ትንቢተ ዳንኤል 12

AMHNIVአማርኛ13 ጥቅሶች2:53 አዳምጥ
አዳምጥ 2:53 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“በዚያን ዘመን ስለ ሕዝብህ የሚቈመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል። መንግሥታት ከተመሠረቱበት ጊዜ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ የመከራ ጊዜ ይሆናል። ነገር ግን በዚያን ጊዜ ስማቸው በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ ይድናሉ።

2በምድር ዐፈር ውስጥ ካንቀላፉት ብዙዎች ይነቃሉ፤ አንዳንዶቹ ለዘላለም ሕይወት፣ ሌሎቹም ለውርደትና ለዘላለም ጕስቍልና ይነሣሉ።

3ጥበበኞች እንደ ሰማይ ጸዳል፣ ብዙዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ።

4ዳንኤል ሆይ፤ አንተ ግን፣ እስከ ፍጻሜው ዘመን ድረስ የመጽሐፉን ቃል ዝጋ፤ አትመውም። ብዙዎች ወዲያ ወዲህ ይራወጣሉ፤ ዕውቀትም ይበዛል።

5እኔም ዳንኤል ተመለከትሁ፤ እነሆ ከፊት ለፊቴ ሌሎች ሁለት ቆመው ነበር፤ አንዱ ከወንዙ በዚህኛው ዳር፣ ሌላው ደግሞ ከወንዙ በዚያኛው ዳር።

6ከእነርሱም አንዱ፣ ከወንዙ ውሃ በላይ የነበረውንና በፍታ የለበሰውን ሰው፣ “እነዚህ አስደናቂ ነገሮች ሊፈጸሙ ምን ያህል ጊዜ ይቀራል?” አለው።

7ከወንዙ ውሃ በላይ የነበረው በፍታ የለበሰው ሰው፣ ቀኝ እጁንና ግራ እጁን ወደ ሰማይ አንሥቶ፣ “ለዘመን፣ ለዘመናት፣ ለዘመንም እኩሌታ ይሆናል፤ የተቀደሰው ሕዝብ ኀይል መሰበር ሲያከትም፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ይፈጸማሉ” ብሎ ለዘላለም በሚኖረው በእርሱ ሲምል ሰማሁ።

8እኔም ሰማሁ፤ ነገር ግን አላስተዋልሁትም፤ ስለዚህ፣ ጌታዬ ሆይ፤ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ ምንድ ነው?” ብዬ ጠየቅሁ።

9እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ዳንኤል ሆይ፤ ቃሉ እስከ ፍጻሜው ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ስለ ሆነ ሂድ፤

10ብዙዎች ይነጻሉ፤ ይጠራሉ፤ እንከን አልባም ይሆናሉ፤ ክፉዎች ግን በክፋታቸው ይጸናሉ፤ ከክፉዎች አንዳቸውም አያስተውሉም፤ ጠቢባን ግን ያስተውላሉ።

11“የዘወትሩ መሥዋዕት ከተቋረጠበትና ጥፋትን የሚያመጣው የጥፋት ርኵሰት ከተተከለበት ጊዜ ጀምሮ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ቀን ይሆናል።

12የሚታገሥና እስከ አንድ ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ አምስት ቀን ፍጻሜ የሚደርስ የተባረከ ነው።

13“አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ፤ ታርፋለህ፤ በቀኖቹ መጨረሻም ተነሥተህ የተመደበልህን ርስት ትቀበላለህ።”

ማብራሪያ

12:1-4. ሚካኤል ማለት "እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው?" ሲሆን፣ ስሙም ከ"ታላቁ አለቃ" ከሚለው ማዕረግ ጋር በመሆን መለኮታዊውን አዳኝ ያመለክታል። ክርስቶስ ስለ ሕዝባችን ልጆች በእነርሱ ፋንታ መስዋዕት ሆኖ ቆመ፤ ለእነርሱ እርግማንን ተሸከመ፣ ከእነርሱም ላይ ለማንሳት። በመሆኑም በጸጋው ዙፋን በእነርሱ ፈንታ እየለመነላቸው ይቆማል።

ከክርስቶስ ተቃዋሚ ጥፋት በኋላም፣ ጌታ ኢየሱስ በመጨረሻው ዘመን በምድር ላይ ይቆማል፤ እርሱም የሕዝቡን ሁሉ ሙሉ ቤዛነት ለማስፈጸም ይታያል። እግዚአብሔር ከስደት ነጻ ማውጣት ሲያደርግላቸው፣ እንደ ሙታን ከሞት መነሣት ነው። ወንጌሉ ሲሰበክ ደግሞ፣ በአፈር ውስጥ የተኙ ብዙዎች፣ አይሁድም ሆኑ አሕዛብ፣ በእርሱ ከጣዖት አምልኮአቸውና ከአይሁድ እምነታቸው ይነቃሉ። በመጨረሻም በአፈር ውስጥ የተኙት ብዙኃን ይነሳሉ፤ ብዙዎች ለሕይወት ይነሣሉ፣ ብዙዎችም ለውርደት።

ለወደፊቱ ሕይወት ለሁሉም ቅዱሳን፣ ለነፍሳቸውና ለዘለዓለም ሕይወታቸው ጥበበኛ ለሆኑት ሁሉ የተጠበቀ ክብር አለ። ብዙዎችን ወደ ጽድቅ የሚመልሱ፣ ኃጢአተኞችንም ከስሕተት መንገዳቸው የሚመልሱ፣ ነፍሳቸውንም ከሞት እንዲድኑ የሚያግዙ (ያዕቆብ 5:20)፣ ወደ ሰማይ እንዲደርሱ የረዷቸው ሰዎች ክብር ይካፈላሉ፣ ይህም የራሳቸውን ክብር ይጨምራል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG “በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤ በዚያም ዘመን በመጽሐፉ… አማርኛ ENGNIV “At that time Michael, the great prince who protects your people, will arise. There will be a time of distress such as … English BCV “በቲ ዘመን እቱይ፥ እቲ ምእንቲ ደቂ ህዝብኻ እስራኤል ዝቐውም፥ ዓብዪ ሓለቓ ሚካኤል፥ ክትስእ እዩ። ሽዑ መንግስቲ ኻብ ዝተመስረተ ጊዜ ጀሚሩ፥ ክሳዕ እቲ ዘመን እቱይ ተርእዩ ዘይፍለጥ፥ ዓ… ትግርኛ GAZBIB Yommus inni anatti dubbachaa ture,“Yeroo sanatti Mikaa'el ergamaa inni guddichi ijoollee saba keef dhaabatu in ka'a; ye… Afaan Oromoo BCV GIZ ወውእተ አሚረ ይትነሣእ ሚካኤል መልአክ ዓቢይ ዘይትቃወም ለደቂቀ ሕዝብከ ወይከውን ዐቢየ ሕማመ እምኔሁ ወምንዳቤ ዘኢኮነ ከማሁ እምአመ ተፈጥረ አሕዛብ ዲበ ምድር እስከ ውእቱ አሚር፤ ወይድኅ… giz GAZGAZ Yommus inni anatti dubbachaa ture,“Yeroo sanatti Mikaa'el ergamaa inni guddichi ijoollee saba keef dhaabatu in ka'a; ye… Afaan Oromoo BCV aksum “በቲ ዘመን እቱይ፥ እቲ ምእንቲ ደቂ ህዝብኻ እስራኤል ዝቐውም፥ ዓብዪ ሓለቓ ሚካኤል፥ ክትስእ እዩ። ሽዑ መንግስቲ ኻብ ዝተመስረተ ጊዜ ጀሚሩ፥ ክሳዕ እቲ ዘመን እቱይ ተርእዩ ዘይፍለጥ፥ ዓ… ትግርኛ SWAHSUV Wakati huo Mikaeli atasimama, jemadari mkuu, asimamaye upande wa wana wa watu wako; na kutakuwa na wakati wa taabu, mfa… Kiswahili