ራእይ ዮሃንስ 7

AMHNIVአማርኛ17 ጥቅሶች3:24 አዳምጥ
አዳምጥ 3:24 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከዚህ በኋላ አራት መላእክት በአራቱ የምድር ማእዘኖች ቆመው አየሁ፤ እነርሱም ነፋስ በምድር ወይም በባሕር፣ ወይም በማንኛውም ዛፍ ላይ እንዳይነፍስ አራቱን የምድር ነፋሶች ያዙ።

2ከዚያም የሕያው አምላክ ማኅተም ያለው ሌላ መልአክ ከምሥራቅ ሲመጣ አየሁ፤ እርሱም ምድርንና ባሕርን ለመጒዳት ሥልጣን የተሰጣቸውን አራቱን መላእክት በታላቅ ድምፅ እንዲህ አላቸው፤

3“በአምላካችን አገልጋዮች ግንባር ላይ ማኅተም እስከምናደርግባቸው ድረስ ምድርን ወይም ባሕርን፣ ወይም ዛፎችን አትጒዱ።”

4የታተሙትንም ቊጥር ሰማሁ፤ እነርሱም ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ፤

5ከይሁዳ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣ ከሮቤል ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣ ከጋድ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣

6ከአሴር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣ ከንፍታሌም ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣ ከምናሴ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣

7ከስምዖን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣ ከሌዊ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣ ከይሳኮር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣

8ከዛብሎን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣ ከዮሴፍ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣ ከብንያም ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ ታተሙ።

9ከዚህም በኋላ አየሁ፤ እነሆ፤ በዙፋኑና በበጉ ፊት ማንም ሊቈጥራቸው የማይችል ከሕዝብ፣ ከነገድ፣ ከወገን፣ ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሕዝብ ቆመው ነበር፤ እነርሱም ነጭ ልብስ ለብሰው፣ የዘንባባ ዝንጣፊ በእጃቸው ይዘው ነበር።

10በታላቅ ድምፅም እንዲህ ብለው ጮኹ፤ “ማዳን በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው፣ የአምላካችንና የበጉ ነው።”

11መላእክቱም ሁሉ በዙፋኑና በሽማግሌዎቹ፣ በአራቱም ሕያዋን ፍጡራን ዙሪያ ቆመው ነበር፤ በዙፋኑ ፊት በግንባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤

12እንዲህም ይሉ ነበር፤ “አሜን፤ ውዳሴና ክብር፣ ጥበብ፣ ምስጋናና፣ ሞገስ፣ ኀይልና ብርታትም፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ለአምላካችን ይሁን፤ አሜን።”

13ከዚያም ከሽማግሌዎቹ አንዱ፣ “እነዚህ ነጭ ልብስ የለበሱት እነማን ናቸው? ከወዴትስ መጡ?” አለኝ።

14እኔም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንተ ታውቃለህ” አልሁት። እርሱም እንዲህ አለኝ፤ እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም በበጉ ደም አጥበው “አንጽተዋል።

15ስለዚህ፣ “በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ሆነው፣ ቀንና ሌሊት በመቅደሱ ያገለግሉታል፤ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው ድንኳኑን በላያቸው ይዘረጋል፤

16ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም፤ ከዚህም በኋላ አይጠሙም፤ ፀሓይ አይመታቸውም፤ ሐሩሩም ሁሉ አያቃጥላቸውም፤

17ምክንያቱም በዙፋኑ መካከል ያለው በግ እረኛቸው ይሆናል፤ ወደ ሕይወት ውሃ ምንጭም ይመራቸዋል፤ እግዚአብሔር እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል።”

ማብራሪያ

7:1-8 በመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌያዊ አነጋገር፣ የአራቱ ነፋሳት በአንድነት መነፋት፣ አስፈሪና አጠቃላይ የሆነ ጥፋትን ያመለክታል። ይሁን እንጂ ጥፋቱ ዘግይቷል። ማኅተሞች ለእያንዳንዱ ሰው የራሱን ንብረት ለማመልከት ያገለግሉ ነበር። ይህ ምልክት በምእመናን ልብ ውስጥ የታተመ የመንፈስ ቅዱስ ምስክር ነው። ጌታም ሕዝቡ ከመታተማቸው በፊት መከራን እንዲቀበሉ አልፈቀደም፤ ይህም ለሁሉም ዓይነት ግጭቶች እንዲዘጋጁ ነው። እንዲሁም፣ በመንፈስ የታተሙት ሰዎች ማኅተማቸው በግንባራቸው ላይ መሆን አለበት፣ በወዳጆችም በጠላቶችም በግልጽ እንዲታይ፣ ነገር ግን አማኙ ራሱ የአምላክን ቃል መስታወት በትጋት ካልተመለከተ በቀር እንዳያየው። የታተሙት ሰዎች ቁጥር፣ አምላክ ያስቀራቸውን የቀሩትን ሰዎች እንደሚያመለክት ሊታወቅ ይችላል። የአምላክ ቤተ ክርስቲያን ከኃጢአተኛው ዓለም ጋር ሲወዳደር ትንሽ መንጋ ብትሆንም፣ በእውነት ግን ትልቅ ማኅበር ናት፣ እናም ከዚህም በላይ ልትሰፋ ነው። እዚህ ላይ ደግሞ ዓለም አቀፋዊቷ ቤተ ክርስቲያን በእስራኤል ምሳሌ ትገለጻለች።

7:9-12

የክርስቶስ በኵራት ቀድመው መንገድ ሲመሩ፣ ከኋላ የተለወጡት አሕዛብ ይከተላሉ፤ ድነታቸውንም በእልልታ ለእግዚአብሔርና ለቤዛው ያመሰግናሉ። በሃይማኖታዊ አምልኮ ተግባራት ወደ እግዚአብሔር እንቀርባለን፤ በክርስቶስም ልንቀርብ ይገባናል፤ የእግዚአብሔር ዙፋን በአማላጅ ባይሆን ኖሮ በኃጢአተኞች ሊቀረብ ባልቻለም ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ከዚህም በኋላ በአራቱ በምድር ማዕዘን ቆመው አራት መላእክት አየሁ፥ እነርሱም ነፋስ በምድር ቢሆን ወይም በባሕር ወይም በማንም ዛፍ እንዳይነፍስ አራቱን የምድር ነፋሳት ያዙ። አማርኛ ENGNIV After this I saw four angels standing at the four corners of the earth, holding back the four winds of the earth to pre… English BCV ድሕሪዙይ እቶም ኣርባዕተ መላእኽቲ፥ ኣብ ኣርባዕተ መኣዝን ምድሪ ደው ኢሎም ረአኹ። ንሳቶም፥ ኣብ ምድሪ ወይ ኣብ ባሕሪ ወይ ኣብ ዝኾነ ኣእዋም፥ ንፋስ ምእንቲ ኸይነፍስ፥ ነቶም ኣርባዕተ ን… ትግርኛ GAZBIB Kana booddees ergamoonni afur golee lafaa arfan irra dhaabatanii, qilleensi lafatti, galaanatti, mukattis akka hin qill… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእምድኅረ ዝንቱ ርኢኩ አርባዕቱ መላእክት ይቀውሙ ውስተ አርባዕቱ መዓዝኒሃ ለምድር ከመ የአኀዙ ከመ ኢይንፋኅ ነፋስ ውስተ ምድር ወኢውስተ ባሕር ወኢውስተ ዕፀታት። giz GAZGAZ Kana booddees ergamoonni afur golee lafaa arfan irra dhaabatanii, qilleensi lafatti, galaanatti, mukattis akka hin qill… Afaan Oromoo BCV aksum ድሕሪዙይ እቶም ኣርባዕተ መላእኽቲ፥ ኣብ ኣርባዕተ መኣዝን ምድሪ ደው ኢሎም ረአኹ። ንሳቶም፥ ኣብ ምድሪ ወይ ኣብ ባሕሪ ወይ ኣብ ዝኾነ ኣእዋም፥ ንፋስ ምእንቲ ኸይነፍስ፥ ነቶም ኣርባዕተ ን… ትግርኛ SWAHSUV Baada ya hayo nikaona malaika wanne wamesimama katika pembe nne za nchi, wakizizuia pepo nne za nchi, upepo usivume juu… Kiswahili