1አዳም፣ ሴት፣ ሄኖስ፣
2ቃይናን፣ መላልኤል፣ ያሬድ፣
3ሄኖክ፣ ማቱሳላ፣ ላሜሕ፣ ኖኅ።
4የኖኅ ወንዶች ልጆች፤ ሴም፣ ካም፣ ያፌት።
5የያፌት ወንዶች ልጆች፤ ጋሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሞሳሕ፣ ቴራስ።
6የጋሜር ወንዶች ልጆች፤ አስከናዝ፣ ሪፋት፣ ቴርጋማ።
7የያዋን ወንዶች ልጆች፤ ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም፣ ሮድኢ።
8የካም ወንዶች ልጆች፤ ኩሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥ፣ ከነዓን።
9የኩሽ ወንዶች ልጆች፤ ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማ፣ ሰብቃታ። የራዕማ ወንዶች ልጆች፤ ሳባ፣ ድዳን።
10ኩሽ ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ላይ የመጀመሪያው ኀያል ጦረኛ ሆነ።
11ምጽራይም የሉዲማውያን፣ የዐናማውያን፣ የላህባማውያን፣ የነፍተሂማውያን፣
12የፈትሩሲማውያን፣ የፍልስጥኤማውያን ቅድመ አባቶች የሆኑት የከስሉሂማውያንና የከፍቶሪማውያን ነገዶች አባት ነው።
13ከነዓን የበኵር ልጁ የሆነው የሲዶን እንዲሁም የኬጢያውያን፣
14የኢያቡሳውያን፣ የአሞራውያን፣ የጌርጌሳውያን፣
15የኤዊያውያን፣ የዐርካውያን፣ የሲኒውያን፣
16የአራዴዎያውያን፣ የሰማርያውያን፣ የአማቲያውያን አባት ነው።
17የሴም ወንዶች ልጆች፤ ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም። የአራም ወንዶች ልጆች፤ ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሳሕ።
18አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤ ሳላም ዔቦርን ወለደ።
19ዔቦር ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ፤ በዘመኑ ምድር ስለተከፈለች፣ የአንደኛው ስም ፋሌቅ ተብሎ ተጠራ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ።
20ዮቅጣንም፡ አልሞዳድን፣ ሣሌፍን፣ ሐስረሞትን፣ ያራሕን፣
21ሀዶራምን፣ አውዛልን፣ ደቅላን፣
22ዖባልን፣ አቢማኤልን፣ ሳባን፣
23ኦፊርን፣ ኤውላጥን፣ ዮባብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ወንዶች ልጆች ናቸው።
24ሴም፣ አርፋክስድ፣ ሳለ፣
25ዔቦር፣ ፋሌቅ፣ ራግው፣
26ሴሮሕ፣ ናኮር፣ ታራ፣
27እንዲሁም በኋላ አብርሃም የተባለው አብራም።
28የአብርሃም ወንዶች ልጆች፤ ይስሐቅ፣ እስማኤል።
29የእነዚህ ዘሮች የሚከተሉት ናቸው፤ የእስማኤል በኵር ልጅ ነባዮት፣ ቄዳር፣ ነብዳኤል፣ መብሳም፣
30ማስማዕ፣ ዱማ፣ ማሣ፣ ኩዳን፣ ቴማን፣
31ኢጡር፣ ናፌስ፣ ቄድማ፤ እነዚህ የእስማኤል ወንዶች ልጆች ናቸው።
32የአብርሃም ቁባት ኬጡራ የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ዘምራን፣ ዮቅሳን፣ ሜዳን፣ ምድያም፣ የስቦቅና፣ ስዌሕ ናቸው። የዮቅሳን ወንዶች ልጆች፤ ሳባ፣ ድዳን።
33የምድያም ወንዶች ልጆች፤ ጌፌር፣ ዔፌር፣ ሄኖኅ፣ አቢዳዕ፣ ኤልዳዓ፤ እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ዘሮች ናቸው።
34አብርሃም ይስሐቅን ወለደ። የይስሐቅ ወንዶች ልጆች፤ ዔሳው፣ እስራኤል።
35የዔሳው ወንዶች ልጆች፤ ኤልፋዝ፣ ራጉኤል፣ የዑስ፣ የዕላም፣ ቆሬ።
36የኤልፋዝ ወንዶች ልጆች፤ ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶም፣ ቄኔዝ፣ ቲምናዕ፣ አማሌቅ።
37የራጉኤል ወንዶች ልጆች፤ ናሖት፣ ዛራ፣ ሣማ፣ ሚዛህ።
38የሴይር ወንዶች ልጆች፤ ሎጣን፣ ሦባል፣ ጽብዖን፣ ዓና፣ ዲሶን፣ ኤጽር፣ ዲሳን።
39የሎጣን ወንዶች ልጆች፤ ሖሪ፣ ሄማም፤ ቲሞናዕ የሎጣን እኅት ነበረች።
40የሦባል ወንዶች ልጆች፤ ዓልዋን፣ ማኔሐት፣ ዔባል፣ ስፎ፣ አውናም። የጽብዖን ወንዶች ልጆች፤ አያ፣ ዓና።
41የዓና ወንድ ልጅ፤ ዲሶን። የዲሶን ወንዶች ልጆች፤ ሔምዳን፣ ኤስባን፣ ይትራን፣ ክራን።
42የኤጽር ወንዶች ልጆች፤ ቢልሐን፣ ዛዕዋን፣ ዓቃን። የዲሳን ወንዶች ልጆች፤ ዑፅ፣ አራን።
43በእስራኤል አንድም ንጉሥ ገና ሳይነግሥ በኤዶም ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ የቢዖር ልጅ ባላቅ፤ ከተማዪቱም ዲንሃባ ትባል ነበር።
44ባላቅ ሲሞትም የባሶራ ሰው የሆነው የዛራ ልጅ ኢዮባብ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
45ኢዮባብ ሲሞት የቴማን አገር ሰው የሆነው ሑሳም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
46ሑሳም ሲሞት በሞዓብ ምድር ምድያምን ድል ያደረገው የባዳድ ልጅ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። የከተማዪቱም ስም ዓዊት ተባለ።
47ሃዳድም ሲሞት የመሥሬቃ ሰው የሆነው ሠምላ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
48ሠምላም ሲሞት በወንዙ አጠገብ ያለችው የረሚቦት ሰው የሆነው ሳኡል በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
49ሳኡልም ሲሞት የዓክቦር ልጅ የሆነው በኣልሐናንም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
50በኣልሐናን ሲሞት ሀዳድ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። ከተማውም ፋዑ ትባል ነበር፤ ሚስቱ መሄጣብኤል ትባላለች፤ እርሷም የሜዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ ነበረች።
51ሀዳድም ሞተ። ዋና ዋናዎቹ የኤዶም ሕዝብ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ቲምናዕ፣ ዓልዋ፣ የቴት፣
52አህሊባማ፣ ኤላ፣ ፊኖን፣
53ቄኔዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣
54መግዲኤል፣ ዒራም። እነዚህ የኤዶም አለቆች ነበሩ።