1ኛ ዜና መዋዕል 27

AMHNIVአማርኛ34 ጥቅሶች6:30 አዳምጥ
አዳምጥ 6:30 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የእስራኤል የቤተ ሰብ አለቆች፣ የሻለቆች፣ የመቶ አለቆች እንዲሁም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የሚመደቡትን ዋና ዋና ክፍሎች በተመለከተ ንጉሡን ያገለገሉ አለቆቻቸው ዝርዝር ይህ ነው። እያንዳንዱ ዋና ክፍል ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረው።

2በመጀመሪያው ወር የመጀመሪያው ዋና ክፍል የበላይ የዘብድኤል ልጅ ያሾብዓም ሲሆን፣ በሥሩ የሚታዘዙ ሃያ አራት ሺህ ሰዎች ነበሩ።

3እርሱም የፋሬስ ዘር ሲሆን፣ በመጀመሪያው ወር የሰራዊቱ ሹማምት ሁሉ የበላይ ነበር።

4በሁለተኛው ወር የክፍለ ጦሩ የበላይ አዛዥ አሆሃዊው ዱዲ ሲሆን፣ የዚሁ ክፍል መሪ ደግሞ ሚቅሎት ነው፤ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።

5በሦስተኛውም ወር የሦስተኛው ክፍለ ጦር የበላይ አዛዥ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነበረ፤ ዋናው እርሱ ሲሆን፣ በሥሩ ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።

6ይህም ከሠላሳዎቹ ይልቅ ኀያል ሲሆን፣ የሠላሳዎቹ የበላይ ነበረ፤ ልጁ ዓሚዛ ባድም የክፍሉ ሰራዊት አዛዥ ነበረ።

7በአራተኛው ወር አራተኛው የበላይ አዛዥ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል ሲሆን፣ በእግሩ የተተካውም ልጁ ዝባድያ ነው፤ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።

8በአምስተኛው ወር አምስተኛው የበላይ አዛዥ ይዝራዊው ሸምሁት ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።

9በስድስተኛ ወር ስድስተኛው የበላይ አዛዥ የቴቁሐዊው የዒስካ ልጅ ዒራስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።

10በሰባተኛው ወር ሰባተኛው የበላይ አዛዥ የኤፍሬም ወገን የሆነው ፍሎናዊው ሴሌስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።

11በስምንተኛው ወር ስምንተኛው የበላይ አዛዥ ከካዛራውያን ወገን የሆነው ኩሳታዊው ሲቦካይ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።

12በዘጠነኛው ወር ዘጠነኛው የበላይ አዛዥ ከብንያም ወገን የሆነው ዓናቶታዊው አቢዔዜር ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።

13በዐሥረኛው ወር ዐሥረኛው የበላይ አዛዥ ከከዛራውያን ወገን የሆነው ነጦፋዊው ኖኤሬ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።

14በዐሥራ አንደኛው ወር ዐሥራ አንደኛው የበላይ አዛዥ ከኤፍሬም ወገን የሆነው ጲርዓቶናዊው በናያስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።

15በዐሥራ ሁለተኛው ወር ዐሥራ ሁለተኛው የበላይ አዛዥ ከጎቶንያል ቤተ ሰብ የሆነው ነጦፋዊው ሔልዳይ ነበረ።

16የየነገዱ የእስራኤል የጦር ሹማምት፤ በሮቤል ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዝክሪ ልጅ አልዓዛር፤ በስምዖን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የመዓካ ልጅ ሰፋጥያስ።

17በሌዊ ነገድ ላይ የተሾመው የቀሙኤል ልጅ ሐሸብያ፤ በአሮን ነገድ ላይ የተሾመው፣ ሳዶቅ።

18በይሁዳ ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዳዊት ወንድም ኤሊሁ፤ በይሳኮር ነገድ ላይ የተሾመው፣ የሚካኤል ልጅ ዖምሪ።

19በዛብሎን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የአብድዩ ልጅ ይሽማያ፤ በንፍታሌም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዓዝሪኤል ልጅ ኢያሪሙት።

20በኤፍሬም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዓዛዝያ ልጅ ሆሴዕ፤ በምናሴ ነገድ እኵሌታ ላይ የተሾመው፣ የፈዳያ ልጅ ኢዩኤል።

21በገለዓድ ባለው የምናሴ ነገድ እኵሌታ ላይ የተሾመው፣ የዘካርያስ ልጅ አዶ፤ በብንያም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የአበኔር ልጅ የዕሢኤል።

22በዳን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የይሮሐም ልጅ ዓዛርኤል፤ እንግዲህ የእስራኤል ነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ።

23እግዚአብሔር እስራኤልን እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደሚያበዛቸው ተስፋ ሰጥቶ ስለ ነበር፣ ዳዊት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በታች የሆነውን አልቈጠረም ነበር።

24የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቊጠር ጀመረ፤ ሆኖም አልፈጸመውም፤ መቈጠራቸው በእስራኤል ላይ ቊጣ ስላመጣ፣ የተቈጠረውም በንጉሡ ዳዊት መዝገብ አልገባም።

25የዓዲኤል ልጅ ዓዝሞት የቤተ መንግሥቱ ዕቃ ቤት ኀላፊ ነበረ፤ የዖዚያ ልጅ ዮናታን በየአውራጃው በየከተማው፣ በየመንደሩና በየቃፊር መጠበቂያው ላሉት ዕቃ ቤቶች ኀላፊ ነበረ።

26የክሉብ ልጅ ዔዝሪ ምድሪቱን ለሚያርሱት ገበሬዎች ኀላፊ ነበረ።

27ራማታዊው ሰሜኢ የወይን ተክል ቦታዎች ኀላፊ ነበረ፤ ሸፋማዊው ዘብዲ የወይን ጠጅ ዕቃ ቤት ኀላፊ ነበረ።

28ጌድራዊው በአልሐናን በምራባዊው ኰረብታዎች ግርጌ ለሚግኙት የወይንና የወርካ ዛፎች ጥበቃ ኀላፊ ነበረ።

29ሳሮናዊው ሰጥራይ በሳሮን ለሚሰማሩት የከብት መንጋዎች ኀላፊ ነበረ፤ የዓድላይ ልጅ ሻፋጥ በሸለቆው ውስጥ ላሉት የከብት መንጋዎች ኀላፊ ነበረ።

30እስማኤላዊው ኡቢያስ የግመሎች ኀላፊ ነበረ። ሜሮኖታዊው ዬሕድያ የአህዮች ኀላፊ ነበረ።

31አጋራዊው ያዚዝ የበግና የፍየል መንጋዎች ኀላፊ ነበረ። እነዚህ ሁሉ የንጉሥ ዳዊት ንብረት ኀላፊዎች ነበሩ።

32አስተዋይ የሆነው የዳዊት አጎት ዮናታን አማካሪና ጸሓፊ ነበረ፤ የሐክሞኒም ልጅ ይሒኤል ደግሞ የንጉሡ ልጆች ሞግዚት ነበረ።

33አኪጦፌል የንጉሡ አማካሪ ሲሆን፣ አርካዊው ኩሲ ደግሞ የንጉሡ ወዳጅ ነበረ።

34የበናያስ ልጅ ዮዳሄና አብያታር በአኪጦፌል እግር ተተኩ። ኢዮአብም የንጉሡ የክብር ዘብ አዛዥ ሆነ።

ማብራሪያ

27:1-15 በዚህ ዓለም መንግሥታት ዘንድ ለጦርነት መዘጋጀት ለሰላም ደህንነትን ያስገኛል፤ በተመሳሳይ መልኩ የሰይጣንን ጥቃቶች ከሁሉ በላይ የሚያበረታታው ንቁ አለመሆን ነው። በእግዚአብሔር ሙሉ የጦር ዕቃ ታጥቀን፣ እምነትን በመተግበር፣ እናም ለትግሉ ልባችንን በማዘጋጀት እስቆምን ድረስ፣ በእርግጠኝነት ደህና እንሆናለን፣ ምናልባትም ውስጣዊ ሰላምን እናጣጥማለን።

ምዕራፍ 27 በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የሲቪል ዝርዝርን፣ ወታደራዊውንም ጨምሮ፣ እናገኛለን።

I. ለእያንዳንዱ ወር አስራ ሁለቱ አለቆች (ቁጥር 1–15)።

II. የየነገዶቹ አለቆች (ቁጥር 16–24)።

III. የቤተ መንግሥቱ ባለሥልጣናት (ቁጥር 25–34)።

ቁጥር 1-15 እዚህ ላይ የመንግሥቱን ሚሊሻ አደረጃጀት በተመለከተ ዘገባ እናገኛለን። ዳዊት ራሱ የጦር ሰው ነበር፤ በሰይፍም ታላላቅ ነገሮችን አድርጓል። ታላላቅ ሠራዊቶችን ወደ ውጊያ ሜዳ አምጥቶ ነበር። አሁን እግዚአብሔር ከጠላቶቹ ሁሉ ዕረፍት በሰጠው ጊዜ እንዴት እንዳደራጃቸው ተነግሮናል። ሁሉንም በአንድ ላይ አላስቀመጣቸውም ነበር፤ ምክንያቱም ያ ለእነርሱም ሆነ ለአገሪቱ ከባድ ይሆን ነበር። ሆኖም ሁሉንም አላፈረሰም ወይም አልበተናቸውም፤ ምክንያቱም ያን ጊዜ መንግሥቱን ያለ ጥበቃ ይተው ነበር፣ ሕዝቡም የተማሩበትን የጦርነት ጥበብ ይረሱ ነበር። ስለዚህ ቋሚ ኃይል እንዲኖር አደረገ፣ ነገር ግን ቋሚ ሠራዊት አልነበረም። ይህ አደረጃጀት በጣም አስተዋይነት የተሞላበት ነው።

1. እርሱ 24,000 ሰዎችን በቋሚነት በጦር መሣሪያ የታጠቁ አድርጎ አስቀመጠ፤ እኔ እንደማስበው በአንድ አካል ውስጥ፣ እና በሰለጠነ መልኩ፣ በመንግሥቱ አንድ ክፍል ወይም በሌላ ክፍል ውስጥ፣ ነፃ ባለርስቶች የራሳቸውን መሣሪያ ይዘውና በሥራ ላይ እያሉ የራሳቸውን ወጪ እየሸፈኑ ነበር። ይህ ለሕዝብ ሰላምና ደህንነት በቂ ጥንካሬ ነበር። በእውነት እስራኤላውያን የሆኑት ጦርነትን መማር አለባቸው፤ ምክንያቱም ዘወትር መጠንቀቅ ያለብን ልንታገልባቸው የሚገቡ ጠላቶች አሉን።

2. በየወሩ ይለዋውጣቸው ነበር፤ ስለዚህም አጠቃላይ የሚሊሻው ቁጥር 288,000 ደርሷል፤ ምናልባትም ከመንግሥቱ ብቃት ካላቸው ወንዶች አንድ አምስተኛ ያህሉ ይሆናል። በዚህ መንገድ በአሥራ ሁለት ክፍሎች በመከፋፈላቸው፣ ሁሉም በወታደራዊ ልምምዶች የሰለጠኑና የለመዱ ነበሩ፤ ሆኖም ማንም ሰው በዓመት ከአንድ ወር በላይ በአገልግሎት ላይ እንዲቆይ ወይም ወጪ እንዲያወጣ አይገደድም ነበር (ይህንንም በቀላሉ መሸፈን ይችሉ ነበር)፣ ልዩ ሁኔታዎች ካልተፈጠሩ በስተቀር፤ ያን ጊዜም ሁሉም በፍጥነት ሊሰበሰቡ ይችሉ ነበር። የመሪዎች ጥበብና ታላቅ ምስጋናቸውም፣ ለሕዝብ ደህንነት ሲሉ፣ ውጤታማ ሆኖም ቀላል እንዲሆን፣ እና ለሕዝቡ በተቻለ መጠን ሸክም እንዳይሆን ማቀድ ነው።

3. እያንዳንዱ ክፍል የራሱ ዋና አዛዥ ነበረው። በሺዎች፣ በመቶዎችና በሃምሳዎች ላይ ከነበሩት የበታች መኮንኖች በተጨማሪ፣ ለእያንዳንዱ ክፍል ወይም ጦር አንድ ዋና መኮንን ነበረ። እነዚህ አስራ ሁለቱ ታላላቅ አዛዦች በዳዊት ጀግኖችና ኃያላን መካከል ተጠቅሰዋል (2 ሳሙኤል 23 እና 1 ዜና መዋዕል 11)። በመጀመሪያ በታላላቅ ተግባራቸው ራሳቸውን አሳይተዋል፣ ከዚያም ወደ እነዚህ ታላላቅ ቦታዎች ከፍ ከፍ አሉ። ክብር ብቃትን ሲከተል ለመንግሥት መልካም ነው። በናያ እዚህ ላይ በቁጥር 5 ላይ “ዋና ካህን” ተብሎ ተጠርቷል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG የእስራኤልም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆችና የሺህ አለቆች የመቶ አለቆችም በክፍሎች ነገር ሁሉ ንጉሡን ያገለገሉትም ሹማምት እንደ ቍጥራቸው እነዚህ ነበሩ። እነዚህም ክፍሎች እያንዳንዳቸው ሀ… አማርኛ ENGNIV This is the list of the Israelites–heads of families, commanders of thousands and commanders of hundreds, and their off… English BCV ደቂ እስራኤል ድማ ኸምዙይ ኮይኖም ተሰሪዖም ነበሩ፦ ዋናታት ማይ ቤት ኣቦታትን ኣሕሉቕ ኣሽሓትን ኣሕሉቕ ሚእትታትን፥ እቶም ብዅሉ ናይ ክፍልታት ሰራዊት ንንጉስ ዘገልግልዎ መኳንንቶምን ኮይኖ… ትግርኛ GAZBIB Israa'eloonni mana mana abbaa isaaniitti dura-buutota ta'an, angafoonni kumaa, angafoonni dhibbaa, warri isaan gamteess… Afaan Oromoo BCV GIZ ወደቂቀ እስራኤልኒ በከመ ኈልቆሙ ለመላእክተ ቤተ አበዊሆሙ ርኡሳነ እልፍ ወርኡሳነ ምእት ወጸሐፍት እለ ይትቀነዩ ወይትለአኩ በቅድመ ሕዝብ ወላዕለ ኵሉ ትእዛዘ ንጉሥ በከመ ኵሉ ክፍለት በኵሉ… giz GAZGAZ Israa'eloonni mana mana abbaa isaaniitti dura-buutota ta'an, angafoonni kumaa, angafoonni dhibbaa, warri isaan gamteess… Afaan Oromoo BCV aksum ደቂ እስራኤል ድማ ኸምዙይ ኮይኖም ተሰሪዖም ነበሩ፦ ዋናታት ማይ ቤት ኣቦታትን ኣሕሉቕ ኣሽሓትን ኣሕሉቕ ሚእትታትን፥ እቶም ብዅሉ ናይ ክፍልታት ሰራዊት ንንጉስ ዘገልግልዎ መኳንንቶምን ኮይኖ… ትግርኛ SWAHSUV Basi wana wa Israeli kwa hesabu yao, wakuu wa mbari za mababa, na maakida wa maelfu na wa mamia, na wasimamizi wao wali… Kiswahili