ደጉ ሳምራዊ
13 ቁጥሮችአማርኛሉቃ 10:25-37
25እነሆም፥ አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው ተነሥቶ፦ “መምህር ሆይ፥ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ?” አለው።
26እርሱም፦ “በሕግ የተጻፈው ምንድር ነው? እንዴትስ ታነባለህ?” አለው።
27እርሱም መልሶ፦ “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም ኃይልህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ፡” አለው።
28ኢየሱስም፦ “እውነት መለስህ፤ ይህን አድርግ በሕይወትም ትኖራለህ፡” አለው።
29እርሱ ግን ራሱን ሊያጸድቅ ወድዶ ኢየሱስን፦ “ባልንጀራዬስ ማን ነው?” አለው።
30ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፦ “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ፤ እነርሱም ደግሞ ገፈፉት ደበደቡትም በሕይወትና በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ።
31ድንገትም አንድ ካህን በዚያ መንገድ ወረደ አይቶትም ገለል ብሎ አለፈ።
32“እንዲሁም ደግሞ አንድ ሌዋዊ ወደዚያ ስፍራ መጣና አይቶት ገለል ብሎ አለፈ።
33አንድ ሳምራዊ ግን ሲሄድ ወደ እርሱ መጣ አይቶትም አዘነለት፥
34“ቀርቦም ዘይትና የወይን ጠጅ በቍስሎቹ ላይ አፍስሶ አሰራቸው፥ በራሱ አህያም ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች ማደርያ ወሰደው ጠበቀውም።
35በማግሥቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለባለቤቱ ሰጠና፦ ‘ጠብቀው፥ ከዚህም በላይ የምትከስረውን ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ’ አለው።
36“እንግዲህ ከነዚህ ከሦስቱ በወንበዴዎች እጅ ለወደቀው ባልንጀራ የሆነው ማንኛው ይመስልሃል?”
37እርሱም፦ “ምሕረት ያደረገለት” አለ። ኢየሱስም፦ “ሂድ አንተም እንዲሁ አድርግ” አለው።