2ኛ ጴጥሮስ 1

AMHNIVአማርኛ21 ጥቅሶች3:46 አዳምጥ
አዳምጥ 3:46 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ ስምዖን ጴጥሮስ፤ በአምላካችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ በኩል እንደ ተቀበልነው ዐይነት ክቡር እምነት ለተቀበሉት፤

2እግዚአብሔርንና ጌታችን ኢየሱስን በማወቅ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።

3በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን እርሱን በማወቅ ለሕይወትና ለእውነተኛ መንፈሳዊነት የሚያስፈልገንን ሁሉ የመለኮቱ ኀይል ሰጥቶናል።

4ከክፉ ምኞት የተነሣ በዓለም ካለው ምግባረ ብልሹ ሕይወት አምልጣችሁ ከመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች እንድትሆኑ በእነዚህ ነገሮች አማካይነት እጅግ ታላቅና ክቡር የሆነውን ተስፋ ሰጥቶናል።

5በዚህም ምክንያት በሙሉ ትጋት በእምነታችሁ ላይ በጎነትን ለመጨመር ጣሩ፤ በበጎነት ላይ ዕውቀትን፣

6በዕውቀት ላይ ራስን መግዛት፣ ራስን በመግዛት ላይ መጽናትን፣ በመጽናት ላይ እውነተኛ መንፈሳዊነትን፤

7በእውነተኛ መንፈሳዊነት ላይ ወንድማዊ መተሳሰብን፣ በወንድማዊ መተሳሰብ ላይ ፍቅርን ጨምሩ።

8እነዚህ ባሕርያት ተትረፍርፈው ቢኖሯችሁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ ዳተኞችና ፍሬ ቢሶች ከመሆን ይጠብቋችኋል።

9እነዚህ ባሕርያት የሌሉት ግን የሩቁን የማያይ ወይም ዕውር ነው፤ ከቀድሞው ኀጢአቱ መንጻቱንም ረስቶአል።

10ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፤ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ለማጽናት ከፊት ይልቅ ትጉ፤ ምክንያቱም እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም፤

11በዚህም ወደ ጌታችንና አዳኛችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋል።

12ስለዚህ ምንም እንኳ እነዚህን ነገሮች ብታውቋቸውና በያዛችሁት እውነት ብትጸኑም፣ ስለ እነዚህ ነገሮች እናንተን ዘወትር ከማሳሰብ ቸል አልልም።

13በዚህ ምድራዊ ድንኳን ውስጥ እስካለሁ ድረስ እናንተን መጐትጐት ትክክል ሆኖ ይታየኛል፤

14ምክንያቱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ገለጠልኝ ይህን ምድራዊ ድንኳን ቶሎ ጥዬ እንደምሄድ ዐውቃለሁ፤

15እነዚህን ነገሮች ከተለየኋችሁም በኋላ ዘወትር ታስቡ ዘንድ እተጋለሁ።

16ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኀይልና ስለ መምጣቱ የነገርናችሁ እኮ የእርሱን ግርማ በዐይናችን አይተን እንጂ፣ በሰዎች ጥበብ የተፈጠረውን ተረት ተከትለን አይደለም፤

17ምክንያቱም ከግርማዊው ክብር “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” የሚል ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርና ሞገስ ተቀብሎአል፤

18እኛም ከእርሱ ጋር በቅዱሱ ተራራ ላይ በነበርንበት ጊዜ ይህ ድምፅ ከሰማይ ሲመጣ ሰምተናል።

19እንግዲያስ ትንቢታዊው ቃል ይበልጥ ተረጋግጦልናል፤ ሌሊቱ እስኪነጋና የንጋት ኮከብ በልባችሁ እስኪበራ ድረስ፣ በጨለማ ስፍራ ለሚበራ መብራት ጥንቃቄ እንደሚደረግ እናንተም ለዚህ ቃል ብትጠነቀቁ መልካም ታደርጋላችሁ።

20ከሁሉ አስቀድሞ ይህን ልታውቁ ይገባችኋል፤ በመጽሐፍ ያለው የትንቢት ቃል ሁሉ ማንም ሰው በገዛ ራሱ መንገድ የሚተረጒመው አይደለም፤

21ምክንያቱም ትንቢት ከእግዚአብሔር የተላኩ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ተናገሩት እንጂ ከቶ በሰው ፈቃድ የመጣ አይደለም።

ማብራሪያ

1:1-11 እምነት ደካማውን ምእመን ከክርስቶስ ጋር ያገናኛል፣ ጠንካራውን ምእመንም እንደሚያገናኘው ሁሉ፤ የአንዱንም ልብ በእርግጥ እንደሚያነጻው ሁሉ የሌላውንም ያነጻል። እያንዳንዱ ቅን ምእመንም በእምነቱ በእግዚአብሔር ፊት ይጸድቃል። እምነት እግዚአብሔርን መምሰልን ይሰራል። በነፍስ ውስጥ ያለ ሌላ ጸጋ ሊያደርጋቸው የማይችላቸውን ውጤቶችም ያፈራል። በክርስቶስ ውስጥ ፍጹም ሙላት ሁሉ ይኖራል። ስለሆነም ይቅርታ፣ ሰላም፣ ጸጋ፣ እውቀትና አዳዲስ መርሆዎች በመንፈስ ቅዱስ በኩል ይሰጣሉ። መለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች ለሆኑ ሰዎች የተሰጡት ተስፋዎች በአእምሮአችን መንፈስ በእውነት ታድሰን እንደሆነ እንድንጠይቅ ያደርጉናል። እነዚህን ተስፋዎች ሁሉ ለመንፈስ ቅዱስ ለሚለውጥና ለሚያነጻ ጸጋ ወደ ጸሎት እንለውጣቸው። ምእመኑም በበጎነቱ ላይ እውቀትን፣ የእግዚአብሔርን ሙሉ እውነትና ፈቃድ ማወቅን በማሳደግ፣ ሊጨምር ይገባል። በእውቀት ላይ ራስን መግዛትን፣ ማለትም በዓለማዊ ነገሮች ሁሉ ልኩን ማወቅን፣ መደመር አለብን፤ በራስ መግዛት ላይም ትዕግሥትን፣ ወይም ለእግዚአብሔር ፈቃድ በደስታ መገዛትን፣ መደመር አለብን። መከራ ትዕግሥትን ታስገኛለች፤ በዚህም ሁሉንም መከራዎችና መስቀሎች በጸጥታና በመገዛት እንሸከማለን። በትዕግሥት ላይ እግዚአብሔርን መምሰልን መደመር አለብን። ይህም በእውነተኛው የእግዚአብሔር አምላኪ ዘንድ የሚገኙትን ቅዱስ ስሜቶችንና ባሕርያትን ያጠቃልላል፤ ለአንድ አባት ልጆች፣ ለአንድ ጌታ ባሪያዎች፣ ለአንድ ቤተሰብ አባላት፣ ወደ አንድ አገር ተጓዦች፣ የአንድ ውርስ ወራሾች ለሆኑት፣ ለሁሉም ባልንጀራ ክርስቲያኖች በለስላሳ ፍቅር ጭምር። ስለሆነም ክርስቲያኖች በመታመንና መልካምን በመስራት ጥሪያቸውንና ምርጫቸውን እንዲያረጋግጡ ይትጉ። እንዲህ በጥንቃቄ መትጋትም የእግዚአብሔር ጸጋና ምሕረት እነርሱን ሙሉ በሙሉ እንዳይወድቁ የሚደግፍ ጠንካራ ማረጋገጫ ነው። በሃይማኖት ስራ በትጋት የሚሠሩት ክርስቶስ በሚነግስበት ወደ ዘላለም መንግሥት የድል መግቢያ ይኖራቸዋል። እነርሱም ከእርሱ ጋር ለዘላለም ይነግሳሉ። ወደ ሰማይ መግቢያንም የምንጠብቀው ሁሉንም መልካም ሥራ በመሥራት ነው።

1:12-15 እያንዳንዱ የትምህርት ነፋስ እንዳያንቀጠቅጠን፣ በእውነት እምነት ውስጥ መጽናት አለብን።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ የሆነ ስምዖን ጴጥሮስ፥ በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ፤ አማርኛ ENGNIV Simon Peter, a servant and apostle of Jesus Christ, To those who through the righteousness of our God and Savior Jesus … English BCV ናይ ኢየሱስ ክርስቶስ ኣገልጋልን ሃዋርያን ካብ ዝኾነ ስምኦን ጴጥሮስ፥ ናብቶም ብናይ እግዚኣብሄርን፥ መድሓኒና ኢየሱስ ክርስቶስን ፅድቂ፥ ከማና ኽብርቲ እምነት ዝተቐበሉ፥ ትግርኛ GAZBIB Ani Simoon Phexros, Yesus Kristosiif hojjetaa, ergamaas ta'ee, warra karaa qajeelina Waaqayyo keenyaaf fayyisaa keenyaa… Afaan Oromoo BCV GIZ እምኀበ ስምዖን ኬፋ ገብሩ ወልኡኩ ለኢየሱስ ክርስቶስ ለእለ ነኀብር ክብረ በሃይማኖት እንተ ከፈለነ በጽድቁ ለአምላክነ ወፈራቂነ ኢየሱስ ክርስቶስ። giz GAZGAZ Ani Simoon Phexros, Yesus Kristosiif hojjetaa, ergamaas ta'ee, warra karaa qajeelina Waaqayyo keenyaaf fayyisaa keenyaa… Afaan Oromoo BCV aksum ናይ ኢየሱስ ክርስቶስ ኣገልጋልን ሃዋርያን ካብ ዝኾነ ስምኦን ጴጥሮስ፥ ናብቶም ብናይ እግዚኣብሄርን፥ መድሓኒና ኢየሱስ ክርስቶስን ፅድቂ፥ ከማና ኽብርቲ እምነት ዝተቐበሉ፥ ትግርኛ SWAHSUV Simoni Petro, mtumwa na mtume wa Yesu Kristo, kwa wale waliopata imani moja na sisi, yenye thamani, katika hali ya Mung… Kiswahili