1ኛ ተሰሎንቄ 1

AMHNIVአማርኛ10 ጥቅሶች2:05 አዳምጥ
አዳምጥ 2:05 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከጳውሎስ፣ ከሲላስና ከጢሞቴዎስ፤ የእግዚአብሔር አብና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ለሆኑት ለተሰሎንቄ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

2በጸሎታችን እያስታወስናችሁ ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን ስለ ሁላችሁ እናመሰግናለን።

3ከእምነት የሆነውን ሥራችሁን፣ ከፍቅር የመነጨውን ድካማችሁንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ ተስፋ የተገኘውን ጽናታችሁን በአምላካችንና በአባታችን ፊት ዘወትር እናስባለን።

4በእግዚአብሔር የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፤ እርሱ እንደ መረጣችሁ እናውቃለን፤

5ምክንያቱም ወንጌላችን ወደ እናንተ የመጣው በኀይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙም መረዳት እንጂ በቃል ብቻ አይደለም። ደግሞ ስለ እናንተ ስንል በመካከላችሁ እንዴት እንደኖርን ታውቃላችሁ።

6እናንተ እኛንና ጌታን መስላችኋል፤ ምንም እንኳ ብርቱ መከራ ቢደርስባችሁም ቃሉን በመንፈስ ቅዱስ ደስታ ተቀብላችኋል።

7ከዚህም የተነሣ በመቄዶንያና በአካይያ ለሚገኙ ምእመናን መልካም ምሳሌ ሆናችኋል።

8የጌታ ቃል ከእናንተ ወጥቶ በመቄዶንያና በአካይያ መሰማቱ ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ያላችሁ እምነት በሁሉ ቦታ ታውቆአል፤ ስለዚህ እኛ በዚህ ጒዳይ ላይ ምንም መናገር አያስፈልገንም፤

9በእንዴት ያለ አቀባበል እንደ ተቀበላችሁንና ሕያውና እውነተኛ የሆነውን አምላክ ለማገልገል ከጣዖታት ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንደ ተመለሳችሁ እነርሱ ራሳቸው ይናገራሉ፤

10ደግሞም ከሙታን ያስነሣውንና ከሰማይ የሚመጣውን ልጁን፣ ከሚመጣውም ቍጣ የሚያድነንን ኢየሱስን እንዴት እንደምትጠባበቁ ይናገራሉ።

ማብራሪያ

1:1-5 መልካም ነገር ሁሉ ከእግዚአብሔር የሚመጣ እንደመሆኑ መጠን፣ ኃጢአተኞች መልካም ነገር ከእግዚአብሔር በክርስቶስ በቀር ከሌላ ሊጠብቁ አይችሉም። ከሁሉ የላቀው መልካም ነገርም እንደ አባታችን ከእግዚአብሔር፣ ስለ ክርስቶስ ሊጠበቅ ይገባል። እኛ ስለ ራሳችን ብቻ ሳይሆን ስለ ሌሎችም መጸለይ ይገባናል፤ ሳናቋርጥም እነርሱን ማሰብ አለብን። እውነተኛ እምነት ባለበት ሁሉ ይሰራል፤ ልብንም ሕይወትንም ይነካል። እምነት በፍቅር ይሠራል፤ ለእግዚአብሔር ባለን ፍቅርና ለባልንጀራችን ባለን ፍቅር ይገለጻል። የተመሠረተ የዘላለም ሕይወት ተስፋ ባለበት ሁሉ፣ ይህ በትዕግሥት መኖር ይገለጣል፤ በምናደርገውም ሁሉ ራሳችንን ለእግዚአብሔር ለማስደሰት ስንጥር የእውነተኛነት ምልክት ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ጳውሎስና ስልዋኖስ ጢሞቴዎስም፥ በእግዚአብሔር አብ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም ወደምትሆን ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስም ጸጋ ሰላም… አማርኛ ENGNIV Paul, Silas and Timothy, To the church of the Thessalonians in God the Father and the Lord Jesus Christ: Grace and peac… English BCV ካብ ጳውሎስን ስልዋኖስን ጢሞቴዎስን፥ ናብታ ኣብ እግዚኣብሄር ኣቦናን፥ ኣብ ጐይታና ኢየሱስ ክርስቶስን ዘላ ቤተ ክርስቲያን ተሰሎንቄ፥ ኻብ እግዚኣብሄር ኣቦናን፥ ካብ ጐይታና ኢየሱስ ክርስቶ… ትግርኛ GAZBIB Phaawulos, Silwaanosii fi Ximotewos biraa, gara waldaa warra Tasaloniiqee isa kan Waaqayyoo abbaa fi kan gooftaa Yesus … Afaan Oromoo BCV GIZ እምጳውሎስ ወስልዋኖስ ወጢሞቴዎስ ለቤተ ክርስቲያን ዘተሰሎንቄ፤ ምእመናን በእግዚአብሔር፣ አቡነ ወእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ሰላም ለክሙ ወጸጋ እግዚአብሔር አቡነ ወእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶ… giz GAZGAZ Phaawulos, Silwaanosii fi Ximotewos biraa, gara waldaa warra Tasaloniiqee isa kan Waaqayyoo abbaa fi kan gooftaa Yesus … Afaan Oromoo BCV aksum ካብ ጳውሎስን ስልዋኖስን ጢሞቴዎስን፥ ናብታ ኣብ እግዚኣብሄር ኣቦናን፥ ኣብ ጐይታና ኢየሱስ ክርስቶስን ዘላ ቤተ ክርስቲያን ተሰሎንቄ፥ ኻብ እግዚኣብሄር ኣቦናን፥ ካብ ጐይታና ኢየሱስ ክርስቶ… ትግርኛ SWAHSUV Paulo, na Silwano, na Timotheo, kwa kanisa la Wathesalonike, lililo katika Mungu Baba, na katika Bwana Yesu Kristo. Nee… Kiswahili