1እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን፡ እስራኤል እንዲህ ይበል፦
2“እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን፡ ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥
3ቍጣቸውን በላያችን በነደደ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር፤
4በዚያን ጊዜ ውኃ ባሰጠመን ነበር፥ በነፍሳችንም ላይ ፈሳሽ ባለፈ ነበር፤
5በዚያን ጊዜ የጐርፍ ውኃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር።
6ለጥርሳቸው ንክሻ ያላደረገን እግዚአብሔር ይባረክ።
7ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች። ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን።
8ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በሠራ፡ በእግዚአብሔር ስም ነው።”