2ኛ ቆሮንቶስ 3

AMHEVGአማርኛ18 ጥቅሶች2:23 አዳምጥ
አዳምጥ 2:23 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እንደ ገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ እንደ ሌሎች የማመስገኛ መልእክት ወደ እናንተ ወይስ ከእናንተ ያስፈልገን ይሆንን?

2ሰዎች ሁሉ የሚያውቁትና የሚያነቡት በልባችን የተጻፈ መልእክታችን እናንተ ናችሁ።

3እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው።

4በክርስቶስም በኩል ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ያለ እምነት አለን።

5ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፤

6እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድ አበቃን፤ ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።

7ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ ተሻረው ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ፥ ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት በክብር ከሆነ፥

8የመንፈስ አገልግሎት እንዴት ይልቅ በክብር አይሆንም?

9የኵነኔ አገልግሎት ክብር ከሆነ፥ ይልቅ የጽድቅ አገልግሎት በክብር አብዝቶ ይበልጣልና።

10ያ የከበረ እንኳ እጅግ በሚበልጠው ክብር ምክንያት በዚህ ነገር ክብሩን አጥቶአልና።

11ያ ይሻር የነበረው በክብር ከሆነ፥ ጸንቶ የሚኖረውማ እጅግ ይልቅ በክብር ሆኖአልና።

12እንግዲህ እንዲህ ያለ ተስፋ ካለን እጅግ ገልጠን እንናገራለን፥

13የዚያንም ይሻር የነበረውን መጨረሻ ትኵር ብለው የእስራኤል ልጆች እንዳይመለከቱ፥ በፊቱ መጋረጃ እንዳደረገ እንደ ሙሴ አይደለንም።

14ነገር ግን አሳባቸው ደነዘዘ። ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ያ መጋረጃ ሳይወሰድ እስከ ዛሬ ድረስ ይኖራልና፤ በክርስቶስ ብቻ የተሻረ ነውና።

15ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ጊዜ ሁሉ ያ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል፤

16ወደ ጌታ ግን ዘወር ባለ ጊዜ ሁሉ መጋረጃው ይወሰዳል።

17ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ።

18እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።

ማብራሪያ

3:1-11 የራስን ከንቱ ውዳሴ ማሳየትም ሆነ የሰውን ምስጋና መፈለግ ለትሑትና ለመንፈሳዊ አእምሮ የሚያሠቃይ ነው። ለታማኝ አገልጋዮች ከምንም በላይ የሚያስደስት ወይም የሚያስመሰግናቸው ነገር የለም፤ ከአገልግሎታቸው ስኬት በቀር፣ ይህም በሚሠሩባቸው ሰዎች መንፈስና ሕይወት እንደሚታይ። የክርስቶስ ሕግ በልባቸው ተጽፎ ነበር፤ የክርስቶስም ፍቅር በዚያ ፈስሶ ነበር። በድንጋይ ጽላት ላይ አልተጻፈም ነበር፣ ለሙሴ እንደተሰጠው የእግዚአብሔር ሕግ፤ ነገር ግን በሥጋዊ የልብ ጽላት ላይ ነው (ይህም የስሜት ፍላጎት የሚያመለክተውን ‘ሥጋዊ’ የሚለውን ቃል አይመለከትም)፣ ሕዝቅኤል 36:26። ልቦናቸው ዝቅ ብሎና ለስልሶ ነበር፣ ይህን ተጽዕኖ ለመቀበል በመንፈስ ቅዱስ እንደገና በሚፈጥረው ኃይል አማካኝነት። እርሱ ክብሩን ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሰጣል። አስታውሱም፣ የእኛ ሙሉ ጥገኝነት በጌታ ላይ እንደሆነ ሁሉ፣ ክብሩም ሁሉ ለርሱ ብቻ ነው። ፊደል ይገድላል፤ የሕጉ ፊደል የሞት አገልግሎት ነው፤ በወንጌል ፊደል ላይ ብቻ የምንታመን ከሆነም፣ ከዚህ የተነሣ የተሻልን አንሆንም፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ሕይወትንና የዘላለም ሕይወትን ይሰጣል። የብሉይ ኪዳን ሥርዓት የሞት አገልግሎት ነበር፤ የአዲስ ኪዳን ግን የሕይወት ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Are we beginning to commend ourselves again? Or do we need, like some people, letters of recommendation to you or from … English BCV ከምዙይ ክንብል እንተለና፥ ገና ንባዕልትና ንንእድ ዲና ዘለና? ወይ ከምቲ ገሊኣቶም ዝገብርዎ፥ ናባኻትኩም ወይ ከዓ ኻባኻትኩም፥ ናይ ናእዳ መልእኽቲ የድልየና ድዩ? ትግርኛ GAZBIB Ammas keessa deebinee ofiif dubbachuu jalqabnaa ree? Yookiis akka namoota tokko tokkoo caaffata nuuf dubbatu gara keess… Afaan Oromoo BCV GIZ አኀዊነ ነአኀዝኑ ካዕበ ይእዜ ንንግርክሙ ንወድስ ርእሰነ? ወቦኑ ዘንፈቅድ ከመ እልክቱ ካልኣን እስከ ንጽሕፍ ኀቤክሙ በእንቲኣነ መጽሐፈ አው ከመ ትጽሐፉ አንትሙ? giz GAZGAZ Ammas keessa deebinee ofiif dubbachuu jalqabnaa ree? Yookiis akka namoota tokko tokkoo caaffata nuuf dubbatu gara keess… Afaan Oromoo BCV aksum ከምዙይ ክንብል እንተለና፥ ገና ንባዕልትና ንንእድ ዲና ዘለና? ወይ ከምቲ ገሊኣቶም ዝገብርዎ፥ ናባኻትኩም ወይ ከዓ ኻባኻትኩም፥ ናይ ናእዳ መልእኽቲ የድልየና ድዩ? ትግርኛ AMHNIV እንደ ገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ እንደ ሌሎቹ ለእናንተ ወይም ከእናንተ የተጻፈ የምስጋና ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆንን? አማርኛ SWAHSUV Je! Tunaanza tena kujisifu wenyewe? Au tunahitaji, kama wengine, barua zenye sifa kuja kwenu, au kutoka kwenu? Kiswahili