ትንቢተ ሕዝቅኤል 2

AMHEVGአማርኛ10 ጥቅሶች1:38 አዳምጥ
አዳምጥ 1:38 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ በእግርህ ቁም እኔም እናገርሃለሁ፡ አለኝ።

2በተናገረኝም ጊዜ መንፈስ ገባብኝ በእግሬም አቆመኝ፥ የሚናገረኝንም ሰማሁ።

3እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ በእኔ ላይ ወደ ዐመፁ ወደ ዓመፀኞች ሰዎች ወደ እስራኤል ልጆች እልክሃለሁ። እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ድረስ ዐመፁብኝ።

4እነርሱ ፊታቸው የተጨማተረ ልባቸውም የደነደነ ልጆች ናቸው። እኔ ወደ እነርሱ እልክሃለሁ፤ አንተም፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ በላቸው።

5እነርሱም ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቢሰሙ ወይም ባይሰሙ ነቢይ በመካከላቸው እንዳለ ያውቃሉ።

6አንተ፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ኵርንችትና እሾህ ከአንተ ጋር ቢኖሩም፥ አንተም በጊንጦች መካከል ብትቀመጥም፥ አትፍራቸው፥ ቃላቸውንም አትፍራ፤ አንተ ቃላቸውን አትፍራ፥ ከፊታቸውም የተነሣ አትደንግጥ፤ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና።

7እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቢሰሙ ወይም ባይሰሙ ቃሌን ትነግራቸዋለህ።

8አንተ ግን፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የምነግርህን ስማ፤ እንደዚያ እንደ ዓመፀኛው ቤት ዓመፀኛ አትሁን፤ አፍህን ክፈት የምሰጥህንም ብላ።

9ባየሁም ጊዜ፥ እነሆ፥ እጅ ወደ እኔ ተዘርግታ ነበር፤ እነሆም፥ የመጽሐፍ ጥቅልል ነበረባት።

10በፊቴም ዘረጋው፥ በውስጥና በውጭም ተጽፎበት ነበር፤ ልቅሶና ኀዘን ዋይታም ተጽፎበት ነበር።

ማብራሪያ

2:1-5 ዕዝቅኤል በብዙዎቹ ራዕዮች እንዳይታበይ፣ አሁንም የሰው ልጅ፣ ደካማና ሟች ፍጡር መሆኑ ይታሰብለት ነበር። ክርስቶስ ራሱን የሰው ልጅ ብሎ ይጠራ እንደነበር ሁሉ፣ ይህ ደግሞ የተከበረ መለያ ነበር። የዕዝቅኤል አኳኋን አክብሮትን ያሳየ ነበር፤ ነገር ግን መቆሙ ለሥራው የላቀ ዝግጁነትንና ብቃትን ያመለክት ነበር። እግዚአብሔር የሚያዘንበትን ለማድረግ ዝግጁ ሆነን ስንቆም ይናገረናል። ዕዝቅኤል የራሱ ብርታት ስላልነበረው፣ መንፈሱ ወደ እርሱ ገባ። እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገውን ሁሉ በእኛ ውስጥ ለመሥራት በጸጋው ደስ ይለዋል። መንፈስ ቅዱስ ፈቃዳችንን ወደ ግዴታችን በማዘንበል በእግራችን እንድንቆም ያደርገናል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6