2ኛ ቆሮንቶስ 3

AMHNIVአማርኛ18 ጥቅሶች2:56 አዳምጥ
አዳምጥ 2:56 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እንደ ገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ እንደ ሌሎቹ ለእናንተ ወይም ከእናንተ የተጻፈ የምስጋና ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆንን?

2እናንተኮ ሰው ሁሉ የሚያውቃችሁና የሚያነባችሁ በልባችን ላይ የተጻፋችሁ ደብዳቤዎቻችን ናችሁ፤

3እናንተ በቀለም ሳይሆን በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ፣ በድንጋይ ጽላት ላይ ሳይሆን በሰው ልብ ጽላት ላይ የተጻፋችሁና በእኛ የተገለገላችሁ የክርስቶስ ግልጽ ደብዳቤ ናችሁ።

4በክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት ይህን የመሰለ ነው፤

5ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፣ በራሳችን ብቃት ከእኛ ነው የምንለው አንዳች ነገር የለንም።

6እርሱም በፊደል ላይ ሳይሆን በመንፈስ ላይ የተመሠረተውን የአዲሱ ኪዳን አገልጋዮች እንድንሆን ብቁዎች አደረገን፤ ምክንያቱም ፊደል ይገድላል፤ መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።

7እንግዲህ እስራኤላውያን ከፊቱ ክብር የተነሣ የሙሴን ፊት ትኵር ብለው ማየት እስኪሳናቸው ድረስ፣ ያ ከጊዜ በኋላ የሚያልፈውና በድንጋይ ላይ በፊደል የተቀረጸው የሞት አገልግሎት በክብር ከመጣ፣

8ታዲያ፣ የመንፈስ አገልግሎት እንዴት ከዚያ የላቀ ክብር አይኖረውም?

9ሰዎችን የሚኰንነው አገልግሎት የከበረ ከሆነ፣ የሚያጸድቀው አገልግሎት የቱን ያህል ይበልጥ የከበረ ይሆን!

10ከዚህ በፊት ክቡር የነበረው የላቀ ክብር ካለው ጋር ሲወዳደር ክብር የሌለው ሆኖአል።

11የሚያልፈው ያን ያህል ክብር ከነበረው፣ ጸንቶ የሚኖረውማ እንዴት የላቀ ክብር አይኖረውም?

12እንግዲህ ይህን የመሰለ ተስፋ ስላለን፣ በድፍረት እንናገራለን።

13እስራኤላውያን የፊቱ ማንጸባረቅ እየጠፋ ሲሄድ መጨረሻውን እንዳይመለከቱ፣ ፊቱን በጨርቅ እንደ ሸፈነው እንደ ሙሴ አይደለንም።

14ነገር ግን ብሉይ ኪዳን በተነበበ ቊጥር ያ መሸፈኛ እስከ ዛሬ ድረስ ስላልተወገደ ልቡናቸው እንደ ደነዘዘ ነው፤ መሸፈኛው አሁንም አልተወገደም፤ የሚወገደው በክርስቶስ ብቻ ነውና።

15እስከ ዛሬም ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ቊጥር መሸፈኛው ልቡናቸውን ይሸፍናል።

16ነገር ግን አንድ ሰው ወደ ጌታ ዘወር ሲል መሸፈኛው ይወገዳል።

17ጌታ መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ ነጻነት አለ።

18እኛም ሁላችን ባልተሸፈነ ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያንጸባረቅን፣ የእርሱን መልክ እንድንመስል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን፤ ይህም የሚሆነው መንፈስ ከሆነ ጌታ ነው።

ማብራሪያ

3:1-11 የራስን ከንቱ ውዳሴ ማሳየትም ሆነ የሰውን ምስጋና መፈለግ ለትሑትና ለመንፈሳዊ አእምሮ የሚያሠቃይ ነው። ለታማኝ አገልጋዮች ከምንም በላይ የሚያስደስት ወይም የሚያስመሰግናቸው ነገር የለም፤ ከአገልግሎታቸው ስኬት በቀር፣ ይህም በሚሠሩባቸው ሰዎች መንፈስና ሕይወት እንደሚታይ። የክርስቶስ ሕግ በልባቸው ተጽፎ ነበር፤ የክርስቶስም ፍቅር በዚያ ፈስሶ ነበር። በድንጋይ ጽላት ላይ አልተጻፈም ነበር፣ ለሙሴ እንደተሰጠው የእግዚአብሔር ሕግ፤ ነገር ግን በሥጋዊ የልብ ጽላት ላይ ነው (ይህም የስሜት ፍላጎት የሚያመለክተውን ‘ሥጋዊ’ የሚለውን ቃል አይመለከትም)፣ ሕዝቅኤል 36:26። ልቦናቸው ዝቅ ብሎና ለስልሶ ነበር፣ ይህን ተጽዕኖ ለመቀበል በመንፈስ ቅዱስ እንደገና በሚፈጥረው ኃይል አማካኝነት። እርሱ ክብሩን ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሰጣል። አስታውሱም፣ የእኛ ሙሉ ጥገኝነት በጌታ ላይ እንደሆነ ሁሉ፣ ክብሩም ሁሉ ለርሱ ብቻ ነው። ፊደል ይገድላል፤ የሕጉ ፊደል የሞት አገልግሎት ነው፤ በወንጌል ፊደል ላይ ብቻ የምንታመን ከሆነም፣ ከዚህ የተነሣ የተሻልን አንሆንም፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ሕይወትንና የዘላለም ሕይወትን ይሰጣል። የብሉይ ኪዳን ሥርዓት የሞት አገልግሎት ነበር፤ የአዲስ ኪዳን ግን የሕይወት ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እንደ ገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ እንደ ሌሎች የማመስገኛ መልእክት ወደ እናንተ ወይስ ከእናንተ ያስፈልገን ይሆንን? አማርኛ ENGNIV Are we beginning to commend ourselves again? Or do we need, like some people, letters of recommendation to you or from … English BCV ከምዙይ ክንብል እንተለና፥ ገና ንባዕልትና ንንእድ ዲና ዘለና? ወይ ከምቲ ገሊኣቶም ዝገብርዎ፥ ናባኻትኩም ወይ ከዓ ኻባኻትኩም፥ ናይ ናእዳ መልእኽቲ የድልየና ድዩ? ትግርኛ GAZBIB Ammas keessa deebinee ofiif dubbachuu jalqabnaa ree? Yookiis akka namoota tokko tokkoo caaffata nuuf dubbatu gara keess… Afaan Oromoo BCV GIZ አኀዊነ ነአኀዝኑ ካዕበ ይእዜ ንንግርክሙ ንወድስ ርእሰነ? ወቦኑ ዘንፈቅድ ከመ እልክቱ ካልኣን እስከ ንጽሕፍ ኀቤክሙ በእንቲኣነ መጽሐፈ አው ከመ ትጽሐፉ አንትሙ? giz GAZGAZ Ammas keessa deebinee ofiif dubbachuu jalqabnaa ree? Yookiis akka namoota tokko tokkoo caaffata nuuf dubbatu gara keess… Afaan Oromoo BCV aksum ከምዙይ ክንብል እንተለና፥ ገና ንባዕልትና ንንእድ ዲና ዘለና? ወይ ከምቲ ገሊኣቶም ዝገብርዎ፥ ናባኻትኩም ወይ ከዓ ኻባኻትኩም፥ ናይ ናእዳ መልእኽቲ የድልየና ድዩ? ትግርኛ SWAHSUV Je! Tunaanza tena kujisifu wenyewe? Au tunahitaji, kama wengine, barua zenye sifa kuja kwenu, au kutoka kwenu? Kiswahili