ትንቢተ ዘካርያስ 1

AMHNIVአማርኛ21 ጥቅሶች4:41 አዳምጥ
አዳምጥ 4:41 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት በስምንተኛው ወር የእግዚአብሔር ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፤

2“እግዚአብሔር በአባቶቻችሁ ላይ እጅግ ተቈጥቶ ነበር፤

3ስለዚህ ለሕዝቡ ንገር፤ እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ ‘ወደ እኔ ተመለሱ’ ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት፤ “እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፤’ ይላል፤ እግዚአብሔር ጸባኦት፤

4የቀደሙት ነቢያት፣ ‘እግዚአብሔር ጸባኦት፣ “ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ’ ይላል በማለት ለአባቶቻችሁ ሰብከው ነበር፤ እነርሱ ግን አልሰሙም፤ እኔንም አላደመጡም፤ እንደ እነርሱ አትሁኑ፤ ይላል እግዚአብሔር።

5አባቶቻችሁ አሁን የት አሉ? ነቢያትስ ለዘላለም በሕይወት ይኖራሉን?

6ለባሪያዎቼ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃልና ሥርዐት በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሰምን? “እነርሱም ንስሓ ገብተው፤ እንዲህ አሉ፤ ‘እግዚአብሔር ጸባኦት በወሰነው መሠረት፣ ለሥራችንና ለመንገዳችን የሚገባውን አድርጎብናል።’ ”

7ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ ሳባጥ በሚባለው በዐሥራ አንደኛው ወር በሃያ አራተኛው ቀን፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፤

8በምሽት ራእይ አየሁ፤ እዚያም በፊቴ አንድ ሰው በመጋላ ፈረስ ላይ ተቀምጦአል፤ እርሱም በሸለቆ ውስጥ በባርሰነት ዛፎች መካከልም ቆሞ ነበር፤ ከበስተ ኋላውም መጋላ፣ ሐመርና አንባላይ ፈረሶች ነበሩ።

9እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁ። ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክም፣ “እነዚህ ምን እንደሆኑ አሳይሃለሁ” አለኝ።

10ከዚያም በባርሰነት ዛፎች መካከል የቆመው ሰው፣ “እነዚህ በምድር ሁሉ እንዲመላለሱ እግዚአብሔር የላካቸው ናቸው” ሲል መለሰ።

11እነርሱም በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆሞ ለነበረው የእግዚአብሔር መልአክ፣ “በምድር ሁሉ ተመላለስን፤ መላዋ ምድርም ዐርፋ በሰላም ተቀምጣለች” ብለው መለሱለት።

12ከዚያም የእግዚአብሔር መልአክ፣ “እግዚአብሔር ጸባኦት ሆይ፤ በእነዚህ ሰባ ዓመታት ውስጥ የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው?” አለ።

13እግዚአብሔርም ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ ደስ በሚያሰኝና በሚያጽናና ቃል መለሰለት።

14ከዚያም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ፤ “ይህን ቃል ተናገር፤ እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ ‘ስለ ጽዮንና ስለ ኢየሩሳሌም እጅግ ቀንቻለሁ፤

15ሰላም አለ በሚሉ አሕዛብ ላይ ግን በጣም ተቈጥቻለሁ፤ በመጠኑ ተቈጥቼ ሳለሁ፣ እነርሱ ግን ጥፋቱ እንዲብስ አደረጉ።’

16“ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በምሕረት ወደ ኢየሩሳሌም እመለሳለሁ፤ በዚያም ቤቴ እንደ ገና ይሠራል፤ መለኪያ ገመድም በኢየሩሳሌም ላይ ይዘረጋል’ ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።

17“ቀጥለህም እንዲህ እያልህ ስበክ፤ እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ ‘ከተሞቼ እንደ ገና ብልጽግና ይትረፈረፍባቸዋል፤ እግዚአብሔርም እንደ ገና ጽዮንን ያጽናናል፤ ኢየሩሳሌምንም ይመርጣል።’ ”

18ከዚያም ወደ ላይ ተመለከትሁ፤ ከፊቴም አራት ቀንዶችን አየሁ፤

19ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረውንም መልአክ፣ “እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁት። እርሱም፣ “እነዚህ ይሁዳን፣ እስራኤልንና ኢየሩሳሌምን የበታተኑ ቀንዶች ናቸው” አለኝ።

20ከዚያም እግዚአብሔር አራት የእጅ ሙያተኞችን አሳየኝ።

21እኔም፣ “እነዚህስ ምን ሊያደርጉ መጡ?” አልሁ። እርሱም፣ “እነዚህ ቀንዶች ማንም ራሱን ቀና ማድረግ እንዳይችል ይሁዳን የበታተኑ ናቸው፤ እነዚህ የእጅ ሙያተኞች ግን የመጡት እነርሱን ሊያስደነግጧቸው፣ ሕዝቡን ለመበታተን በይሁዳ ምድር ላይ ቀንዳቸውን ያነሡትን የእነዚህን የአሕዛብ ቀንዶች ሰብሮ ለመጣል ነው” አለኝ።

ማብራሪያ

1:1-6 የእግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ኃይልና ሉዓላዊ ግዛት ኃጢአተኞችን ንስሐ ገብተው ወደ እርሱ እንዲመለሱ ሊያሳስብና ሊያበረታታ ይገባል። የሠራዊት ጌታ ወዳጃችን እንዲሆን እጅግ የሚናፈቅ ነው፤ ጠላታችን እንዲሆን ግን እጅግ የሚያስፈራ ነው። ያለፈውን እንገመግም፥ እግዚአብሔር በባሪያዎቹ በነቢያት አማካይነት ለአባቶቻችሁ የላከውን መልእክት እናስተውል። አሁን ከክፉ መንገዶቻችሁና ከክፉ ሥራዎቻችሁ ተመለሱ። ኃጢአቶቻችሁን እንድትተዉ ተገፋፉ፤ ይህም የሚመጣውን ጥፋት ለመከላከል ብቸኛው መንገድ ነው።

አባቶቻችን ምን ሆኑ? ለእነርሱ የሰበኩላቸውስ ነቢያት? ሁሉም ሞተው አልፈዋል። እነርሱ እዚህ ነበሩ፥ እኛ በምንኖርባቸው ከተሞችና አገሮች ውስጥ፥ በአንድ ጎዳና ላይ ሲመላለሱ፥ በአንድ ቤቶች ውስጥ ሲኖሩ፥ በአንድ ሱቆችና የንግድ ስፍራዎች ውስጥ ሲነግዱ፥ በአንድ ስፍራ እግዚአብሔርን ሲያመልኩ። ግን ወዴት አሉ? ሲሞቱ አላበቁም ነበር፤ እነርሱ በዘላለም፥ በመንፈሳውያን ዓለም፥ በምንፈጥንበት የማይለወጥ ዓለም ውስጥ ናቸው። ወዴት አሉ? ከእነርሱ መካከል በኃጢአት ኖረው የሞቱት በሥቃይ ውስጥ ናቸው። በክርስቶስ ኖረው የሞቱት ግን በሰማይ ናቸው፤ እኛም እንደ እነርሱ ብንኖርና ብንሞት በቅርብ ጊዜና ለዘላለም ከእነርሱ ጋር እንሆናለን። እነርሱ የራሳቸውን ነፍስ ካልተጠነቀቁ፥ ይህስ ዘሮቻቸውም የራሳቸውን ነፍስ እንዲያጠፉ ምክንያት ይሆናልን?

ነቢያት አልፈዋል፤ ክርስቶስ ግን ለዘላለም የሚኖር ነቢይ ነው፤ ሁሉም ሌሎች ነቢያት ግን ለአገልግሎታቸው የተወሰነ ጊዜ ተደርጎላቸዋል። ወይ ይህ ግንዛቤ ተገቢውን ክብደት ቢሰጠው! የሚሞቱ አገልጋዮች ከሚሞቱ ሰዎች ጋር ስለማይሞቱ ነፍሶቻቸውና ሁለቱም በጫፉ ላይ ስለቆሙበት አስፈሪ ዘላለም እየተነጋገሩ መሆናቸውን። በሌላው ዓለም እኛም ነቢያቶቻችንም ለዘላለም እንኖራለን፤ ለዚያ ዓለም መዘጋጀት በዚህ ዓለም ታላቅ ግድየታችን መሆን አለበት።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስምንተኛው ወር የእግዚአብሔር ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ አማርኛ ENGNIV In the eighth month of the second year of Darius, the word of the Lord came to the prophet Zechariah son of Berekiah, t… English BCV ዳርዮስ ምስ ነገሰ፥ ኣብ ካልኣይ ዓመቱ፥ በታ ሻምነይቲ ወርሒ፥ ናብ ወዲ ኣዶ፥ ወዲ በራክዩ ነቢይ ዘካርያስ፥ ከምዙይ ዝብል ቃል እግዚኣብሄር መፀ። ትግርኛ GAZBIB Daariyos mo'ee waggaa lammaffaa isaatti, waggichattiis ji'a saddeettaffaatti dubbiin Waaqayyoo gara Zakaariyaas raajich… Afaan Oromoo BCV GIZ ወበካልእ ዓመተ መንግሥቱ ለዳርዮስ በሳምን ወርኅ ኮነ ቃለ እግዚአብሔር ኀበ ዘካርያስ ወልደ በራኪዩ ወልደ ሐዶ ነቢይ ወይቤሎ፦ giz GAZGAZ Daariyos mo'ee waggaa lammaffaa isaatti, waggichattiis ji'a saddeettaffaatti dubbiin Waaqayyoo gara Zakaariyaas raajich… Afaan Oromoo BCV aksum ዳርዮስ ምስ ነገሰ፥ ኣብ ካልኣይ ዓመቱ፥ በታ ሻምነይቲ ወርሒ፥ ናብ ወዲ ኣዶ፥ ወዲ በራክዩ ነቢይ ዘካርያስ፥ ከምዙይ ዝብል ቃል እግዚኣብሄር መፀ። ትግርኛ SWAHSUV Katika mwezi wa nane, mwaka wa pili wa Dario, neno la Bwana lilimjia Zekaria, mwana wa Berekia, mwana wa Ido, nabii, ku… Kiswahili