2ኛ ጴጥሮስ 1

AMHEVGአማርኛ20 ጥቅሶች3:15 አዳምጥ
አዳምጥ 3:15 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ የሆነ ስምዖን ጴጥሮስ፥ በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ፤

2የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።

4ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን።

5ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥

6በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥

7እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ።

8እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤

9እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል።

10ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና።

11እንዲሁ ወደ ዘላለሙ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋልና።

12ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ምንም ብታውቁ በእናንተም ዘንድ ባለ እውነት ምንም ብትጸኑ፥ ስለ እነዚህ ዘወትር እንዳሳስባችሁ ቸል አልልም።

13ሁልጊዜም በዚህ ማደሪያ ሳለሁ በማሳሰቤ ላነቃችሁ የሚገባኝ ይመስለኛል።

14ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመለከተኝ ከዚህ ማደሪያዬ መለየቴ ፈጥኖ እንዲሆን አውቃለሁና።

15ከመውጣቴም በኋላ እነዚህን ነገሮች እንድታስቡ በየጊዜው ትችሉ ዘንድ እተጋለሁ።

16የእርሱን ግርማ አይተን እንጂ በብልሃት የተፈጠረውን ተረት ሳንከተል የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ኃይልና መምጣት አስታወቅናችሁ።

17ከገናናው ክብር፦ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፡” የሚል ያ ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ምስጋናን ተቀብሎአልና፤

18እኛም በቅዱሱ ተራራ ከእርሱ ጋር ሳለን ይህን ድምፅ ከሰማይ ሲወርድ ሰማን።

19ከእርሱም ይልቅ እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን፤ ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ።

20ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤

21ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።

ማብራሪያ

1:1-11 እምነት ደካማውን ምእመን ከክርስቶስ ጋር ያገናኛል፣ ጠንካራውን ምእመንም እንደሚያገናኘው ሁሉ፤ የአንዱንም ልብ በእርግጥ እንደሚያነጻው ሁሉ የሌላውንም ያነጻል። እያንዳንዱ ቅን ምእመንም በእምነቱ በእግዚአብሔር ፊት ይጸድቃል። እምነት እግዚአብሔርን መምሰልን ይሰራል። በነፍስ ውስጥ ያለ ሌላ ጸጋ ሊያደርጋቸው የማይችላቸውን ውጤቶችም ያፈራል። በክርስቶስ ውስጥ ፍጹም ሙላት ሁሉ ይኖራል። ስለሆነም ይቅርታ፣ ሰላም፣ ጸጋ፣ እውቀትና አዳዲስ መርሆዎች በመንፈስ ቅዱስ በኩል ይሰጣሉ። መለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች ለሆኑ ሰዎች የተሰጡት ተስፋዎች በአእምሮአችን መንፈስ በእውነት ታድሰን እንደሆነ እንድንጠይቅ ያደርጉናል። እነዚህን ተስፋዎች ሁሉ ለመንፈስ ቅዱስ ለሚለውጥና ለሚያነጻ ጸጋ ወደ ጸሎት እንለውጣቸው። ምእመኑም በበጎነቱ ላይ እውቀትን፣ የእግዚአብሔርን ሙሉ እውነትና ፈቃድ ማወቅን በማሳደግ፣ ሊጨምር ይገባል። በእውቀት ላይ ራስን መግዛትን፣ ማለትም በዓለማዊ ነገሮች ሁሉ ልኩን ማወቅን፣ መደመር አለብን፤ በራስ መግዛት ላይም ትዕግሥትን፣ ወይም ለእግዚአብሔር ፈቃድ በደስታ መገዛትን፣ መደመር አለብን። መከራ ትዕግሥትን ታስገኛለች፤ በዚህም ሁሉንም መከራዎችና መስቀሎች በጸጥታና በመገዛት እንሸከማለን። በትዕግሥት ላይ እግዚአብሔርን መምሰልን መደመር አለብን። ይህም በእውነተኛው የእግዚአብሔር አምላኪ ዘንድ የሚገኙትን ቅዱስ ስሜቶችንና ባሕርያትን ያጠቃልላል፤ ለአንድ አባት ልጆች፣ ለአንድ ጌታ ባሪያዎች፣ ለአንድ ቤተሰብ አባላት፣ ወደ አንድ አገር ተጓዦች፣ የአንድ ውርስ ወራሾች ለሆኑት፣ ለሁሉም ባልንጀራ ክርስቲያኖች በለስላሳ ፍቅር ጭምር። ስለሆነም ክርስቲያኖች በመታመንና መልካምን በመስራት ጥሪያቸውንና ምርጫቸውን እንዲያረጋግጡ ይትጉ። እንዲህ በጥንቃቄ መትጋትም የእግዚአብሔር ጸጋና ምሕረት እነርሱን ሙሉ በሙሉ እንዳይወድቁ የሚደግፍ ጠንካራ ማረጋገጫ ነው። በሃይማኖት ስራ በትጋት የሚሠሩት ክርስቶስ በሚነግስበት ወደ ዘላለም መንግሥት የድል መግቢያ ይኖራቸዋል። እነርሱም ከእርሱ ጋር ለዘላለም ይነግሳሉ። ወደ ሰማይ መግቢያንም የምንጠብቀው ሁሉንም መልካም ሥራ በመሥራት ነው።

1:12-15 እያንዳንዱ የትምህርት ነፋስ እንዳያንቀጠቅጠን፣ በእውነት እምነት ውስጥ መጽናት አለብን።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Simon Peter, a servant and apostle of Jesus Christ, To those who through the righteousness of our God and Savior Jesus … English BCV ናይ ኢየሱስ ክርስቶስ ኣገልጋልን ሃዋርያን ካብ ዝኾነ ስምኦን ጴጥሮስ፥ ናብቶም ብናይ እግዚኣብሄርን፥ መድሓኒና ኢየሱስ ክርስቶስን ፅድቂ፥ ከማና ኽብርቲ እምነት ዝተቐበሉ፥ ትግርኛ GAZBIB Ani Simoon Phexros, Yesus Kristosiif hojjetaa, ergamaas ta'ee, warra karaa qajeelina Waaqayyo keenyaaf fayyisaa keenyaa… Afaan Oromoo BCV GIZ እምኀበ ስምዖን ኬፋ ገብሩ ወልኡኩ ለኢየሱስ ክርስቶስ ለእለ ነኀብር ክብረ በሃይማኖት እንተ ከፈለነ በጽድቁ ለአምላክነ ወፈራቂነ ኢየሱስ ክርስቶስ። giz GAZGAZ Ani Simoon Phexros, Yesus Kristosiif hojjetaa, ergamaas ta'ee, warra karaa qajeelina Waaqayyo keenyaaf fayyisaa keenyaa… Afaan Oromoo BCV aksum ናይ ኢየሱስ ክርስቶስ ኣገልጋልን ሃዋርያን ካብ ዝኾነ ስምኦን ጴጥሮስ፥ ናብቶም ብናይ እግዚኣብሄርን፥ መድሓኒና ኢየሱስ ክርስቶስን ፅድቂ፥ ከማና ኽብርቲ እምነት ዝተቐበሉ፥ ትግርኛ AMHNIV የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ ስምዖን ጴጥሮስ፤ በአምላካችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ በኩል እንደ ተቀበልነው ዐይነት ክቡር እምነት ለተቀበሉት፤ አማርኛ SWAHSUV Simoni Petro, mtumwa na mtume wa Yesu Kristo, kwa wale waliopata imani moja na sisi, yenye thamani, katika hali ya Mung… Kiswahili