ትንቢተ ዳንኤል 7

AMHEVGአማርኛ28 ጥቅሶች5:43 አዳምጥ
አዳምጥ 5:43 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በባቢሎን ንጉሥ በብልጣሶር በመጀመሪያው ዓመት ዳንኤል በአልጋው ላይ ሕልምንና የራሱን ራእይ አየ፤ ከዚያም በኋላ ሕልሙን ጻፈ፥ ዋነኛውንም ነገር ተናገረ።

2ዳንኤልም ተናገረ እንዲህም አለ፦ “በሌሊት በራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ አራቱ የሰማይ ነፋሳት በታላቁ ባሕር ላይ ይጋጩ ነበር።

3አራትም ታላላቅ አራዊት ከባሕር ወጡ፥ እያንዳንዲቱም ልዩ ልዩ ነበረች።

4መጀመሪያይቱ አንበሳ ትመስል ነበር፥ የንስርም ክንፍ ነበራት፤ ክንፎችዋም ከእርስዋ እስኪነቀሉ ድረስ አይ ነበር፥ ከምድርም ከፍ ከፍ ተደረገች፥ እንደ ሰውም በሁለት እግር እንድትቆም ተደረገች፥ የሰውም ልብ ተሰጣት።

5እነሆም፥ ሁለተኛይቱ ድብ የምትመስል ሌላ አውሬ ነበረች፥ በአንድ ወገንም ቆመች፥ ሦስትም የጐድን አጥንቶች በአፍዋ ውስጥ በጥርስዋ መካከል ነበሩ፤ እንደዚህም፦ ‘ተነሥተሽ እጅግ ሥጋ ብዪ፡’ ተባለላት።

6“ከዚህም በኋላ፥ እነሆ፥ ነብር የምትመስል በጀርባዋም ላይ አራት የወፍ ክንፎች የነበሩአት ሌላ አውሬ አየሁ፤ ለአውሬይቱም አራት ራሶች ነበሩአት፥ ግዛትም ተሰጣት።

7“ከዚህም በኋላ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ የምታስፈራና የምታስደነግጥ እጅግም የበረታች፥ ታላላቅም የብረት ጥርሶች የነበሩአት አራተኛ አውሬ ነበረች፤ ትበላና ታደቅቅ ነበር፥ የቀረውንም በእግርዋ ትረግጥ ነበር፤ ከእርስዋም በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየች ነበረች፤ አሥር ቀንዶችም ነበሩአት።

8“ቀንዶችንም ተመለከትሁ፤ እነሆም፥ በመካከላቸው ሌላ ትንሽ ቀንድ ወጣ፥ በፊቱም ከቀደሙት ቀንዶች ሦስት ተነቃቀሉ፤ እነሆም፥ በዚያ ቀንድ እንደ ሰው ዓይኖች የነበሩ ዓይኖች በትዕቢትም የሚናገር አፍ ነበሩበት።

9ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ፥ የራሱም ጠጕር እንደ ጥሩ ጥጥ ነበረ፤ ዙፋኑም የእሳት ነበልባል ነበረ፥ መንኰራኵሮቹም የሚነድድ እሳት ነበሩ።

10የእሳትም ፈሳሽ ከፊቱ ይፈልቅና ይወጣ ነበር፤ ሺህ ጊዜ ሺህ ያገለግሉት ነበር፥ እልፍ አእላፋትም በፊቱ ቆመው ነበር፤ ፍርድም ሆነ፥ መጻሕፍትም ተገለጡ።

11የዚያን ጊዜም ቀንዱ ይናገረው ከነበረው ከታላቁ ቃል ድምፅ የተነሣ አየሁ፤ አውሬይቱም እስክትገደል፥ አካልዋም እስኪጠፋ ድረስ፥ በእሳትም ለመቃጠል እስክትሰጥ ድረስ አየሁ።

12ከቀሩትም አራዊት ግዛታቸው ተወሰደ፤ የሕይወታቸው ዕድሜ ግን እስከ ዘመንና እስከ ጊዜ ድረስ ረዘመ።

13በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት።

14ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።

15“በእኔም በዳንኤል በሥጋዬ ውስጥ መንፈሴ ደነገጠች፥ የራሴም ራእይ አስቸገረኝ።

16በዚያም ከቆሙት ወደ አንዱ ቀርቤ ስለዚህ ሁሉ እውነቱን ጠየቅሁት፤ እርሱም ነገረኝ፥ የነገሩንም ፍቺ አስታወቀኝ።

17‘እነዚህ አራቱ ታላላቅ አራዊት ከምድር የሚነሡ አራት ነገሥታት ናቸው።

18ነገር ግን የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን ይወስዳሉ፥ እስከ ዘላለም ዓለምም መንግሥቱን ይወርሳሉ።’

19“ከዚህም በኋላ ከቀሩት ሁሉ ተለይታ እጅግ ስለምታስፈራው፥ ጥርሶችዋም የብረት ጥፍሮችዋም የናስ ስለሆኑት፥ ስለምትበላውና ስለምታደቅቀው የቀረውንም በእግርዋ ስለምትረግጠው ስለ አራተኛይቱ አውሬ፥

20በራስዋም ላይ ስለ ነበሩ ስለ አሥር ቀንዶች፥ በኋላም ስለ ወጣው፥ በፊቱም ሦስቱ ስለ ወደቁ፥ ዓይኖችና ትዕቢት የተናገረ አፍ ስለ ነበሩት፥ መልኩም ከሌሎች ስለ በለጠ ስለ ሌላው ቀንድ እውነቱን ለማወቅ ፈቀድሁ።

21እነሆም፥ ያ ቀንድ ከቅዱሳን ጋር ሲዋጋ አየሁ፥

22በዘመናት የሸመገለው እስኪመጣ ድረስ፥ ፍርድም ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪሰጥ ድረስ፥ ቅዱሳኑም መንግሥቱን የሚወስዱበት ዘመን እስኪመጣ ድረስ አሸነፋቸውም።

23እንዲህም አለ፦ ‘አራተኛይቱ አውሬ በምድር ላይ አራተኛ መንግሥት ትሆናለች፤ እርሱም ከመንግሥታት ሁሉ የተለየ ይሆናል፥ ምድሪቱንም ሁሉ ይበላል፥ ይረግጣታል ያደቅቃትማል።

24አሥሩም ቀንዶች ከዚያ መንግሥት የሚነሡ አሥር ነገሥታት ናቸው፤ ከእነርሱም በኋላ ሌላ ይነሣል፥ እርሱም ከፊተኞች የተለየ ይሆናል፥ ሦስቱንም ነገሥታት ያዋርዳል።

25በልዑሉም ላይ ቃልን ይናገራል፥ የልዑልንም ቅዱሳን ይሰባብራል፥ ዘመናትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል፤ እስከ ዘመንና እስከ ዘመናት እስከ እኵሌታ ዘመንም በእጁ ይሰጣሉ።

26ነገር ግን ፍርድ ይሆናል፥ እስከ ፍጻሜም ድረስ ያፈርሱትና ያጠፉት ዘንድ ግዛቱን ያስወግዱታል።

27መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ ይሰጣል፤ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቶችም ሁሉ ይገዙለታል ይታዘዙለትማል።’

28“የነገሩም ፍጻሜ እስከዚህ ድረስ ነው። እኔም ዳንኤል በአሳቤ እጅግ ተቸገርሁ፥ ፊቴም ተለወጠብኝ፤ ዳሩ ግን ነገሩን በልቤ ጠብቄአለሁ።”

ማብራሪያ

7:1-8 ይህ ራእይ ከናቡከደነፆር ሕልም ጋር አንድ ዓይነት ትንቢታዊ ምሳሌዎችን ይዟል። በነፋሳት የተናወጠው ታላቁ ባሕር፣ በሥልጣን ጥመኞች መኳንንትና ድል አድራጊዎች የሚረበሹትን ምድርንና በእርሷ ላይ የሚኖሩትን ሕዝቦች ያመለክታል። አራቱ አራዊት ደግሞ የናቡከደነፆር ምስል አራት ክፍሎች እንደነበሩት፣ አንድ ዓይነት አራት መንግሥታትን ያመለክታሉ። ኃያላን ድል አድራጊዎች በኃጢአተኛው ዓለም ላይ የእግዚአብሔር የበቀል መሣሪያዎች ብቻ ናቸው። አረመኔው አውሬ የባሕርያቸውን አስጸያፊ ገጽታዎች ይወክላል። ነገር ግን ለእያንዳንዱ የተሰጠው ግዛት ወሰን አለው፤ ቁጣቸው ጌታን ለማመስገን ይውላል፣ የቀረውንም እርሱ ይገታዋል።

7:9-14 እነዚህ ጥቅሶች በእነርሱ ላይ ለሚደርሰው ስደት የእግዚአብሔር ሕዝቦች መጽናኛና ድጋፍ ይሆናሉ። ስለሚመጣው ፍርድ የሚናገሩ ብዙ የአዲስ ኪዳን ትንቢቶች ይህንን ራእይ በግልጽ ያመለክታሉ፤ በተለይም ራእይ 20:11,12። መሲሑ እዚህ ላይ የሰው ልጅ ተብሎ ተጠርቷል፤ እርሱ የኃጢአተኛ ሥጋን ምሳሌ ለብሶ እንደ ሰው ተገኝቷል፣ ነገር ግን እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV In the first year of Belshazzar king of Babylon, Daniel had a dream, and visions passed through his mind as he was lyin… English BCV ብልጣሶር ኣብ ባቢሎን ምስ ነገሰ፥ ኣብታ ቐዳመይቲ ዓመቱ፥ ዳንኤል ኣብ ዓራቱ እንተሎ ሕልምን ራእይን ረአየ። ሽዑ ነቲ ሕልሚ ፀሓፎ፤ ርእሰ ነገሩውን ተናገረ፤ ትግርኛ GAZBIB Bara Belshaazaar mootii Baabilon waggaa duraa keessa, Daani'el siree isaa irra ciisee utuu jiruu abjuu arge, mul'annis … Afaan Oromoo BCV GIZ በቀዳማዊ ዓመተ መንግሥቱ ለበልጣሰር ንጉሠ ከለዴዎን ሐለመ ዳንኤል ሕልመ ወርእየ ርእሶ በውስተ ምስካቡ ወጸሐፈ ሕልሞ። giz GAZGAZ Bara Belshaazaar mootii Baabilon waggaa duraa keessa, Daani'el siree isaa irra ciisee utuu jiruu abjuu arge, mul'annis … Afaan Oromoo BCV aksum ብልጣሶር ኣብ ባቢሎን ምስ ነገሰ፥ ኣብታ ቐዳመይቲ ዓመቱ፥ ዳንኤል ኣብ ዓራቱ እንተሎ ሕልምን ራእይን ረአየ። ሽዑ ነቲ ሕልሚ ፀሓፎ፤ ርእሰ ነገሩውን ተናገረ፤ ትግርኛ AMHNIV የባቢሎን ንጉሥ ቤልሻዛር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት ዳንኤል በዐልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ ሕልም አለመ፤ ራእይም አየ፤ የሕልሙንም ዋና ሐሳብ ጻፈው። አማርኛ SWAHSUV Katika mwaka wa kwanza wa Belshaza, mfalme wa Babeli, Danieli aliona ndoto, na maono ya kichwa chake, kitandani mwake; … Kiswahili