2ኛ ጴጥሮስ 2

AMHEVGአማርኛ20 ጥቅሶች4:05 አዳምጥ
አዳምጥ 4:05 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤

2ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሉአቸዋል በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል።

3ገንዘብንም በመመኘት በተፈጠረ ነገር ይረቡባችኋል፤ ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይም ጥፋታቸውም አያንቀላፋም።

4እግዚአብሔር ኃጢአትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው፥

5ለቀደመውም ዓለም ሳይራራ ከሌሎች ሰባት ጋር ጽድቅን የሚሰብከውን ኖኅን አድኖ በኃጢአተኞች ዓለም ላይ የጥፋትን ውኃ ካወረደ፥

6ኃጢአትንም ያደርጉ ዘንድ ላሉት ምሳሌ አድርጎ ከተማዎችን ሰዶምንና ገሞራን አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎና ገልብጦ ከፈረደባቸው፥

7ጻድቅ ሎጥም በመካከላቸው ሲኖር እያየና እየሰማ ዕለት ዕለት በዓመፀኛ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን አስጨንቆ ነበርና በዓመፀኞች ሴሰኛ ኑሮ የተገፋውን ያን ጻድቅ ካዳነ፥

9ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንዲያድን፥ በደለኞችንም ይልቁንም በርኵስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን ጌትነትንም የሚንቁትን እየቀጣቸው ለፍርድ ቀን እንዴት እንዲጠብቅ ያውቃል። ደፋሮችና ኵሩዎች ሆነው ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይንቀጠቀጡም፤

11ዳሩ ግን መላእክት በኃይልና በብርታት ከእነርሱ ይልቅ ምንም ቢበልጡ በጌታ ፊት በእነርሱ ላይ የስድብን ፍርድ አያመጡም።

12እነዚህ ግን ለመጠመድና ለመጥፋት በፍጥረታቸው እንደ ተወለዱ አእምሮ እንደ ሌላቸው እንስሶች ሆነው፥ በማያውቁት ነገር እየተሳደቡ በጥፋታቸው ይጠፋሉ፤

13የዓመፃቸውን ደመወዝ ይቀበላሉ። በቀን ሲዘፍኑ እንደ ተድላ ይቆጥሩታል፤ ነውረኞችና ርኵሳን ሆነው ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣ ይዘፍናሉ፤

14ምንዝር የሞላባቸው ኃጢአትንም የማይተዉ ዓይኖች አሉአቸው፤ የማይጸኑትን ነፍሳት ያታልላሉ፤ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ናቸው።

15ቅንን መንገድ ትተው ተሳሳቱ፤ የባሶርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከተሉ፤ እርሱ የዓመፃን ደመወዝ ወደደ፥

16ነገር ግን ስለ መተላለፉ ተዘለፈ፤ ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነቢዩን እብድነት አገደ።

17ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው እነዚህ ውኃ የሌለባቸው ምንጮች በዐውሎ ነፋስም የተነዱ ደመናዎች ናቸው።

18ከንቱና ከመጠን ይልቅ ታላቅ የሆነውን ቃል ይናገራሉና፥ በስሕተትም ከሚኖሩት አሁን የሚያመልጡትን በሥጋ ሴሰኛ ምኞት ያታልላሉ።

19ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው፦ “አርነት ትወጣላችሁ፡” እያሉ ተስፋ ይሰጡአቸዋል፤ ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ ተገዝቶ ባሪያ ነውና።

20በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ ዳግመኛ በእርስዋ ተጠላልፈው የተሸነፉ ቢሆኑ፥ ከፊተኛው ኑሮአቸው ይልቅ የኋለኛው የባሰ ሆኖባቸዋል።

21አውቀዋት ከተሰጣቸው ከቅድስት ትእዛዝ ከሚመለሱ የጽድቅን መንገድ ባላወቋት በተሻላቸው ነበርና።

22ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፥ ደግሞ፦ “የታጠበች እርያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች፡” እንደሚባል እውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋል።

ማብራሪያ

2:1-9 የስህተት መንገድ ጎጂ መንገድ ቢሆንም፣ ብዙዎች ሁልጊዜ በእርሱ ለመሄድ ዝግጁ ናቸው። በእርሱ የተጠራንበትን ቅዱስ ስም ጠላት እንዳያቃልል ወይም እርሱም መንገድ፣ እውነትና ሕይወት የሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ያለው የድነት መንገድን እንዳያነውር ዕድል እንዳንሰጥ ጥንቃቄ እናድርግ። እነዚህ አታላዮች ሐሰተኛ ቃላትን ተጠቅመዋል፤ የተከታዮቻቸውን ልብም አሳቱ። እንደነዚህ ያሉት አስቀድሞ ተፈርዶባቸዋል፤ የእግዚአብሔርም ቁጣ በእነርሱ ላይ ይኖራል።

እግዚአብሔር የሚሠራበት የተለመደው መንገድ በምሳሌዎች ታይቷል። መላእክት ባለመታዘዛቸው የተነሣ ከክብራቸውና ከግርማቸው ሁሉ ተጣሉ፤ ፍጥረታት በሰማይ እንኳን ኃጢአት ቢሠሩ፣ በሲኦል ሊሰቃዩ ይገባቸዋል። ኃጢአት የጨለማ ሥራ ነው፤ ጨለማም የኃጢአት ደሞዝ ነው። እግዚአብሔር ከጥንቱ ዓለም ጋር እንዴት እንደተያያዘ ተመልከቱ። የኃጢአተኞች ቁጥር ከጥራታቸው በላይ ሞገስ አያስገኝም። ኃጢአቱ ዓለም አቀፋዊ ከሆነ፣ ቅጣቱም እንዲሁ ወደ ሁሉም ይደርሳል። ለም መሬት ባለው ሕዝብ ኃጢአት በዛብን፣ እግዚአብሔር በአንድ ጊዜ ለም መሬትን ወደ በረሃነት፣ በውኃ የረሰረሰችውንም አገር ወደ አመድ ሊለውጥ ይችላል። ምንም ዕቅዶች ወይም ፖለቲካዊ እርምጃዎች ከኃጢአተኛ ሕዝብ ላይ ፍርድን ሊያስወግዱ አይችሉም። እሳትንና ውኃን ሕዝቡን እንዳይጎዱ የሚጠብቅ እርሱ፣ ኢሳ 43:2፣ ጠላቶቹን በእነዚህ በማናቸውም ሊያጠፋ ይችላል፤ እነርሱ በፍጹም ደኅንነት የላቸውም። እግዚአብሔር በኃጢአተኞች ላይ ጥፋትን ሲልክ፣ ለጻድቃን መዳንን ያዝዛል። በመጥፎ ጓደኝነት ወይ ጥፋተኝነትን ወይም ሐዘንን ከመቀበል ውጭ አንሆንም። የሌሎች ኃጢአት ለኛ መከራ ይሁንልን።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV But there were also false prophets among the people, just as there will be false teachers among you. They will secretly… English BCV ግና ሓሰውቲ ነቢያት ኣብ ማእኸል ህዝቢ እግዚኣብሄር ተሲኦም ከም ዝነበሩ፥ ኣብ ማእኸልኩምውን፥ ሓሰውቲ መምህራን ክትስኡ እዮም። ንሳቶም ብሕቡእ፥ ጥፍኣት ዘስዕብ መናፍቕነት ከምፅኡ እዮም። … ትግርኛ GAZBIB Akkuma raajonni sobduun saba sana gidduu turan, akkasuma barsiisonni sobduun isin gidduu in jiraatu. Isaan warra utuu i… Afaan Oromoo BCV GIZ ወቦ ባሕቱ ሐሳውያነ ነቢያት ማእከለ ሕዝብ ከመ እለ ሀለዉ ማእከሌክሙ ወውስቴትክሙ እለ ሐሰተ ይሜህሩ ወእለ ካሕደ ያበውኡ ለሕርትምና ወይክሕድዎ ለእግዚኦሙ ዘተሣየጦሙ በደሙ ወያመጽእዎ ላዕሌ… giz GAZGAZ Akkuma raajonni sobduun saba sana gidduu turan, akkasuma barsiisonni sobduun isin gidduu in jiraatu. Isaan warra utuu i… Afaan Oromoo BCV aksum ግና ሓሰውቲ ነቢያት ኣብ ማእኸል ህዝቢ እግዚኣብሄር ተሲኦም ከም ዝነበሩ፥ ኣብ ማእኸልኩምውን፥ ሓሰውቲ መምህራን ክትስኡ እዮም። ንሳቶም ብሕቡእ፥ ጥፍኣት ዘስዕብ መናፍቕነት ከምፅኡ እዮም። … ትግርኛ AMHNIV ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት በሕዝቡ መካከል እንደ ነበሩ እንዲሁም በእናንተ መካከል ሐሰተኞች መምህራን ይነሣሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው ጥፋት የሚያስከትል የስሕተት ትምህርት … አማርኛ SWAHSUV Lakini kuliondokea manabii wa uongo katika wale watu, kama vile kwenu kutakavyokuwako waalimu wa uongo, watakaoingiza k… Kiswahili