ትንቢተ ዳንኤል 3

AMHEVGአማርኛ30 ጥቅሶች6:47 አዳምጥ
አዳምጥ 6:47 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ንጉሡ ናቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ክንድ ወርዱም ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቁን ምስል አሠራ፤ በባቢሎንም አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው።

2ንጉሡም ናቡከደነፆር መኳንንትንና ሹማምቶችን፥ አዛዦችንና አዛውንቶችን፥ በጅሮንዶችንና አማካሪዎችን፥ መጋቢዎችንም፥ አውራጃ ገዦችንም ሁሉ ይሰበስቡ ዘንድ፥ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ይመጡ ዘንድ ላከ።

3በዚያን ጊዜም መኳንንቱና ሹማምቶቹ፥ አዛዦቹና አዛውንቶቹ፥ በጅሮንዶቹና አማካሪዎቹ፥ መጋቢዎቹና አውራጃ ገዦቹ ሁሉ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ተሰበሰቡ፤ ናቡከደነፆርም ባቆመው ምስል ፊት ቆሙ።

4አዋጅ ነጋሪውም እየጮኸ እንዲህ አለ፦ “ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የምትናገሩ ሆይ፥

5የመለከትንና የእንቢልታን፥ የመሰንቆንና የክራርን፥ የበገናንና የዋሽንትን፥ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፥ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል።

6ተደፍቶም የማይሰግድ በዚያን ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል።”

7ስለዚህ በዚያን ጊዜ አሕዛብ ሁሉ የመለከቱንና የእንቢልታውን፥ የመሰንቆውንና የክራሩን፥ የበገናውንና የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የተናገሩ ሁሉ ተደፉ፥ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቅ ምስል ሰገዱ።

8በዚያን ጊዜም ከለዳውያን ቀርበው አይሁድን ከሰሱ።

9ለንጉሡም ለናቡከደነፆር ተናገሩ እንዲህም አሉ፦ “ንጉሥ ሆይ፥ ሺህ ዓመት ንገሥ።

10አንተ፥ ንጉሥ ሆይ፦ ‘የመለከትንና የእንቢልታን፥ የመሰንቆንና የክራርን፥ የበገናንና የዋሽንትን፥ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ የሚሰማ ሰው ሁሉ ተደፍቶ ለወርቁ ምስል ይስገድ፤

11ተደፍቶም የማይሰግድ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል፡’ ብለህ አዘዝህ።

12በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምሃቸው ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም የሚባሉ አይሁድ አሉ፤ ንጉሥ ሆይ፥ እነዚህ ሰዎች ትእዛዝህን እንቢ ብለዋል፤ አማልክትህን አያመልኩም፥ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል አይሰግዱም።”

13ናቡከደነፆርም በብስጭትና በቍጣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም ያመጡ ዘንድ አዘዘ፤ እነዚህንም ሰዎች ወደ ንጉሡ ፊት አመጡአቸው።

14ናቡከደነፆርም፦ “ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ሆይ፥ አምላኬን አለማምለካችሁ፥ ላቆምሁትም ለወርቁ ምስል አለመስገዳችሁ እውነት ነውን?

15አሁንም የመለከቱንና የእንቢልታውን የመሰንቆውንና የክራሩን የበገናውንና የዋሽንቱን የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ተደፍታችሁ ላሠራሁት ምስል ብትሰግዱ መልካም ነው፤ ባትሰግዱ ግን በዚያ ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችሁ፤ ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው?” ብሎ ተናገራቸው።

16ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም መለሱ ንጉሡንም፦ “ናቡከደነፆር ሆይ፥ በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም።

17የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፥ ንጉሥ ሆይ!

18ነገር ግን፥ ንጉሥ ሆይ፥ እርሱ ባያድነን፥ አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ፡” አሉት።

19የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም ላይ ቍጣ ሞላበት፥ የፊቱም መልክ ተለወጠባቸው፤ እርሱም ተናገረ፥ የእቶንም እሳት ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድርገው እንዲያነድዱት አዘዘ።

20ሲድራቅንና ሚሳቅንም አብደናጎንም ያስሩ ዘንድ፥ ወደሚነድድም ወደ እቶን እሳት ይጥሉአቸው ዘንድ በሠራዊቱ ውስጥ ከነበሩት ኃያላን አዘዘ።

21የዚያን ጊዜም እነዚህ ሰዎች ከሰናፊላቸውና ከቀሚሳቸው ከመጐናጸፊያቸውም ከቀረውም ልብሳቸው ጋር ታስረው በሚነድድ በእቶን እሳት ውስጥ ተጣሉ።

22የንጉሡም ትእዛዝ አስቸኳይ ስለሆነ የእቶኑም እሳት እጅግ ስለሚነድድ፥ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው።

23እነዚህም ሦስቱ ሰዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ታስረው በሚነድደው በእቶኑ እሳት ውስጥ ወደቁ።

24የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ፤ አማካሪዎቹንም፦ “ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን?” ብሎ ተናገራቸው። እነርሱም፦ ንጉሥ ሆይ፥ “እውነት ነው፡” ብለው ለንጉሡ መለሱለት።

25እርሱም፦ “እነሆ፥ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም፤ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል፡” ብሎ መለሰ።

26የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር ወደሚነድደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ፦ “እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች፥ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም፥ ኑ ውጡ፡” ብሎ ተናገራቸው። ሲድራቅና ሚሳቅም አብደናጎም ከእሳቱ መካከል ወጡ።

27መሳፍንቱና ሹማምቶቹም አዛዦቹና የንጉሡ አማካሪዎች ተሰብስበው እሳቱ በእነዚያ ሰዎች አካል ላይ ኃይል እንዳልነበረው፥ የራሳቸውም ጠጕር እንዳልተቃጠለች፥ ሰናፊላቸውም እንዳልተለወጠ፥ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው አዩ።

28ናቡከደነፆርም መልሶ፦ “መልአኩን የላከ፥ ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፥ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ።

29እኔም እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም አምላክ ላይ የስድብን ነገር የሚናገር ወገንና ሕዝብ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ይቈረጣሉ፥ ቤቶቻቸውም የጕድፍ መጣያ ይደረጋሉ ብዬ አዝዣለሁ፡” አለ።

30የዚያን ጊዜም ንጉሡ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም በባቢሎን አውራጃ ውስጥ ከፍ ከፍ አደረጋቸው።

ማብራሪያ

3:1-7 የምስሉ ከፍታ ወደ ሠላሳ ክንድ ያህል ሲሆን፣ ምናልባትም መቀመጫው ተጨምሮበት ይሆናል። እንዲሁም ይበልጥ የሚታሰበው ከጥቅል ውድ ብረት የተሰራ ሳይሆን በወርቅ ሳህኖች ብቻ የተሸፈነ ነበር። ትዕቢትና ጠባብ አመለካከት ሰዎችን ተገዢዎቻቸውን ትክክልም ይሁን ስህተት ሃይማኖታቸውን እንዲከተሉ ያስገድዳሉ። ዓለማዊ ጥቅም ሲያጓጓና ቅጣትም ሲያስፈራ፣ እምቢ የሚሉ ጥቂቶች ናቸው። ይህ ለቸልተኞች፣ ለስጋውያንና ለማያምኑት ቀላል ነው፤ እነርሱም አብዛኞቹ ናቸው። አብዛኞቹም በራሳቸው መንገድ ይሄዳሉ። ግድ የለሹ ዓለም በሙዚቃ ዜማ የማይሳበው ወይም በእቶን እሳት አስፈሪነት የማይገፋበት ምንም የከፋ ነገር የለም። በእንደዚህ ባሉ ዘዴዎች ሐሰተኛ አምልኮ ተመስርቶ ሲዘልቅ ቆይቷል።

3:8-18 እውነተኛ አምልኮ መንፈስን የሚያረጋጋ፣ የሚያቀዘቅዝና የሚያለሰልስ ነው። ነገር ግን አጉል እምነትና ለሐሰተኛ አማልክት መሰጠት የሰዎችን ፍላጎት ያነድዳል። ጉዳዩ በአጭር ቃል ተጠቃልሏል፦ "ተመለሱ፣ አለዚያ ትቃጠላላችሁ።" ትዕቢተኞች ሰዎች አሁንም ቢሆን እንደ ናቡከደነፆር፡ "ኃይሉን ፈርቼ የማከብርለት እግዚአብሔር ማነው?" ለማለት ዝግጁ ናቸው። ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ ሊታዘዙ ወይም እንዳልሆኑ አላመነቱም። ሕይወትም ሆነ ሞት ከግምት ውስጥ መግባት የለባቸውም ነበር። ኃጢአትን ለማስወገድ የሚፈልጉ ሰዎች፣ በሚፈተኑበት ወይም በሚፈሩበት ነገር ላይ ግልጽ የሆነ ክፋት ሲታይ፣ ከፈተና ጋር መደራደር የለባቸውም። በዚያ ላይ አትቆሙ፣ ነገር ግን ክርስቶስ እንዳደረገው፡ "ከኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን!" በሉ። ቀጥተኛ መልስ በሚጠበቅበት ጊዜ አሻሚ መልስ አላዘጋጁም። ግዴታቸውን ዋና ጉዳያቸው የሚያደርጉ ሰዎች ስለ ፍጻሜው መጨነቅ ወይም መፍራት አያስፈልጋቸውም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV King Nebuchadnezzar made an image of gold, ninety feet high and nine feet wide, and set it up on the plain of Dura in t… English BCV ንጉስ ናቡከደነፆር ስሳ እመት ዝቑመቱ፥ ሽዱሽተ እመት ዝጐድኑ ናይ ወርቂ ምስሊ ኣስርሐ። ኣብ ጐልጐል ዱራ ኣብ ኣውራጃ ባቢሎንውን ኣቖሞ። ትግርኛ GAZBIB Nebukadnezaar mootichi bifa fakkeenyaa hojjaa isaa dhundhuma jaatamaan, bal'ina isaa immoo dhundhuma ja'aan warqee irra… Afaan Oromoo BCV GIZ አመ ዐሠርቱ ወሰማንቱ ዓመተ መንግሥቱ ለናቡከደነጾር ገብረ ምስለ ዘወርቅ ኑኁ ስሳ በእመት ወግድሙ ስድስ በእመት፤ ወአቀሞ ውስተ ሐቅለ ዱራ ብሔረ ባቢሎን። giz GAZGAZ Nebukadnezaar mootichi bifa fakkeenyaa hojjaa isaa dhundhuma jaatamaan, bal'ina isaa immoo dhundhuma ja'aan warqee irra… Afaan Oromoo BCV aksum ንጉስ ናቡከደነፆር ስሳ እመት ዝቑመቱ፥ ሽዱሽተ እመት ዝጐድኑ ናይ ወርቂ ምስሊ ኣስርሐ። ኣብ ጐልጐል ዱራ ኣብ ኣውራጃ ባቢሎንውን ኣቖሞ። ትግርኛ AMHNIV ንጉሡ ናቡከደነፆር ከፍታው ሥልሳ ክንድ፣ ወርዱ ስድስት ክንድ የሆነ የወርቅ ምስል አሠራ፤ በባቢሎንም አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው። አማርኛ SWAHSUV Nebukadreza, mfalme, alifanya sanamu ya dhahabu, ambayo urefu wake ulikuwa ni dhiraa sitini, na upana wake dhiraa sita;… Kiswahili