1የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሆይ፥ አመስግኑት፥ የእግዚአብሔርንም ስም አመስግኑ።
2ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ፡ የእግዚአብሔር ስም ቡሩክ ይሁን።
3ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ፡ የእግዚአብሔር ስም ይመስገን።
4እግዚአብሔር በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍተኛ ነው፥ ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው።
5እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ማን ነው? በላይ የሚኖር፤
6በሰማይና በምድር የተዋረዱትን የሚያይ፤
7ከአለቆች ጋር ከሕዝቡም አለቆች ጋር ያኖረው ዘንድ፡ ችግረኛን ከመሬት የሚያነሣ፥ ምስኪኑንም ከፋንድያ ከፍ ከፍ የሚያደርግ፤
9መካኒቱን በቤት የሚያኖራት፥ ደስ የተሰኘችም የልጆች እናት የሚያደርጋት። ሃሌ ሉያ።