ትንቢተ ዘካርያስ 1

AMHEVGአማርኛ21 ጥቅሶች4:10 አዳምጥ
አዳምጥ 4:10 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስምንተኛው ወር የእግዚአብሔር ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፦

2“እግዚአብሔር በአባቶቻችሁ ላይ እጅግ ተቈጥቶ ነበር።

3ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ወደ እኔ ተመለሱ፥’ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ‘እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥’ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

4የቀደሙት ነቢያት ለአባቶቻችሁ እንዲህ ብለው ሰብከዋል፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፤’ እነርሱ ግን አልሰሙም፥ እኔንም አላደመጡም፤ እንደ እነርሱ አትሁኑ፥ ይላል እግዚአብሔር።

5አባቶቻችሁ ወዴት ናቸው? ነቢያትስ ለዘላለም በሕይወት ይኖራሉን?

6“ለባሪያዎቼስ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? እነርሱም ተመልሰው፦ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ያደርግብን ዘንድ እንዳሰበ እንዲሁ አድርጎብናል፡’ አሉ።”

7በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት ሳባጥ በሚባል በአሥራ አንደኛው ወር በሀያ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፦

8እነሆም፥ አንድ ሰው በመጋላ ፈረስ ተቀምጦ በሌሊት አየሁ፥ እርሱም በሸለቆው ውስጥ ባሉ በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆሞ ነበር፤ በስተ ኋላውም መጋላና ሐመር አንባላይም ፈረሶች ነበሩ።

9እኔም፦ “ጌታዬ ሆይ፥ እነዚህ ምንድር ናቸው?” አልሁ። ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ፦ “እነዚህ ምን እንደ ሆኑ አሳይሃለሁ፡” አለኝ።

10በባርሰነት ዛፎች መካከልም ቆሞ የነበረው ሰው፦ “እነዚህ በምድር ላይ ይመላለሱ ዘንድ እግዚአብሔር የላካቸው ናቸው፡” ብሎ መለሰ።

11በባርሰነት ዛፎች መካከልም ቆሞ የነበረውን የእግዚአብሔርን መልአክ፦ “በምድር ላይ ተመላለስን፥ እነሆም፥ ምድር ሁሉ ዝም ብላ ዐርፋ ተቀምጣለች፡” ብለው መለሱለት።

12የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ፦ “አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው?” አለ።

13እግዚአብሔርም መልሶ ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው።

14ስለዚህም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ፦ “ስበክ፥ እንዲህም በል፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘እኔ በታላቅ ቅንዓት በኢየሩሳሌምና በጽዮን ቀንቻለሁ።

15እኔ ጥቂት ብቻ ተቈጥቼ ሳለሁ እነርሱ ክፋትን ስላገዙት፥ ባልተቸገሩት አሕዛብ ላይ እጅግ ተቈጥቻለሁ።’

16“‘ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ኢየሩሳሌም በምሕረት ተመልሻለሁ፤ ቤቴ ይሠራባታል፤ በኢየሩሳሌምም ላይ ገመድ ይዘረጋበታል፥’ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

17ደግሞም እንዲህ ስትል ስበክ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ከተሞቼ ደግሞ በበጎ ነገር ይረካሉ፤ እግዚአብሔርም ደግሞ ጽዮንን ያጽናናል፥ ኢየሩሳሌምንም ደግሞ ይመርጣል’።”

18ዓይኖቼንም አንሥቼ እነሆ፥ አራት ቀንዶች አየሁ።

19ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረውን መልአክ፦ “እነዚህ ምንድር ናቸው?” አልሁት። እርሱም፦ “እነዚህ ይሁዳንና እስራኤልን ኢየሩሳሌምንም የበተኑ ቀንዶች ናቸው፡” ብሎ መለሰልኝ።

20እግዚአብሔርም አራት ጠራቢዎች አሳየኝ።

21እኔም፦ “እነዚህ የመጡት ምን ሊሠሩ ነው?” አልሁ። እርሱም፦ “አንድ ሰው ራሱን እስከማያነሣ ድረስ እነዚህ ቀንዶች ይሁዳን የበተኑ ናቸው፤ እነዚህ ግን ሊያስፈራሩአቸው፥ የይሁዳንም አገር ይበትኑ ዘንድ ቀንዳቸውን ያነሡትን የአሕዛብን ቀንዶች ሊጥሉ መጥተዋል፡” ብሎ ተናገረ።

ማብራሪያ

1:1-6 የእግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ኃይልና ሉዓላዊ ግዛት ኃጢአተኞችን ንስሐ ገብተው ወደ እርሱ እንዲመለሱ ሊያሳስብና ሊያበረታታ ይገባል። የሠራዊት ጌታ ወዳጃችን እንዲሆን እጅግ የሚናፈቅ ነው፤ ጠላታችን እንዲሆን ግን እጅግ የሚያስፈራ ነው። ያለፈውን እንገመግም፥ እግዚአብሔር በባሪያዎቹ በነቢያት አማካይነት ለአባቶቻችሁ የላከውን መልእክት እናስተውል። አሁን ከክፉ መንገዶቻችሁና ከክፉ ሥራዎቻችሁ ተመለሱ። ኃጢአቶቻችሁን እንድትተዉ ተገፋፉ፤ ይህም የሚመጣውን ጥፋት ለመከላከል ብቸኛው መንገድ ነው።

አባቶቻችን ምን ሆኑ? ለእነርሱ የሰበኩላቸውስ ነቢያት? ሁሉም ሞተው አልፈዋል። እነርሱ እዚህ ነበሩ፥ እኛ በምንኖርባቸው ከተሞችና አገሮች ውስጥ፥ በአንድ ጎዳና ላይ ሲመላለሱ፥ በአንድ ቤቶች ውስጥ ሲኖሩ፥ በአንድ ሱቆችና የንግድ ስፍራዎች ውስጥ ሲነግዱ፥ በአንድ ስፍራ እግዚአብሔርን ሲያመልኩ። ግን ወዴት አሉ? ሲሞቱ አላበቁም ነበር፤ እነርሱ በዘላለም፥ በመንፈሳውያን ዓለም፥ በምንፈጥንበት የማይለወጥ ዓለም ውስጥ ናቸው። ወዴት አሉ? ከእነርሱ መካከል በኃጢአት ኖረው የሞቱት በሥቃይ ውስጥ ናቸው። በክርስቶስ ኖረው የሞቱት ግን በሰማይ ናቸው፤ እኛም እንደ እነርሱ ብንኖርና ብንሞት በቅርብ ጊዜና ለዘላለም ከእነርሱ ጋር እንሆናለን። እነርሱ የራሳቸውን ነፍስ ካልተጠነቀቁ፥ ይህስ ዘሮቻቸውም የራሳቸውን ነፍስ እንዲያጠፉ ምክንያት ይሆናልን?

ነቢያት አልፈዋል፤ ክርስቶስ ግን ለዘላለም የሚኖር ነቢይ ነው፤ ሁሉም ሌሎች ነቢያት ግን ለአገልግሎታቸው የተወሰነ ጊዜ ተደርጎላቸዋል። ወይ ይህ ግንዛቤ ተገቢውን ክብደት ቢሰጠው! የሚሞቱ አገልጋዮች ከሚሞቱ ሰዎች ጋር ስለማይሞቱ ነፍሶቻቸውና ሁለቱም በጫፉ ላይ ስለቆሙበት አስፈሪ ዘላለም እየተነጋገሩ መሆናቸውን። በሌላው ዓለም እኛም ነቢያቶቻችንም ለዘላለም እንኖራለን፤ ለዚያ ዓለም መዘጋጀት በዚህ ዓለም ታላቅ ግድየታችን መሆን አለበት።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV In the eighth month of the second year of Darius, the word of the Lord came to the prophet Zechariah son of Berekiah, t… English BCV ዳርዮስ ምስ ነገሰ፥ ኣብ ካልኣይ ዓመቱ፥ በታ ሻምነይቲ ወርሒ፥ ናብ ወዲ ኣዶ፥ ወዲ በራክዩ ነቢይ ዘካርያስ፥ ከምዙይ ዝብል ቃል እግዚኣብሄር መፀ። ትግርኛ GAZBIB Daariyos mo'ee waggaa lammaffaa isaatti, waggichattiis ji'a saddeettaffaatti dubbiin Waaqayyoo gara Zakaariyaas raajich… Afaan Oromoo BCV GIZ ወበካልእ ዓመተ መንግሥቱ ለዳርዮስ በሳምን ወርኅ ኮነ ቃለ እግዚአብሔር ኀበ ዘካርያስ ወልደ በራኪዩ ወልደ ሐዶ ነቢይ ወይቤሎ፦ giz GAZGAZ Daariyos mo'ee waggaa lammaffaa isaatti, waggichattiis ji'a saddeettaffaatti dubbiin Waaqayyoo gara Zakaariyaas raajich… Afaan Oromoo BCV aksum ዳርዮስ ምስ ነገሰ፥ ኣብ ካልኣይ ዓመቱ፥ በታ ሻምነይቲ ወርሒ፥ ናብ ወዲ ኣዶ፥ ወዲ በራክዩ ነቢይ ዘካርያስ፥ ከምዙይ ዝብል ቃል እግዚኣብሄር መፀ። ትግርኛ AMHNIV ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት በስምንተኛው ወር የእግዚአብሔር ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፤ አማርኛ SWAHSUV Katika mwezi wa nane, mwaka wa pili wa Dario, neno la Bwana lilimjia Zekaria, mwana wa Berekia, mwana wa Ido, nabii, ku… Kiswahili