1ኛ ዮሐንስ 3

AMHNIVአማርኛ24 ጥቅሶች4:10 አዳምጥ
አዳምጥ 4:10 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ አትረፍርፎ ያፈሰሰልን ፍቅር ምንኛ ታላቅ ነው! እኛም እንዲሁ ልጆቹ ነን። ዓለም እኛን የማያውቀንም እርሱን ስላላወቀው ነው።

2ወዳጆች ሆይ፤ እኛ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ወደ ፊት ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። እርሱ በሚገለጥበት ጊዜ እናየዋለንና፣ እርሱን እንደ ምንመስል እናውቃለን።

3በእርሱ ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ፣ እርሱ ንጹሕ እንደሆነ ራሱን ያነጻል።

4ኀጢአት የሚያደርግ ሁሉ ዐመፅን ያደርጋል፤ ኀጢአትም ዐመፅ ነው።

5እርሱ ኀጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፤ በእርሱም ኀጢአት የለም።

6በእርሱም የሚኖር ኀጢአትን አያደርግም፤ ኀጢአት የሚያደርግ ግን እርሱን አላየውም ወይም አላወቀውም።

7ልጆች ሆይ፤ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤ እርሱ ጻድቅ እንደሆነ፣ ጽድቅን የሚያደርግ ጻድቅ ነው።

8ኀጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው። ምክንያቱም ዲያብሎስ ከመጀመሪያ አንሥቶ ኀጢአትን የሚያደርግ ነው። የእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠውም የዲያብሎስን ሥራ ያፈርስ ዘንድ ነው።

9ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኀጢአትን አያደርግም፤ የእርሱ ዘር በውስጡ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደም ኀጢአትን ሊያደርግ አይችልም።

10የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች ተለይተው የሚታወቁት በዚህ ነው፦ ጽድቅን የማያደርግ፣ ወንድሙንም የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም።

11ከመጀመሪያ የሰማችኋት፣ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል የምትለዋ መልእክት ይህች ናትና፤

12የክፉው ወገን ሆኖ ወንድሙን እንደ ገደለው እንደ ቃየን አትሁኑ፤ ለምን ገደለው? ምክንያቱም የእርሱ ሥራ ክፉ፣ የወንድሙ ግን ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።

13ወንድሞች ሆይ፤ ዓለም ቢጠላችሁ አትደነቁ።

14ወንድሞቻችንን ስለምንወድ ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤ ፍቅር የሌለው ሁሉ በሞት ይኖራል።

15ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳይም የዘላለም ሕይወት እንደሌለው ታውቃላችሁ።

16ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወቱን ስለ እኛ አሳልፎ ስለ ሰጠ፣ ፍቅር ምን እንደሆነ በዚህ እናውቃለን፤ እኛም ሕይወታችንን ስለ ወንድሞቻችን አሳልፈን ልንሰጥ ይገባናል።

17ማንም ሀብት እያለው፣ ወንድሙ ሲቸገር አይቶ ባይራራለት፣ የእግዚአብሔር ፍቅር እንዴት በእርሱ ይኖራል?

18ልጆች ሆይ፤ በተግባርና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ።

19እኛ የእውነት ወገን መሆናችንን በዚህ እናውቃለን፤ ልባችንንም በፊቱ እናሳርፋለን፣

20ይህም ልባችን በእኛ ላይ በሚፈርድብን ነገር ሁሉ ነው። እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉን ነገር ያውቃል።

21ወዳጆች ሆይ፤ ልባችን የማይፈርድብን ከሆነ በእግዚአብሔር ፊት ድፍረት አለን፤

22ትእዛዛቱንም ስለምንጠብቅና በፊቱም ደስ የሚያሰኘውን ስለምናደርግ የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እንቀበላለን።

23ትእዛዙም በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እንድናምንና እርሱ እንዳዘዘንም እርስ በርሳችን እንድንዋደድ ነው።

24ትእዛዞቹንም የሚጠብቁ ሁሉ በእርሱ ይኖራሉ፤ እርሱም በእነርሱ ይኖራል። በእኛ መኖሩን በዚህ ይኸውም እርሱ በሰጠን መንፈስ እናውቃለን።

ማብራሪያ

3:1,2 ዓለም የእውነተኛ የክርስቶስ ተከታዮች ደስታ ምን ያህል እንደሆነ አያውቅም። ዓለም እነዚህ ምስኪኖች፣ ትሑታንና የተናቁ ሰዎች የእግዚአብሔር ተወዳጆች እንደሆኑና በሰማይም እንደሚኖሩ አያስብም። የክርስቶስ ተከታዮች ጌታቸው ከእነርሱ በፊት እጅግ በክፉ በተያዘባት የባዕዳን ምድር ላይ ስለሆኑ፣ እዚህ ባለው አስቸጋሪ ኑሯቸው ይርኩ። የእግዚአብሔር ልጆች በእምነት መመላለስና በተስፋ መኖር አለባቸው። የጌታ ኢየሱስን መገለጥ በእምነት፣ በተስፋና በጋለ ምኞት ቢጠብቁ መልካም ነው። የእግዚአብሔር ልጆች ይታወቃሉ፣ ከራሳቸውም (ከጌታቸው) ጋር ባላቸው መመሳሰል ይገለጣሉ። እርሱን በመመልከት ወደዚያው አምሳል ይለወጣሉ።

3:3-10 የእግዚአብሔር ልጆች ጌታቸው ርኩስና ቅዱስ ያልሆነ ነገር ሁሉ ከእርሱ ጋር እንዲኖር የማይፈቅድ፣ የንጹሕ ዓይኖች ባለቤት መሆኑን ያውቃሉ። ርኩስ ምኞቶችንና የሥጋ ፍላጎቶችን ለማርካት የሚፈቅደው፣ የእግዚአብሔር ልጆች ሳይሆን የግብዞች ተስፋ ነው። እኛ እንደ ውድ ልጆቹ እርሱን የምንከተል በመሆን፣ የእርሱን የማይነገረውን ምሕረቱን ያለንን ግንዛቤ እናሳይ፤ የሚገባንንም ታዛዥ፣ አመስጋኝና ትሑት አእምሮ እንግለጽ። ኃጢአት ማለት መለኮታዊውን ሕግ መጣስ ነው። በእርሱ ማለትም በክርስቶስ ኃጢአት አልነበረም። ከውድቀት የተነሱት ኃጢአት የሌለባቸው ድካሞች ሁሉ፤ ማለትም ሰውን ለሥቃይ የሚያጋልጡና ለፈተናም የሚያጋልጡ የአእምሮ ወይም የሰውነት ድካሞችን ሁሉ እርሱ ተቀበለ። ነገር ግን የእኛን የሞራል ድካሞች፣ ኃጢአት የማድረግ ዝንባሌያችንን ግን እርሱ አልነበረውም። በክርስቶስ የሚኖር በኃጢአት ሥራ አይዘወትርም። ኃጢአትን መተው ከጌታ ክርስቶስ ጋር መንፈሳዊ አንድነት፣ በእርሱ መጽናትና መዳን የሆነ ዕውቀት ትልቁ ማስረጃ ነው። ራስን ማታለል ተጠንቀቁ። ጽድቅን የሚያደርግ ጻድቅ ነው፤ የክርስቶስ ተከታይ መሆንም በእርሱ ታዛዥነትና መከራ ላይ በእምነት ያለውን ድርሻ ያሳያል። ነገር ግን አንድ ሰው እንደ ሰይጣን ሆኖ ሲሠራ፣ በተመሳሳይ ጊዜ የክርስቶስ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ሊሆን አይችልም። የእግዚአብሔር ልጅ ሊያጠፋው የመጣውን ነገር አናገልግል ወይም አናበረታታ። ከእግዚአብሔር እንደገና መወለድ ማለት በእግዚአብሔር መንፈስ ኃይል ከውስጥ መታደስ ነው። አድሳሹ ጸጋ ጸንቶ የሚኖር መርህ ነው። ሃይማኖት ጥበብ አይደለም፣ የብልሃትና የችሎታ ጉዳይም አይደለም፤ ነገር ግን አዲስ ባሕርይ ነው። እንደገና የተወለደው ሰው ከእግዚአብሔር ከመወለዱ በፊት እንዳደረገው፣ እንዲሁም እንደገና ያልተወለዱት ሌሎች እንደሚያደርጉት ኃጢአት መሥራት አይችልም። በአእምሮው ውስጥ የኃጢአትን ክፋትና መጥፎነት የሚያሳየው ብርሃን አለ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም። አማርኛ ENGNIV How great is the love the Father has lavished on us, that we should be called children of God! And that is what we are!… English BCV ውሉድ እግዚኣብሄር ተብሂልና ምእንቲ ኽንፅዋዕ፥ እግዚኣብሄር ኣብ፥ ከመይ ዝበለ ፍቕሪ ኸም ዝሃበና እስኪ ረአዩ! ውሉድ እግዚኣብሄርውን ኢና። ዓለም ንእኡ ስለ ዘይፈለጠቶ እያ፥ ነኣናውን ዘይ… ትግርኛ GAZBIB Abbaan jaalala guddaa attamii akka nu argisiise mee ilaalaa! Jaalala kanaan nuyi ijoollee Waaqayyoo jedhamnee in waamam… Afaan Oromoo BCV GIZ ወርእዩ ዘከመ እፎ ፍቅሩ ዘወሀበነ አብ ከመ ውሉደ እግዚአብሔር ንኩን ወኮነሂ፣ ወበእንተዝ ኢፈተወነ ዓለም እስመ ሎቱኒ ኢያእመሮ። giz GAZGAZ Abbaan jaalala guddaa attamii akka nu argisiise mee ilaalaa! Jaalala kanaan nuyi ijoollee Waaqayyoo jedhamnee in waamam… Afaan Oromoo BCV aksum ውሉድ እግዚኣብሄር ተብሂልና ምእንቲ ኽንፅዋዕ፥ እግዚኣብሄር ኣብ፥ ከመይ ዝበለ ፍቕሪ ኸም ዝሃበና እስኪ ረአዩ! ውሉድ እግዚኣብሄርውን ኢና። ዓለም ንእኡ ስለ ዘይፈለጠቶ እያ፥ ነኣናውን ዘይ… ትግርኛ SWAHSUV Tazameni, ni pendo la namna gani alilotupa Baba, kwamba tuitwe wana wa Mungu; na ndivyo tulivyo. Kwa sababu hii ulimwen… Kiswahili