ትንቢተ ዳንኤል 12

AMHEVGአማርኛ13 ጥቅሶች2:20 አዳምጥ
አዳምጥ 2:20 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤ በዚያም ዘመን በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይድናል።

2በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉቱ ብዙዎች ይነቃሉ፤ እኵሌቶቹ ወደ ዘላለም ሕይወት፥ እኵሌቶቹም ወደ እፍረትና ወደ ዘላለም ጕስቍልና።

3ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀዳል፥ ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ።

4ዳንኤል ሆይ፥ አንተ ግን እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ ቃሉን ዝጋ፥ መጽሐፉንም አትም፤ ብዙ ሰዎች ይመረምራሉ፥ እውቀትም ይበዛል።”

5እኔም ዳንኤል አየሁ፤ እነሆም፥ ሁለት ሌሎች ቆመው ነበር፥ አንዱ በዚህ በወንዙ ዳር፥ ሌላውም በዚያ በወንዙ ዳር።

6አንዱም ከወንዙ ውኃ በላይ የነበረውን በፍታም የለበሰውን፦ “የዚህ ድንቅ ፍጻሜ እስከ መቼ ነው?” አለው።

7ከወንዙም ውኃ በላይ የነበረው በፍታም የለበሰው ሰው ቀኝና ግራ እጁን ወደ ሰማይ አንሥቶ፦ “ለዘመንና ለዘመናት ለዘመንም እኵሌታ ነው፤ የተቀደሰውም ሕዝብ ኃይል መበተን በተጨረሰ ጊዜ ይህ ሁሉ ይፈጸማል፡” ብሎ ለዘላለም ሕያው ሆኖ በሚኖረው ሲምል ሰማሁ።

8ሰማሁም ነገር ግን አላስተዋልሁም፤ የዚያን ጊዜም፦ “ጌታዬ ሆይ፥ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ ምንድር ነው?” አልሁ።

9እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “ዳንኤል ሆይ፥ ቃሉ እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ነውና ሂድ፤

10ብዙ ሰዎች ሰውነታቸውን ያጠራሉ ያነጡማል ይነጥሩማል፤ ክፉዎች ግን ክፋትን ያደርጋሉ፤ ክፉዎችም ሁሉ አያስተውሉም፥ ጥበበኞች ግን ያስተውላሉ።

11የዘወትሩም መሥዋዕት ከቀረ ጀምሮ፥ የጥፋትም ርኵሰት ከቆመ ጀምሮ ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ቀን ይሆናል።

12የሚታገሥ፥ እስከ ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ አምስት ቀንም የሚደርስ ምስጉን ነው።

13አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ፤ አንተም ታርፋለህ፥ በቀኑም መጨረሻ በዕጣ ክፍልህ ትቆማለህ።”

ማብራሪያ

12:1-4. ሚካኤል ማለት "እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው?" ሲሆን፣ ስሙም ከ"ታላቁ አለቃ" ከሚለው ማዕረግ ጋር በመሆን መለኮታዊውን አዳኝ ያመለክታል። ክርስቶስ ስለ ሕዝባችን ልጆች በእነርሱ ፋንታ መስዋዕት ሆኖ ቆመ፤ ለእነርሱ እርግማንን ተሸከመ፣ ከእነርሱም ላይ ለማንሳት። በመሆኑም በጸጋው ዙፋን በእነርሱ ፈንታ እየለመነላቸው ይቆማል።

ከክርስቶስ ተቃዋሚ ጥፋት በኋላም፣ ጌታ ኢየሱስ በመጨረሻው ዘመን በምድር ላይ ይቆማል፤ እርሱም የሕዝቡን ሁሉ ሙሉ ቤዛነት ለማስፈጸም ይታያል። እግዚአብሔር ከስደት ነጻ ማውጣት ሲያደርግላቸው፣ እንደ ሙታን ከሞት መነሣት ነው። ወንጌሉ ሲሰበክ ደግሞ፣ በአፈር ውስጥ የተኙ ብዙዎች፣ አይሁድም ሆኑ አሕዛብ፣ በእርሱ ከጣዖት አምልኮአቸውና ከአይሁድ እምነታቸው ይነቃሉ። በመጨረሻም በአፈር ውስጥ የተኙት ብዙኃን ይነሳሉ፤ ብዙዎች ለሕይወት ይነሣሉ፣ ብዙዎችም ለውርደት።

ለወደፊቱ ሕይወት ለሁሉም ቅዱሳን፣ ለነፍሳቸውና ለዘለዓለም ሕይወታቸው ጥበበኛ ለሆኑት ሁሉ የተጠበቀ ክብር አለ። ብዙዎችን ወደ ጽድቅ የሚመልሱ፣ ኃጢአተኞችንም ከስሕተት መንገዳቸው የሚመልሱ፣ ነፍሳቸውንም ከሞት እንዲድኑ የሚያግዙ (ያዕቆብ 5:20)፣ ወደ ሰማይ እንዲደርሱ የረዷቸው ሰዎች ክብር ይካፈላሉ፣ ይህም የራሳቸውን ክብር ይጨምራል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV “At that time Michael, the great prince who protects your people, will arise. There will be a time of distress such as … English BCV “በቲ ዘመን እቱይ፥ እቲ ምእንቲ ደቂ ህዝብኻ እስራኤል ዝቐውም፥ ዓብዪ ሓለቓ ሚካኤል፥ ክትስእ እዩ። ሽዑ መንግስቲ ኻብ ዝተመስረተ ጊዜ ጀሚሩ፥ ክሳዕ እቲ ዘመን እቱይ ተርእዩ ዘይፍለጥ፥ ዓ… ትግርኛ GAZBIB Yommus inni anatti dubbachaa ture,“Yeroo sanatti Mikaa'el ergamaa inni guddichi ijoollee saba keef dhaabatu in ka'a; ye… Afaan Oromoo BCV GIZ ወውእተ አሚረ ይትነሣእ ሚካኤል መልአክ ዓቢይ ዘይትቃወም ለደቂቀ ሕዝብከ ወይከውን ዐቢየ ሕማመ እምኔሁ ወምንዳቤ ዘኢኮነ ከማሁ እምአመ ተፈጥረ አሕዛብ ዲበ ምድር እስከ ውእቱ አሚር፤ ወይድኅ… giz GAZGAZ Yommus inni anatti dubbachaa ture,“Yeroo sanatti Mikaa'el ergamaa inni guddichi ijoollee saba keef dhaabatu in ka'a; ye… Afaan Oromoo BCV aksum “በቲ ዘመን እቱይ፥ እቲ ምእንቲ ደቂ ህዝብኻ እስራኤል ዝቐውም፥ ዓብዪ ሓለቓ ሚካኤል፥ ክትስእ እዩ። ሽዑ መንግስቲ ኻብ ዝተመስረተ ጊዜ ጀሚሩ፥ ክሳዕ እቲ ዘመን እቱይ ተርእዩ ዘይፍለጥ፥ ዓ… ትግርኛ AMHNIV “በዚያን ዘመን ስለ ሕዝብህ የሚቈመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል። መንግሥታት ከተመሠረቱበት ጊዜ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ የመከራ ጊዜ ይሆናል። ነገር ግን በዚያ… አማርኛ SWAHSUV Wakati huo Mikaeli atasimama, jemadari mkuu, asimamaye upande wa wana wa watu wako; na kutakuwa na wakati wa taabu, mfa… Kiswahili