ትንቢተ አሞጽ 4

AMHNIVአማርኛ13 ጥቅሶች3:08 አዳምጥ
አዳምጥ 3:08 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እናንተ በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ የባሳን ላሞች፣ ድኾችን የምትጨቁኑና ችግረኞችን የምታስጨንቁ፣ ባሎቻችሁንም፣ “መጠጥ አቅርቡልን” የምትሉ ሴቶች ይህን ቃል ስሙ፣

2ጌታ እግዚአብሔር በቅድስናው እንዲህ ሲል ምሎአል፤ “እነሆ፤ በመንጠቆ ተይዛችሁ የምትወሰዱበት ትሩፋናችሁ እንኳ በዓሣ መንጠቆ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል።

3እያንዳንዳችሁ በቅጥሩ በተነደለው መሽሎኪያ ወደ ሬማንም ትጣላላችሁ፤” ይላል እግዚአብሔር።

4“ወደ ቤቴል ሂዱና ኀጢአትን ሥሩ፤ ወደ ጌልገላም ሂዱና ኀጢአትን አብዙ፤ በየማለዳው መሥዋዕቶቻችሁን፣ በየሦስቱ ዓመት ዐሥራታችሁን አቅርቡ።

5እርሾ ያለበትን እንጀራ የምሥጋና መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ፤ በፈቃዳችሁም በምታቀርቡት ቊርባን ተመኩ፤ እናንት እስራኤላውያን በእነርሱም ተኵራሩ፤ ማድረግ የምትወዱት ይህን ነውና፤” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

6በየከተማው ሆዳችሁን ባዶ አደረግሁት፤ በየመንደሩም የምትበሉትን አሳጣኋችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም” ይላል እግዚአብሔር።

7“መከር ሊደርስ ሦስት ወር ሲቀረውም፣ ዝናብ ከለከልኋችሁ፤ በአንዱ ከተማ ላይ አዘነብሁ፤ በሌላው ላይ ግን እንዳይዘንብ አደረግሁ፤ አንዱ ዕርሻ ሲዘንብለት፣ ሌላው ዝናብ አጥቶ ደረቀ።

8ሰዎች ውሃ ፍለጋ ከከተማ ወደ ከተማ ባዘኑ፣ ይሁን እንጂ ጠጥተው አልረኩም፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤” ይላል እግዚአብሔር።

9“የአትክልትና የወይን ቦታዎቻችሁን ብዙ ጊዜ መታሁ፤ በዋግና በአረማሞም አጠፋኋቸው፤ አንበጦችም የበለስና የወይራ ዛፎቻችሁን በሉ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤” ይላል እግዚአብሔር።

10“በግብፅ ላይ እንዳደረግሁት፣ መቅሠፍትን ላክሁባችሁ፤ ከተማረኩት ፈረሶቻችሁ ጋር፣ ጐልማሶቻችሁን በሰይፍ ገደልሁ፤ የሰፈራችሁ ግማት አፍንጫችሁ እንዲገባ አደረግሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም” ይላል እግዚአብሔር።

11“ሰዶምንና ገሞራን እንደ ገለበጥኋቸው፣ አንዳንዶቻችሁን ገለበጥሁ፤ ከእሳት እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤” ይላል እግዚአብሔር።

12“ስለዚህ እስራኤል ሆይ፤ እንደዚህ አደርግብሃለሁ፤ እንደዚህም ስለማደርግብህ፣ እስራኤል ሆይ፤ አምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ።”

13ተራሮችን የሚሠራ፣ ነፋስን የሚፈጥር፣ ሐሳቡንም ለሰው የሚገልጥ፣ ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፣ የምድርንም ከፍታዎች የሚረግጥ፣ ስሙ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው።

ማብራሪያ

ቍጥር ፬፡፩-፭፦ በግፍ የተገኘው ነገር ብዙውን ጊዜ ለሥጋ የሚያስፈልገውን ለማሟላትና የሥጋን ምኞት ለመፈጸም ይውላል። በጭቆና የተገኘው ነገር በእርካታ ሊደሰቱበት አይችልም። ከቅዱሳት መጻሕፍት ውጪ በሆኑ ሥርዓቶችና ተግባራት ላይ ያላቸው መተማመን ውሸትን እንደሚያምኑ ብቻ የሚያረጋግጥባቸው ሰዎች ምንኛ የሚያሳዝኑ ናቸው! እምነታችን፣ ተስፋችንና አምልኳችን በእግዚአብሔር ቃል የተደገፉ መሆናቸውን እናረጋግጥ።

፬፡፮-፲፫ የሥጋዊ ልቦችን ሞኝነት ተመልከቱ፤ የሚያረካቸውን ነገር ፍለጋ ከአንዱ ፍጥረት ወደ ሌላው ይንከራተታሉ፣ የማያረካቸውን ነገር ደግሞ ይለ…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ፥ ድሆችንም የምትበድሉ፥ ችጋረኞችንም የምታሰጨንቁ፥ ጌቶቻቸውንም፦ “አምጡ እንጠጣ፡” የምትሉ እናንተ የባሳን ላሞች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ። አማርኛ ENGNIV Hear this word, you cows of Bashan on Mount Samaria, you women who oppress the poor and crush the needy and say to your… English BCV ኣትን ኣብ እምባ ሰማርያ እትነብራ፥ ንድኻታት እተጥቅዓ፥ ሽግረኛታትውን እተጨንቓ፥ ንጐይተቶም ድማ “ኣምፅኡ ንስተ” እትብላ፥ ኣላሕም ባሳን እዝ ቃል እዙይ ስምዓ። ትግርኛ GAZBIB Isin yaa giiftolii, warra akka saawwan biyya Baashaan tulluu Samaariyaa irratti gabbattanii, warra dadhaboo immoo cunqu… Afaan Oromoo BCV GIZ ስምዑ ዘንተ ነገረ እጐልተ ባሳን እለ ውስተ አድባረ ሰማርያ እለ ይትኤገላ ነዳየ ወየሀይዳ ምስኪናነ እለ ይብላሆሙ ለአጋእስቲሆሙ ሀቡነ ንስተይ። giz GAZGAZ Isin yaa giiftolii, warra akka saawwan biyya Baashaan tulluu Samaariyaa irratti gabbattanii, warra dadhaboo immoo cunqu… Afaan Oromoo BCV aksum ኣትን ኣብ እምባ ሰማርያ እትነብራ፥ ንድኻታት እተጥቅዓ፥ ሽግረኛታትውን እተጨንቓ፥ ንጐይተቶም ድማ “ኣምፅኡ ንስተ” እትብላ፥ ኣላሕም ባሳን እዝ ቃል እዙይ ስምዓ። ትግርኛ SWAHSUV Lisikieni neno hili, enyi ng'ombe wa Bashani, mnaokaa juu ya mlima wa Samaria, mnaowaonea maskini, na kuwaponda wahitaj… Kiswahili