2ኛ ጴጥሮስ 2

AMHNIVአማርኛ22 ጥቅሶች4:33 አዳምጥ
አዳምጥ 4:33 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት በሕዝቡ መካከል እንደ ነበሩ እንዲሁም በእናንተ መካከል ሐሰተኞች መምህራን ይነሣሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው ጥፋት የሚያስከትል የስሕተት ትምህርት በስውር ያስገባሉ፤ በዚህም በራሳቸው ላይ ድንገተኛ ጥፋት ያመጣሉ።

2ብዙዎች አስነዋሪ ድርጊቶቻቸውን ይከተላሉ፤ በእነርሱም ምክንያት የእውነት መንገድ ይሰደባል።

3እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን እየተስገበገቡ በፈጠራ ታሪካቸው ይበዘብዙዋችኋል። ፍርዳቸው ከጥንት ጀምሮ ዝግጁ ነው፤ መጥፊያቸውም አያንቀላፋም።

4እግዚአብሔር ኀጢአት የሠሩትን መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ከጣላቸውና በጨለማ ጒድጓድ ውስጥ ለፍርድ ካስቀመጣቸው፣

5የጽድቅ ሰባኪ የነበረውንም ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር አድኖ ለቀድሞው ዓለም ሳይራራ በኀጢአተኞች ላይ የጥፋት ውሃ ካመጣ፣

6ደግሞም ኀጢአት ለሚያደርጉ ሁሉ ምሳሌ እንዲሆኑ የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ዐመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎ ከፈረደባቸው፣

7ጻድቅ የሆነውንና በዐመፀኞች ሴሰኛ ድርጊት እየተሣቀቀ የኖረውን ሎጥን ካዳነ፣

8ያ ጻድቅ ሰው በእነርሱ መካከል ሲኖር በሚያየውና በሚሰማው ነገር ነፍሱ ዕለት ዕለት በዐመፀኛ ድርጊታቸው ብትጨነቅም፣

9ጌታ፣ በእውነት እያመለኩት የሚኖሩትን ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸውና ዐመፀኞችን እየቀጣ ለፍርድ ቀን እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል።

10በተለይም በርኩስ ምኞት የሥጋ ፍላጎታቸውን የሚከተሉትንና ሥልጣንን የሚንቁትን ለፍርድ ጠብቆ ያቈያቸዋል። እነዚህ ሰዎች ደፋሮችና እብሪተኞች ስለሆኑ ሰማያውያንን ፍጡራን ሲሳደቡ አይፈሩም፤

11ነገር ግን መላእክት ከእነርሱ ይልቅ ብርቱና ኀያል ሆነው ሳሉ፣ በጌታ ፊት በእነርሱ ላይ የስድብ ቃል አይሰነዝሩም።

12እነዚህ ሰዎች ግን ምንም በማያውቁት ነገር እየገቡ ይሳደባሉ፤ እነርሱም ለመያዝና ለመገደል እንደ ተወለዱ፣ በስሜታቸው ብቻ እንደሚመሩና ልቦናም እንደሌላቸው አራዊት ናቸው፤ የሚጠፉትም እንደ እንስሳት ነው።

13ለዐመፃቸው የሚገባውን የዐመፅ ዋጋ ይቀበላሉ፤ በጠራራ ፀሓይ ሲፈነጥዙ እንደ ደስታ ይቈጥሩታል፤ በግብዣ ላይ ሳሉ ነውረኞችና ርኩሶች ሆነው ከእናንተም ጋር በፍቅር ግብዣ ላይ ይቀመጣሉ፤

14ዐይናቸው ቅንዝር የተሞላ በመሆኑ ኀጢአትን ከመሥራት አይቈጠቡም፤ ጽኑ ያልሆኑትን ነፍሳት ያስታሉ፤ ስስትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ናቸው!

15ቀናውን መንገድ ትተው፣ የዐመፅን ደመወዝ የወደደውን የቢዖርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከትለው ስተዋል፤

16እርሱ ግን ስለ መተላለፉ ተገሥጾአል፤ መናገር የማይችል አህያ በሰው ቋንቋ ተናግሮ የነቢዩን እብደት ገታ።

17እነዚህ ሰዎች የደረቁ ምንጮችና በዐውሎ ነፋስ የሚነዱ ደመናዎች ናቸው፤ የሚጠብቃቸውም ድቅድቅ ጨለማ ነው፤

18ከንቱ ቃል እየደረደሩ በስሕተት ከሚኖሩት መካከል አምልጠው የመጡትን ሰዎች በሴሰኛ ሥጋዊ ምኞት በማባበል ያታልላሉና።

19እነርሱ ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው ሳሉ፣ ሌሎችን ነጻ ትወጣላችሁ እያሉ ተስፋ ይሰጧቸዋል፤ ሰው ለተገዛለት ለዚያ ነገር ባሪያ ነውና።

20ጌታችንንና አዳኛችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ እንደ ገና ተጠላልፈው ቢሸነፉ ከመጀመሪያው ይልቅ የኋለኛው ሁኔታቸው የከፋ ይሆንባቸዋል።

21የጽድቅን መንገድ ካወቁ በኋላ ከተሰጣቸው ቅዱስ ትእዛዝ ወደ ኋላ ከሚመለሱ፣ ቀድሞውኑ የጽድቅን መንገድ ባላወቋት ይሻላቸው ነበር።

22“ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል” እንዲሁም “ዐሣማ ቢታጠብም ተመልሶ በጭቃ ላይ ይንከባለላል” የሚለው ምሳሌ እውን ይሆንባቸዋል።

ማብራሪያ

2:1-9 የስህተት መንገድ ጎጂ መንገድ ቢሆንም፣ ብዙዎች ሁልጊዜ በእርሱ ለመሄድ ዝግጁ ናቸው። በእርሱ የተጠራንበትን ቅዱስ ስም ጠላት እንዳያቃልል ወይም እርሱም መንገድ፣ እውነትና ሕይወት የሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ያለው የድነት መንገድን እንዳያነውር ዕድል እንዳንሰጥ ጥንቃቄ እናድርግ። እነዚህ አታላዮች ሐሰተኛ ቃላትን ተጠቅመዋል፤ የተከታዮቻቸውን ልብም አሳቱ። እንደነዚህ ያሉት አስቀድሞ ተፈርዶባቸዋል፤ የእግዚአብሔርም ቁጣ በእነርሱ ላይ ይኖራል።

እግዚአብሔር የሚሠራበት የተለመደው መንገድ በምሳሌዎች ታይቷል። መላእክት ባለመታዘዛቸው የተነሣ ከክብራቸውና ከግርማቸው ሁሉ ተጣሉ፤ ፍጥረታት በሰማይ እንኳን ኃጢአት ቢሠሩ፣ በሲኦል ሊሰቃዩ ይገባቸዋል። ኃጢአት የጨለማ ሥራ ነው፤ ጨለማም የኃጢአት ደሞዝ ነው። እግዚአብሔር ከጥንቱ ዓለም ጋር እንዴት እንደተያያዘ ተመልከቱ። የኃጢአተኞች ቁጥር ከጥራታቸው በላይ ሞገስ አያስገኝም። ኃጢአቱ ዓለም አቀፋዊ ከሆነ፣ ቅጣቱም እንዲሁ ወደ ሁሉም ይደርሳል። ለም መሬት ባለው ሕዝብ ኃጢአት በዛብን፣ እግዚአብሔር በአንድ ጊዜ ለም መሬትን ወደ በረሃነት፣ በውኃ የረሰረሰችውንም አገር ወደ አመድ ሊለውጥ ይችላል። ምንም ዕቅዶች ወይም ፖለቲካዊ እርምጃዎች ከኃጢአተኛ ሕዝብ ላይ ፍርድን ሊያስወግዱ አይችሉም። እሳትንና ውኃን ሕዝቡን እንዳይጎዱ የሚጠብቅ እርሱ፣ ኢሳ 43:2፣ ጠላቶቹን በእነዚህ በማናቸውም ሊያጠፋ ይችላል፤ እነርሱ በፍጹም ደኅንነት የላቸውም። እግዚአብሔር በኃጢአተኞች ላይ ጥፋትን ሲልክ፣ ለጻድቃን መዳንን ያዝዛል። በመጥፎ ጓደኝነት ወይ ጥፋተኝነትን ወይም ሐዘንን ከመቀበል ውጭ አንሆንም። የሌሎች ኃጢአት ለኛ መከራ ይሁንልን።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እ… አማርኛ ENGNIV But there were also false prophets among the people, just as there will be false teachers among you. They will secretly… English BCV ግና ሓሰውቲ ነቢያት ኣብ ማእኸል ህዝቢ እግዚኣብሄር ተሲኦም ከም ዝነበሩ፥ ኣብ ማእኸልኩምውን፥ ሓሰውቲ መምህራን ክትስኡ እዮም። ንሳቶም ብሕቡእ፥ ጥፍኣት ዘስዕብ መናፍቕነት ከምፅኡ እዮም። … ትግርኛ GAZBIB Akkuma raajonni sobduun saba sana gidduu turan, akkasuma barsiisonni sobduun isin gidduu in jiraatu. Isaan warra utuu i… Afaan Oromoo BCV GIZ ወቦ ባሕቱ ሐሳውያነ ነቢያት ማእከለ ሕዝብ ከመ እለ ሀለዉ ማእከሌክሙ ወውስቴትክሙ እለ ሐሰተ ይሜህሩ ወእለ ካሕደ ያበውኡ ለሕርትምና ወይክሕድዎ ለእግዚኦሙ ዘተሣየጦሙ በደሙ ወያመጽእዎ ላዕሌ… giz GAZGAZ Akkuma raajonni sobduun saba sana gidduu turan, akkasuma barsiisonni sobduun isin gidduu in jiraatu. Isaan warra utuu i… Afaan Oromoo BCV aksum ግና ሓሰውቲ ነቢያት ኣብ ማእኸል ህዝቢ እግዚኣብሄር ተሲኦም ከም ዝነበሩ፥ ኣብ ማእኸልኩምውን፥ ሓሰውቲ መምህራን ክትስኡ እዮም። ንሳቶም ብሕቡእ፥ ጥፍኣት ዘስዕብ መናፍቕነት ከምፅኡ እዮም። … ትግርኛ SWAHSUV Lakini kuliondokea manabii wa uongo katika wale watu, kama vile kwenu kutakavyokuwako waalimu wa uongo, watakaoingiza k… Kiswahili