1ኛ ቆሮንቶስ 14

AMHNIVአማርኛ40 ጥቅሶች6:57 አዳምጥ
አዳምጥ 6:57 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ፍቅርን ተከታተሉ፤ መንፈሳዊ ስጦታዎችን፣ በተለይም ትንቢት የመናገርን ስጦታ በብርቱ ፈልጉ።

2በልሳን የሚናገር ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርምና፤ ምስጢር የሆነውን በመንፈስ ስለ ሚናገር የሚረዳው የለም።

3ትንቢትን የሚናገር ግን ለማነጽ፣ ለማበረታታትና ለማጽናናት ለሰው ይናገራል።

4በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ ትንቢትን የሚናገር ግን ቤተ ክርስቲያንን ያንጻል።

5ሁላችሁም በልሳን ብትናገሩ እወዳለሁ፤ ከዚህ ይልቅ ግን ትንቢትን ብትናገሩ እወዳለሁ። ቤተ ክርስቲያን እንድትታነጽ በልሳን የሚናገር ሰው የተናገረውን ካልተረጐመ፣ በልሳን ከሚናገር ይልቅ ትንቢትን የሚናገር ይበልጣል።

6እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ፣ በመግለጥ ወይም በዕውቀት ወይም በትንቢት ወይም በትምህርት ካልነገርኋችሁ በልሳን ብናገር ምን እጠቅማችኋለሁ?

7እንደ ዋሽንትና እንደ በገና ያሉ ሕይወት የሌላቸው ነገሮች እንኳ የድምፃቸው ቃና ልዩነት ከሌለው ዜማቸውን እንዴት ማወቅ ይቻላል?

8ደግሞም መለከት ትክክል ያልሆነ የጥሪ ድምፅ ካሰማ፣ ለጦርነት ማን ይዘጋጃል?

9እናንተም እንደዚሁ ናችሁ፤ ከአንደበታችሁ ትርጒም ያለው ቃል ካልወጣ፣ የምትናገሩትን ማን ሊያስተውለው ይችላል? ለነፋስ የምትናገሩ ትሆናላችሁ።

10በዓለም ላይ ብዙ ዐይነት ቋንቋዎች አሉ፤ ትርጒም የሌለውም ቋንቋ የለም።

11እንግዲህ አንድ ሰው የሚናገረውን ቋንቋ ትርጒሙን ካላወቅሁ፣ ለሚናገረው እንግዳ እሆንበታለሁ፤ እርሱም ለእኔ እንግዳ ይሆንብኛል።

12እናንተም እንደዚሁ ናችሁ፤ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለማግኘት የምትሹ በመሆናችሁ፣ ቤተ ክርስቲያን የምትታነጽበትን ስጦታዎች ለማግኘት ይበልጥ ፈልጉ።

13ስለዚህ በልሳን የሚናገር ሰው የሚናገረውን መተርጐም እንዲችል ይጸልይ።

14በልሳን በምጸልይበት ጊዜ መንፈሴ ይጸልያል፤ አእምሮዬ ግን ያለ ፍሬ ነው።

15ታዲያ፣ ምን ማድረግ አለብኝ? በመንፈስ እጸልያለሁ፤ በአእምሮም ደግሞ እጸልያለሁ፤ በመንፈስ እዘምራለሁ፤ በአእምሮም ደግሞ እዘምራለሁ።

16እንዲህማ ካልሆነ እግዚአብሔርን በመንፈስ በምታመሰግንበት ጊዜ፣ ለነገሩ እንግዳ የሆነ ሰው አንተ የምትናገረውን ካልተረዳ፣ እንዴት አድርጎ ለምስጋናህ፣ “አሜን” ሊል ይችላል?

17አንተ በሚገባ ታመሰግን ይሆናል፤ ሌላው ሰው ግን አይታነጽበትም።

18ከሁላችሁ የበለጠ በልሳን ስለምናገር እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።

19ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሌሎችን ለማስተማር፣ ዐሥር ሺህ ቃላት በልሳን ከምናገር ይልቅ፣ አምስት ቃላት በአእምሮዬ ብናገር ይሻላል።

20ወንድሞች ሆይ፤ በአስተሳሰባችሁ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፉ ነገር ሕፃናት ሁኑ፤ በአስተሳሰባችሁ ግን ጐልማሶች ሁኑ።

21በሕግም እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፤ “ቋንቋቸው እንግዳ በሆነ ሰዎች፣ በባዕዳንም አንደበት፣ ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ፤ ይህም ሆኖ አይሰሙኝም፤” ይላል ጌታ።

22ስለዚህ በልሳን መናገር ለማያምኑ የሚሆን ምልክት እንጂ ለሚያምኑ አይደለም፤ ትንቢት ግን ለሚያምኑ እንጂ ለማያምኑ አይደለም።

23እንግዲህ የቤተ ክርስቲያን ምእመናን በአንድነት በተሰበሰቡበት፣ ሁሉም በልሳን በመናገር ላይ ሳሉ፣ እንግዶች ወይም የማያምኑ ሰዎች ወደ ጉባኤው ቢገቡ፣ አብደዋል አይሉምን?

24ነገር ግን ሁሉም ትንቢት በመናገር ላይ ሳሉ፣ እንግዳ ወይም የማያምን ሰው ቢገባ፣ በሁሉ ይወቀሣል፤ በሁሉ ይመረመራል፤

25በልቡም የተሰወረው ነገር ይገለጣል፤ እንዲሁም፣ “እግዚአብሔር በርግጥ በመካከላችሁ ነው” በማለት በግንባሩ ተደፍቶ ለእግዚአብሔር ይሰግዳል።

26ወንድሞች ሆይ፤ እንግዲህ ምን እንበል? በምትሰበሰቡበት ጊዜ እያንዳንዱ መዝሙር አለው፤ ትምህርት አለው፤ መግለጥ አለው፤ በልሳን መናገር አለው፤ መተርጐም አለው። ይህ ሁሉ ግን ለማነጽ ይሁን።

27በልሳን የሚናገር ቢኖር፣ ሁለት ወይም ቢበዛ ሦስት በየተራ ይናገሩ፤ ሌላው ደግሞ ይተርጒም፤

28የሚተረጒም ሰው ከሌለ ግን በጉባኤ መካከል ዝም ይበልና፤ ለራሱና ለእግዚአብሔር ይናገር።

29ሁለት ወይም ሦስት ነቢያት ይናገሩ፤ ሌሎቹ ደግሞ የተነገረውን በጥንቃቄ ይመዝኑ።

30ከተቀመጡትም መካከል አንድ ሰው አንድ ነገር ቢገለጥለት፣ የመጀመሪያው ተናጋሪ ዝም ይበል።

31እያንዳንዳችሁ እንድትማሩና እያንዳንዳችሁ እንድትበረታቱ፣ ሁላችሁ በየተራ ትንቢት መናገር ትችላላችሁ።

32የነቢያት መናፍስት ለነቢያት ይታዘዛሉ፤

33እግዚአብሔር የሰላም አምላክ እንጂ የሁከት አምላክ አይደለም። በቅዱሳን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲሁ ነው፤

34ሴቶች በጉባኤ ዝም ይበሉ፤ ሕግም እንደሚለው እንዲታዘዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውም፤

35ሴቶች ለማወቅ የሚፈልጉት አንዳንድ ነገር ካለ፣ ባሎቻቸውን በቤት ይጠይቁ፤ ምክንያቱም ሴት በጉባኤ መካከል ብትናገር የሚያሳፍር ነው።

36የእግዚአብሔር ቃል የወጣው ከእናንተ ነውን? ወይስ የደረሰው ወደ እናንተ ብቻ ነውን?

37ማንም ነቢይ ነኝ የሚል ወይም መንፈሳዊ ስጦታ አለኝ የሚል ቢኖር፣ ይህ የጻፍሁላችሁ የጌታ ትእዛዝ መሆኑን ይወቅ፤

38ይህን የማያውቅ ቢሆን ግን እርሱም አይታወቅ።

39ስለዚህ፣ ወንድሞች ሆይ፤ ትንቢት ለመናገር በብርቱ ፈልጉ፤ በልሳን መናገርንም አትከልክሉ፤

40ነገር ግን ሁሉም በአግባብና በሥርዐት ይሁን።

ማብራሪያ

፲፬፡፩-፭ ትንቢት መናገር፣ ማለትም ቅዱሳት መጻሕፍትን መግለጥ፣ በልሳን ከመናገር ጋር ይነፃፀራል። ይህ ከቅዱሳት መጻሕፍት ግልፅ ትርጓሜ ይልቅ ትኩረትን ይስብ ነበር፤ ትዕቢትንም በይበልጥ ያረካል ነበር እንጂ የክርስቲያናዊ ፍቅርን ዓላማ ያነሰ ያበረታታል ነበር፤ ለሰዎች ነፍሳትም በእኩል መልኩ መልካም አያደርግም ነበር። ሊገባ የማይችል ነገር በፍፁም ሊያጸና አይችልም። ሰሚዎች መናገር ወይም መረዳት በማይችሉት ቋንቋ ከተነገሩ፣ ከታላላቅ ትምህርቶች እንኳ ምንም ጥቅም ሊገኝ አይችልም። እያንዳንዱ ችሎታ ወይም ስጦታ በሚሰጠው ጥቅም ልክ ዋጋ አለው። ብርቱ መንፈሳዊ ፍቅር እንኳ በማስተዋል አጠቃቀም ሊመራ ይገባል፤ አለበለዚያ ሰዎች ሊያስተዋውቁት የሚሞክሩትን እውነት ያሳፍራሉ።

፲፬፥፮-፲፬ ሐዋርያም ቢሆን፣ ሰሚዎቹ በሚረዱት መንገድ ካልተናገረ በቀር ሊያነጽ አይችልም ነበር። ለሚሰሙት ትርጉም የሌላቸውን ቃላት መናገር ነፋስ እንደመናገር ነው። ትርጉም የሌለው ነገር የመናገርን ዓላማ ማሟላት አይችልም፤ በዚህ ሁኔታ ተናጋሪውና ሰሚዎቹ እርስ በእርሳቸው አረማውያን ናቸው። ሁሉም ሃይማኖታዊ አገልግሎቶች በክርስቲያናዊ ጉባኤዎች ውስጥ ሁሉም እንዲሳተፉበትና እንዲጠቀሙበት በሚያስችል መንገድ መፈጸም አለባቸው። ግልጽና ለመረዳት ቀላል የሆነ ቋንቋ ለሕዝብ አምልኮ እንዲሁም ለሌሎች መንፈሳዊ ልምምዶች እጅግ ተገቢ ነው። እውነተኛ የክርስቶስ ተከታይ ሁሉ የተማረ ወይም ጥሩ ንግግር ያለው ሰው ተብሎ ስም ከማግኘት ይልቅ ለሌሎች መልካም ለማድረግ ይመኛል።

14:15-25

ባልተረዱ ጸሎቶች ላይ አሜን ማለት አይቻልም። እውነተኛ ክርስቲያን አገልጋይ ለራሱ ከፍተኛውን ጭብጨባ ከማግኘት ይልቅ፣ ለሰዎች ነፍሳት መንፈሳዊ በጎ ነገር ለማድረግ ይበልጥ ይጥራል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6