2ኛ ቆሮንቶስ 10

AMHNIVአማርኛ18 ጥቅሶች3:25 አዳምጥ
አዳምጥ 3:25 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እኔ ጳውሎስ፣ በእናንተ ፊት ስሆን “ዐይነ ዐፋር”፣ ከእናንተ ስርቅ ግን፣ “ደፋር” የተባልሁ በክርስቶስ የዋህነትና ገርነት እለምናችኋለሁ።

2ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ በዓለማዊ መንገድ እንደምንኖር አድርገው በሚቈጥሩን ሰዎች ላይ በድፍረት ለመናገር ቈርጫለሁ፤ እናንተን ግን በዚያ ዐይነት ድፍረት እንድናገር እንዳታደርጉኝ እለምናችኋለሁ።

3የምንኖረው በዚህ ዓለም ቢሆንም፣ የምንዋጋው በዚህ ዓለም ስልት አይደለም።

4ደግሞም የምንዋጋበት የጦር መሣሪያ የዚህ ዓለም መሣሪያ አይደለም፤ ይሁን እንጂ ምሽግን ለመደምሰስ የሚችል መለኮታዊ ኀይል ያለው ነው።

5በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ በትዕቢት የሚነሣውን ክርክርና ከንቱ ሐሳብ ሁሉ እናፈርሳለን፤ አእምሮንም ሁሉ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን።

6መታዘዛችሁ በተፈጸመ ጊዜ አለ መታዘዝን ሁሉ ለመቅጣት ተዘጋጅተናል።

7እናንተ የምትመለከቱት ውጫዊውን ነገር ብቻ ነው። ማንም የክርስቶስ በመሆኑ ቢመካ እርሱ የክርስቶስ እንደሆነ ሁሉ እኛም የክርስቶስ መሆናችንን ሊገነዘብ ይገባዋል።

8ጌታ በሰጠን ሥልጣን እጅግ ብመካም በዚህ አላፍርም፤ ሥልጣኑን የተቀበል ነው እናንተን ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ አይደለምና።

9በመልእክቶቼ የማስፈራራችሁ አይምሰላችሁ።

10አንዳንዶች፣ “መልእክቶቹ ከባድና ጠንካራ ናቸው፤ ነገር ግን ሰውነቱ ሲታይ ደካማ፣ ንግግሩም የተናቀ ነው” ይላሉ።

11እንዲህ የሚሉ ሰዎች በሩቅ ሆነን በመልእክታችን የምንናገረውን ሁሉ በቅርብ ሆነን በተግባራችን የምንገልጸውም እንደዚያው መሆኑን መገንዘብ አለባቸው።

12ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ሰዎች ጋር ራሳችንን ልንመድብ ወይም ልናነጻጽር አንደፍርም፤ እነርሱ ራሳቸውን በራሳቸው ሲመዝኑና ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር ሲያነጻጽሩ አስተዋዮች አይደሉም።

13እኛ ግን ከመጠን በላይ አንመካም፤ የምንመካው እግዚአብሔር በመደበልንና እስከ እናንተም እንኳ በሚደርሰው የአገልግሎታችን ወሰን ነው።

14የክርስቶስን ወንጌል ይዘን ወደ እናንተ በመጣን ጊዜ፣ ከተመደበልን የአገልግሎት ወሰን አላለፍንም።

15ደግሞም ሌሎች በደከሙበት ሥራ ከመጠን በላይ በመመካት ከተመደበልን ወሰን አናልፍም፤ ይልቁንም እምነታችሁ እያደገ በሄደ ቍጥር በእናንተ ዘንድ የተመደበልን አገልግሎት እየሰፋ እንደሚሄድ ተስፋ እናደርጋለን።

16ስለዚህ በሌላው ሰው ክልል አስቀድሞ በተሠራ ሥራ ሳንመካ፣ ከእናንተ ወዲያ ባለው አገር ወንጌልን መስበክ እንችላለን።

17ነገር ግን፣ “የሚመካ በጌታ ይመካ”፤

18ምክንያቱም ጌታ ራሱ የሚያመሰግነው እንጂ፣ ራሱን በራሱ የሚያመሰግን ተቀባይነት አይኖረውም።

ማብራሪያ

10:1-6 ሌሎች ሐዋርያውን እያናቁና እየተሳለቁበት ሳለ፣ እርሱ ግን ስለራሱ ዝቅ ያለ አሳብ ነበረው፤ በትሕትናም ተናገረ። የራሳችንን ድካሞች ልናውቅ፣ ሰዎች ቢነቅፉንም እንኳ ስለራሳችንም በትሕትና ልናስብ ይገባል። የአገልግሎት ሥራ ከመንፈሳዊ ጠላቶች ጋር የሚደረግ መንፈሳዊ ጦርነት ነው፤ ለመንፈሳዊ ዓላማዎችም ጭምር ነው። የውጪ ኃይል የወንጌል ዘዴ አይደለም፣ ነገር ግን በእውነት ኃይልና በጥበብ የዋህነት የሚደረግ በጽኑ ማሳመን ነው። ሕሊና ለብቻው ለእግዚአብሔር ብቻ ተጠያቂ ነው፤ ሰዎችም በኃይል ሳይገደዱ ወደ እግዚአብሔርና ወደ ግዴታቸው ሊሳቡ ይገባል። በዚህም ምክንያት የጦር ዕቃዎቻችን እጅግ ኃይለኛ ናቸው፤ የእውነት ማስረጃም አሳማኝ ነው። በሰዎች ልብ ውስጥ ባለው በኃጢአትና በሰይጣን ኃይላት በወንጌል ላይ ምን ያህል ተቃውሞ ይነሳል! ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል የሚያገኛቸውን ድሎች ተመልከት። የተመደቡት ዘዴዎች ለአንዳንዶች ደካማ መስለው ቢታዩም፣ በእግዚአብሔር አማካይነት ኃይለኛ ይሆናሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እኔም ራሴ ጳውሎስ፥ በእናንተ ዘንድ ፊት ለፊት ሳለሁ ትሑት የሆንሁ፥ ከእናንተ ግን ብርቅ የምደፍራችሁ፥ በክርስቶስ የዋህነትና ገርነት እመክራችኋለሁ፤ አማርኛ ENGNIV By the meekness and gentleness of Christ, I appeal to you–I, Paul, who am “timid” when face to face with you, but “bold… English BCV ኣነ ጳውሎስ፥ ኣብ ቅድሜኹም ትሑት፥ ካባኻትኩም እንትርሕቕ ግና፥ ደፋር ዝተብሃልኩ፥ ብናይ ክርስቶስ ሕያዋይነትን ለውሃትን፥ እልምነኩም ኣለኹ። ትግርኛ GAZBIB Ani Phaawulos ofiin koo garraamummaadhaa fi garalaafummaa Kristosiin cimsee isin nan gorsa; ani yommuun isin bira jiru … Afaan Oromoo BCV GIZ አስተበቍዐክሙ አኀዊነ አነ ጳውሎስ በየውሀት ወበምሕረተ ክርስቶስ፣ እስመ ሶበ እሄሉ ኀቤክሙ መጠነ አነ በገጽ፣ ወበኀበሰ ኢሀሎኩ እተፊ ላዕሌክሙ፣ ብቍዑኒ እስመ እንዘ ኢሀለውኩ እትአመን በተ… giz GAZGAZ Ani Phaawulos ofiin koo garraamummaadhaa fi garalaafummaa Kristosiin cimsee isin nan gorsa; ani yommuun isin bira jiru … Afaan Oromoo BCV aksum ኣነ ጳውሎስ፥ ኣብ ቅድሜኹም ትሑት፥ ካባኻትኩም እንትርሕቕ ግና፥ ደፋር ዝተብሃልኩ፥ ብናይ ክርስቶስ ሕያዋይነትን ለውሃትን፥ እልምነኩም ኣለኹ። ትግርኛ SWAHSUV Basi, mimi Paulo mwenyewe nawasihi kwa upole na utaratibu wa Kristo; mimi niliye mnyenyekevu nikiwapo pamoja nanyi, bal… Kiswahili