መጽሐፈ መክብብ 8

AMHNIVአማርኛ17 ጥቅሶች3:12 አዳምጥ
አዳምጥ 3:12 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ነገሮችን መግለጽ የሚችል፣ እንደ ጠቢብ ያለ ሰው ማን ነው? ጥበብ የሰውን ፊት ታበራለች፤ የከበደ ገጽታውንም ትለውጣለች።

2በእግዚአብሔር ፊት መሐላ ስለፈጸምህ፣ የንጉሥን ትእዛዝ አክብር እልሃለሁ።

3ከንጉሥ ፊት ተጣድፈህ አትውጣ፤ የወደደውንም ማድረግ ስለሚችል ለጥፋት አትሰለፍ።

4የንጉሥ ቃል የበላይ ስለ ሆነ እርሱን፣ “ምን ታደርጋለህ?” ማን ሊለው ይችላል?

5እርሱን የሚታዘዝ ሁሉ አይጐዳም፤ ጥበበኛም ልብ ትክክለኛውን ጊዜና ተገቢውን አሠራር ያውቃል።

6የሰው መከራ እጅግ ቢጫነውም፣ ለሁሉም ነገር ትክክለኛ ጊዜና ተገቢ አሠራር አለው።

7ሰው የወደ ፊቱን ስለማያውቅ፣ ሊመጣ ያለውን ማን ሊነግረው ይችላል?

8ሰው ነፋስን መቈጣጠር አይችልም፤ በዕለተ ሞቱም ላይ ሥልጣን ያለው ማንም የለም፤ በጦርነት ጊዜ ማንም ከግዴታ ነጻ እንደማይሆን፣ ክፋትም የሚለማመዷትን አትለቃቸውም።

9ከፀሓይ በታች የተሠራውን ሁሉ በአእምሮዬ መርምሬ፣ ይህን ሁሉ አየሁ። ሰው ሰውን ለመጒዳት ገዥ የሚሆንበት ጊዜ አለ።

10እንዲሁም ወደ ቅዱሱ ስፍራ ይመጡና ይሄዱ የነበሩት ክፉዎች ተቀብረው አየሁ፤ ይህን ባደረጉበት ከተማም ይመሰገኑ ነበር፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

11በወንጀል ላይ ባፋጣኝ ፍርድ ካልተሰጠ፣ የሰዎች ልብ ክፉን በማድረግ ዕቅድ ይሞላል።

12ኀጥእ መቶ ወንጀል ሠርቶ ዕድሜው ቢረዝምም፣ እግዚአብሔርን የሚያከብሩ፣ ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላቸው ሰዎች መልካም እንደሚሆንላቸው ዐውቃለሁ።

13ነገር ግን ክፉዎች እግዚአብሔርን ስለማይፈሩ መልካም አይሆንላቸውም፤ ዕድሜያቸው እንደ ጥላ አይረዝምም።

14በምድር ላይ የሚከሠት ሌላም ከንቱ ነገር አለ፤ ጻድቃን ለክፉዎች የሚገባውን፣ ክፉ ሰዎችም ለጻድቃን የሚገባውን ይቀበላሉ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ነው አልሁ።

15ለሰው፣ ከፀሓይ በታች ከመብላት፣ ከመጠጣትና ከመደሰት ሌላ የተሻለ ነገር ስለሌለ፣ በሕይወት ደስ መሰኘት መልካም ነው አልሁ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ከፀሓይ በታች በሰጠው የሕይወት ዘመኑ ሁሉ በሥራው ደስታ ይኖረዋል።

16ጥበብን ለማወቅና ሌት ተቀን እንቅልፍ የማያውቀውን በምድር ያለውን የሰውን ድካም ለመገንዘብ በአእምሮዬ ስመረምር፣

17እግዚአብሔር ያደረገውን ሁሉ አየሁ። ከፀሓይ በታች የሚደረገውን ማንም ሊያውቅ አይችልም፤ ሰው ለመመርመር ብዙ ቢጥርም፣ ትርጒሙን ማግኘት አይችልም፤ ጠቢብም እንኳ ዐውቀዋለሁ ቢል፣ ፈጽሞ ሊገነዘበው አይችልም።

ማብራሪያ

8:1-5

በሀብት፣ በሥልጣን፣ በክብር ወይም በብቃት ከሚታወቁት የሰው ልጆች መካከል ማንም ቢሆን እንደ ጠቢቡ ሰው የላቀ፣ ጠቃሚ ወይም ደስተኛ አይደለም። የእግዚአብሔርን ቃል መግለጥ ወይም ከእርሱ እውነቶችና ከአሠራሩ በትክክል ማስተማር የሚችል ሌላ ማን ነው? ደካማና ጥገኛ የሆኑ ፍጡራን ሁሉን ቻይን ማመፅ እንዴት ያለ እብደት ሊሆን ነው! እጅግ በርካቶች የተሳሳተ ፍርድ በመስጠት በዚህም ሕይወት በሚመጣውም በራሳቸው ላይ መከራን ያመጣሉ!

፰፥፮-፰ እግዚአብሔር በጥበቡ የወደፊቱን ክስተቶች እውቀት ከእኛ የሰወረው፣ ሁልጊዜም ለለውጦች ዝግጁ እንድንሆን ዘንድ ነው። ሁላችንም እንሞታለን፤ ምንም መሸሽ ወይም መደበቂያ ስፍራ ሊያድነን አይችልም፣ እንዲሁም ሙሉ በሙሉ መቋቋም የሚያስችል ምንም ዓይነት መሳሪያ የለም። በየቀኑ ዘጠና ሺህ ሰዎች፣ በየደቂቃው ከስድሳ በላይ ሰዎች፣ በየቅጽበቱ ደግሞ አንድ ሰው ይሞታል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6