃለሁ።

17ራብንና የዱር አራዊትን እሰድባችኋለሁ፤ እነርሱም ልጅ አልባ ያደርጓችኋል። ቸነፈርና ደም መፋሰስ ያጥለቀልቃችኋል፤ ሰይፍንም አመጣባችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።”

ማብራሪያ

5:1-4 ነቢዩ የራሱን ፀጉርና ፂሙን መላጨት አለበት፣ ይህም እግዚአብሔር ያንን ሕዝብ ሙሉ በሙሉ እንደጣለውና እንደተወው ያመለክታል። አንዱ ክፍል በከተማዋ መካከል በእሳት መቃጠል አለበት፤ ይህም እጅግ ብዙዎች በረሃብና በቸነፈር እንደሚጠፉ ያመለክታል። ሌላኛው ክፍል ቁራጭ ቁራጭ ተደርጎ እንዲበተን ነበር፤ ይህም በሰይፍ የሞቱትን ብዙዎችን ይወክላል። ሌላኛው ክፍል በነፋስ መበተን ነበረበት፤ ይህም አንዳንዶች በድል አድራጊው ምድር እንደሚማረኩ፣ ሌሎች ደግሞ ለመጠለያ ወደ ጎረቤት አገሮች እንደሚሸሹ…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የተሳለን ጐራዴ ውሰድ፥ እንደ ጢም መላጫ ወደ አንተ ትወስደዋለህ፥ ራስህንና ጢምህንም ትላጭበታለህ፤ ሚዛንንም ውሰድ ጠጕሩንም ትከፋፍላለህ። አማርኛ ENGNIV “Now, son of man, take a sharp sword and use it as a barber's razor to shave your head and your beard. Then take a set … English BCV “ንስኻ ድማ፥ ኣታ ወዲ ሰብ፥ ከም መላፀ ላፃዪ ዝበለ በሊሕ ሰይፊ ውሰድ እሞ፥ ርእስኻን ጭሕምኻን ተላፀየሉ፤ ሚዛን ወሲድካውን ነቲ ፀጕሪ ምቐሎ። ትግርኛ GAZBIB Ammas Waaqayyo,“Yaa mucaa namaa! Ati billaa qara qabeessa fudhadhuutii akka qarabaatti ittiin mataa kee fi areeda kee h… Afaan Oromoo BCV GIZ ወአንተ ወልደ ዕጓለ እመሕያው ንሣእ ለከ ኲናት በሊሕ ዘይበልሕ እምላጼ ቀራፂ፡ ተሣየጥ ለከ ወተላፀይ ባቲ ርእስከ ወጽሕመከ፡ ወትነሥእ ለከ እብነ መዳልወ ወትደልዎ ወትከፍሎሙ። giz GAZGAZ Ammas Waaqayyo,“Yaa mucaa namaa! Ati billaa qara qabeessa fudhadhuutii akka qarabaatti ittiin mataa kee fi areeda kee h… Afaan Oromoo BCV aksum “ንስኻ ድማ፥ ኣታ ወዲ ሰብ፥ ከም መላፀ ላፃዪ ዝበለ በሊሕ ሰይፊ ውሰድ እሞ፥ ርእስኻን ጭሕምኻን ተላፀየሉ፤ ሚዛን ወሲድካውን ነቲ ፀጕሪ ምቐሎ። ትግርኛ SWAHSUV Nawe, mwanadamu, ujipatie upanga mkali, kama wembe wa kinyozi ujipatie, ukaupitishe juu ya kichwa chako na ndevu zako; … Kiswahili