ትንቢተ ሕዝቅኤል 15

AMHEVGአማርኛ8 ጥቅሶች1:17 አዳምጥ
አዳምጥ 1:17 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦

2የሰው ልጅ ሆይ፥ የወይን ግንድ፥ በዱር ዛፎች መካከል ያለ የወይን አረግ፥ ከዛፍ ሁሉ ይልቅ ብልጫው ምንድር ነው?

3በውኑ ሥራ የሚሠራበትን እንጨት ከእርሱ ይወስዳሉን? ወይስ ሰዎች ዕቃ የሚንጠለጠልበትን ኵላብ ከእርሱ ይወስዳሉን?

4እነሆ፥ ለመቃጠል በእሳት ላይ ተጥሎአል፥ እሳቱም ሁለቱን ጫፎቹን በልቶአል፥ መካከሉም ተቃጥሎአል፤ በውኑ ለሥራ ይጠቅማልን?

5እነሆ፥ ደህና ሳለ ለሥራ ካልጠቀመ፥ ይልቁንስ እሳት ከበላው እርሱም ከተቃጠለ በኋላ እንዴት ሥራ ይሠራበታል?

6ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዱር ዛፎች መካከል ያለውን የወይን ግንድ እሳት ይበላው ዘንድ እንደ ሰጠሁት፥ እንዲሁ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳልፌ እሰጣለሁ።

7ፊቴንም በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ ከእሳትም ይወጣሉ፥ እሳት ግን ይበላቸዋል፤ ፊቴንም በእነርሱ ላይ ባደረግሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

8ዓመፅን አድርገዋልና ምድሪቱን ባድማ አደርጋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

ምዕራፍ ፲፭፥፩-፰ - ኢየሩሳሌም እንደማያፈራ ወይን።

ፍሬ የሚያፈራ ወይን ጠቃሚ ነው። ነገር ግን የማያፈራ ከሆነ ዋጋ የለውም፤ ከንቱ ነው፤ ወደ እሳትም ይጣላል። እንዲሁ ሰው ለእግዚአብሔር በመኖር ክቡር የሆነ ፍሬን ማፍራት ይችላል፤ ይህም የህልውናው ብቸኛ ዓላማ ነው። ይህንንም ካልፈጸመ ሊጠፋ እንጂ ምንም ጥቅም የለውም። እንግዲህ እግዚአብሔርንና እውነተኛ ሃይማኖትን ሙሉ በሙሉ በመዘንጋት ለሚኖሩ ሰዎች ምንኛ ዓይነ ስውርነት ተጣብቆባቸዋል…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6