2ኛ ቆሮንቶስ 10

AMHEVGአማርኛ16 ጥቅሶች2:42 አዳምጥ
አዳምጥ 2:42 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እኔም ራሴ ጳውሎስ፥ በእናንተ ዘንድ ፊት ለፊት ሳለሁ ትሑት የሆንሁ፥ ከእናንተ ግን ብርቅ የምደፍራችሁ፥ በክርስቶስ የዋህነትና ገርነት እመክራችኋለሁ፤

2በዓለማዊ ልማድ እንደምንመላለስ በሚቆጥሩን በአንዳንዶች ላይ አምኜ ልደፍር አስባለሁ፥ በዚያ እምነት ግን ከእናንተ ጋር ሆኜ እንዳልደፍር እለምናችኋለሁ።

3በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤

4የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤

5የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥

6መታዘዛችሁም በተፈጸመች ጊዜ አለመታዘዝን ሁሉ ልንበቀል ተዘጋጅተናል።

7በፊታችሁ ያለውን ተመልከቱ። ማንም የክርስቶስ መሆኑን ተረድቶ ቢሆን፥ ይህን እንደ ገና በራሱ ይቁጠረው፤ እርሱ የክርስቶስ እንደ ሆነ እኛ ደግሞ እንዲሁ ነን።

8ጌታ እናንተን ለማነጽ እንጂ እናንተን ለማፍረስ ያይደለ በሰጠው በሥልጣናችን ከፊት ይልቅ ብመካ እንኳ አላፍርም።

9በመልእክቶቼ የማስደነግጣችሁ አይምሰላችሁ።

10መልእክቶቹስ ከባድና ኃይለኛ ናቸው፥ ሰውነቱ ግን ሲታይ ደካማ ነው፥ ንግግሩም የተናቀ ነው ይላሉና።

11እንዲሁ የሚል ይህን ይቁጠረው፤ በሩቅ ሳለን በመልእክታችን በኩል በቃል እንዳለን፥ በፊቱ ደግሞ ሳለን በሥራ እንዲሁ ነን።

12ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንዶች ጋር ራሳችንን ልንቆጥር ወይም ራሳችንን ልናስተያይ አንደፍርምና፤ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር ሲያመዛዝኑ፥ ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር ሲያስተያዩ፥ አያስተውሉም።

13እኛ ግን እግዚአብሔር እንደ ወሰነልን እስከ እናንተ እንኳ እንደሚደርስ እንደ ክፍላችን ልክ እንጂ ያለ ልክ አንመካም።

14ወደ እናንተ እንደማንደርስ አድርገን ከመጠን አናልፍምና፥ የክርስቶስን ወንጌል በመስበክ እስከ እናንተ እንኳ ደርሰናልና፤

15በሌሎች ድካም ያለ ልክ አንመካም፥ ነገር ግን እምነታችሁ ሲያድግ ከእናንተ ወዲያ ባለው አገር እስክንሰብክ ሥራችንን እየጨመርን፥ በክፍላችን በእናንተ ዘንድ እንድንከብር ተስፋ እናደርጋለን፤ በሌላው ክፍል ስለ ተዘጋጀው ነገር አንመካም።

17የሚመካ ግን በጌታ ይመካ፤ እግዚአብሔር የሚያመሰግነው እንጂ ራሱን የሚያመሰግን እርሱ ተፈትኖ የሚወጣ አይደለምና።

ማብራሪያ

10:1-6 ሌሎች ሐዋርያውን እያናቁና እየተሳለቁበት ሳለ፣ እርሱ ግን ስለራሱ ዝቅ ያለ አሳብ ነበረው፤ በትሕትናም ተናገረ። የራሳችንን ድካሞች ልናውቅ፣ ሰዎች ቢነቅፉንም እንኳ ስለራሳችንም በትሕትና ልናስብ ይገባል። የአገልግሎት ሥራ ከመንፈሳዊ ጠላቶች ጋር የሚደረግ መንፈሳዊ ጦርነት ነው፤ ለመንፈሳዊ ዓላማዎችም ጭምር ነው። የውጪ ኃይል የወንጌል ዘዴ አይደለም፣ ነገር ግን በእውነት ኃይልና በጥበብ የዋህነት የሚደረግ በጽኑ ማሳመን ነው። ሕሊና ለብቻው ለእግዚአብሔር ብቻ ተጠያቂ ነው፤ ሰዎችም በኃይል ሳይገደዱ ወደ እግዚአብሔርና ወደ ግዴታቸው ሊሳቡ ይገባል። በዚህም ምክንያት የጦር ዕቃዎቻችን እጅግ ኃይለኛ ናቸው፤ የእውነት ማስረጃም አሳማኝ ነው። በሰዎች ልብ ውስጥ ባለው በኃጢአትና በሰይጣን ኃይላት በወንጌል ላይ ምን ያህል ተቃውሞ ይነሳል! ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል የሚያገኛቸውን ድሎች ተመልከት። የተመደቡት ዘዴዎች ለአንዳንዶች ደካማ መስለው ቢታዩም፣ በእግዚአብሔር አማካይነት ኃይለኛ ይሆናሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV By the meekness and gentleness of Christ, I appeal to you–I, Paul, who am “timid” when face to face with you, but “bold… English BCV ኣነ ጳውሎስ፥ ኣብ ቅድሜኹም ትሑት፥ ካባኻትኩም እንትርሕቕ ግና፥ ደፋር ዝተብሃልኩ፥ ብናይ ክርስቶስ ሕያዋይነትን ለውሃትን፥ እልምነኩም ኣለኹ። ትግርኛ GAZBIB Ani Phaawulos ofiin koo garraamummaadhaa fi garalaafummaa Kristosiin cimsee isin nan gorsa; ani yommuun isin bira jiru … Afaan Oromoo BCV GIZ አስተበቍዐክሙ አኀዊነ አነ ጳውሎስ በየውሀት ወበምሕረተ ክርስቶስ፣ እስመ ሶበ እሄሉ ኀቤክሙ መጠነ አነ በገጽ፣ ወበኀበሰ ኢሀሎኩ እተፊ ላዕሌክሙ፣ ብቍዑኒ እስመ እንዘ ኢሀለውኩ እትአመን በተ… giz GAZGAZ Ani Phaawulos ofiin koo garraamummaadhaa fi garalaafummaa Kristosiin cimsee isin nan gorsa; ani yommuun isin bira jiru … Afaan Oromoo BCV aksum ኣነ ጳውሎስ፥ ኣብ ቅድሜኹም ትሑት፥ ካባኻትኩም እንትርሕቕ ግና፥ ደፋር ዝተብሃልኩ፥ ብናይ ክርስቶስ ሕያዋይነትን ለውሃትን፥ እልምነኩም ኣለኹ። ትግርኛ AMHNIV እኔ ጳውሎስ፣ በእናንተ ፊት ስሆን “ዐይነ ዐፋር”፣ ከእናንተ ስርቅ ግን፣ “ደፋር” የተባልሁ በክርስቶስ የዋህነትና ገርነት እለምናችኋለሁ። አማርኛ SWAHSUV Basi, mimi Paulo mwenyewe nawasihi kwa upole na utaratibu wa Kristo; mimi niliye mnyenyekevu nikiwapo pamoja nanyi, bal… Kiswahili