ትንቢተ አብድዩ 1

AMHNIVአማርኛ21 ጥቅሶች4:00 አዳምጥ
አዳምጥ 4:00 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት ሰምተናል፤ መልእክተኛውም ወደ አሕዛብ ተልኮ እንዲህ ብሎአል፤ “ተነሡ፤ እርሷን ለመውጋት እንውጣ።”

2“እነሆ፤ በአሕዛብ መካከል ታናሽ አደርግሃለሁ፤ እጅግ የተናቅህ ትሆናለህ።

3አንተ በሰንጣቃ ዐለት ውስጥ የምትኖር፣ መኖሪያህንም በከፍታ ስፍራ ያደረግህ፣ ለራስህም፣ “ማን ወደ ምድር ሊያወርደኝ ይችላል?” የምትል፣ የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል።

4እንደ ንስር መጥቀህ ወደ ላይ ብትወጣ፣ ጐጆህንም በከዋክብት መካከል ብታደርግ፣ ከዚያ አወርድሃለሁ” ይላል እግዚአብሔር።

5“ሌቦች ወደ አንተ ቢመጡ፣ ዘራፊዎችም በሌሊት ቢገቡ፣ የሚሰርቁት የሚፈልጉትን ያህል ብቻ አይደለምን? ወይን ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡ፣ ጥቂት ቃርሚያ አይተዉምን? አንተ ግን ምንኛ ጥፋት ይጠብቅሃል!

6ዔሳው ግን እንዴት ተዘረፈ? የሸሸገውስ ሀብት ምንኛ ተመዘበረ!

7ወዳጆችህ ሁሉ ወደ ድንበር ይገፉሃል፤ ጓደኞችህ ያታልሉሃል፤ ያሸንፉህማል፤ እንጀራህን የበሉ ወጥመድ ይዘረጉብሃል፤ አንተ ግን አታውቀውም።

8“በዚያ ቀን ጥበበኛ ሰዎችን ከኤዶም፣ አስተዋዮችንም ከዔሳው ተራሮች አልደመስስምን?” ይላል እግዚአብሔር።

9ቴማን ሆይ፤ ተዋጊዎችህ ይደነግጣሉ፤ በዔሳውም ተራሮች ያለ ሁሉ፣ ተገድሎ ይጠፋል።

10በወንድምህ በያዕቆብ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፣ በዕፍረት ትሸፈናለህ፤ ለዘላለምም ትጠፋለህ።

11እንግዶች ሀብቱን ዘርፈው ሲሄዱ፣ ባዕዳንም በበሮቹ ሲገቡ፣ በኢየሩሳሌምም ላይ ዕጣ ሲጣጣሉ፣ በዚያ ቀን ገለልተኛ ሆነህ ተመለከትህ፣ አንተም ከእነርሱ እንደ አንዱ ሆንህ።

12ክፉ ቀን በገጠመው ጊዜ፤ በወንድምህ ሥቃይ መደሰት አልነበረብህም፤ በጥፋታቸው ቀን፣ የይሁዳ ሕዝብ ሲያዝኑ ሐሤት ማድረግ አልነበረብህም፤ በጭንቀታቸውም ቀን፣ በትዕቢት ልትናገር አይገባህም ነበር።

13በጥፋታቸው ቀን፣ በሕዝቤ በር መግባት የለብህም ነበር፤ በጥፋታቸው ቀን፣ በጭንቀታቸው መደሰት አልነበረብህም፤ በጥፋታቸው ቀን፣ ሀብታቸውን መዝረፍ አይገባህም ነበር።

14ስደተኞቻቸውን ለመግደል፣ በመንታ መንገድ መጠባበቅ አይገባህም ነበር፣ በጭንቀታቸው ቀን፣ የተረፉትን አሳልፈህ መስጠት አልነበረብህም።

15“በአሕዛብ ሁሉ ላይ፣ የእግዚአብሔር ቀን ደርሶአል፤ አንተ እንዳደረግኸው፣ በአንተም ላይ ይደረጋል፤ ክፉ ሥራህም በራስህ ላይ ይመለሳል።

16እናንተ በቅዱሱ ተራራዬ እንደ ጠጣችሁ፣ አሕዛብ ሁሉ ዘወትር ይጠጣሉ፤ ይጠጣሉ፤ አብዝተውም ይጠጣሉ፤ ከዚህም በፊት እንዳልሆኑት ይሆናሉ።

17ነገር ግን በጽዮን ተራራ ነጻ መውጣት ይሆናል፤ የያዕቆብ ቤትም እርሷ የተቀደሰች ትሆናለች፤ ርስታቸውን ይወርሳሉ።

18የያዕቆብ ቤት እሳት፣ የዮሴፍም ቤት ነበልባል ይሆናል፤ የዔሳው ቤት ገለባ ይሆናል፤ ያቃጥሉታል፤ ይበሉትማል፤ ከዔሳው ቤት የሚተርፍ፣ አይኖርም።” እግዚአብሔር ተናግሮአል።

19የኔጌብ ሰዎች፣ የዔሳውን ተራራ ይይዛሉ፤ ከተራራው ግርጌ ያሉ ሰዎችም፣ የፍልስጥኤማውያንን ምድር ይወርሳሉ፤ የኤፍሬምንና የሰማርያንም ዕርሻ ይይዛሉ፤ ብንያምም ገለዓድን ይወርሳል።

20በከነዓን ያለው ይህ የእስራኤል ስደተኞች ወገን፣ እስከ ሰራጵታ ያለውን ምድር ይወርሳል፤ በሰፋራድም ያሉ የኢየሩሳሌም ስደተኞች፣ የኔጌብን ከተሞች ይወርሳሉ።

21የዔሳውን ተራሮች ለመግዛት፣ ነጻ አውጪዎች ወደ ጽዮን ተራራ ይወጣሉ፤ መንግሥቱም የእግዚአብሔር ይሆናል።

ማብራሪያ

፩፡፩-፲፮ ይህ ትንቢት በኤዶም ላይ ነው። ጥፋቱ፣ የአባታቸው የዔሳው መገለል እንደነበረው ሁሉ፣ ምሳሌያዊ ይመስላል፤ እንዲሁም የወንጌል ቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ጥፋትንም ያመለክታል። የዚያን ጦርነት የድል ትንቢት ተመልከቱ፤ ኤዶም ይበዘበዛል፣ ይወድቃልም። የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ሁሉ በእነሱ በሚተማመኑባቸው ነገሮች ሁሉ ተስፋ ይቆርጣሉ። እግዚአብሔር ራሳቸውን ከፍ የሚያደርጉና የሚያወድሱትን በቀላሉ ዝቅ ማድረግ ይችላል፤ እርሱም ያደርገዋል። ሥጋዊ መዘናጋት ሰዎችን ለጥፋት ያበስላል፣ ጥፋቱም ሲመጣ የበለጠ ያከፋዋል። በምድር ላይ ያለው ሀብት ሌቦች ሰብረው ገብተው እንዳይሰርቁት አጥብቆ መቀመጥ አይችልም፤ ስለዚህም ለራሳችን በሰማይ ሀብት ማከማቸት ጥበብ ነው። በሥጋ የሚታመኑ ሁሉ በእነርሱ ላይ ያስታጥቁታል። የቃል ኪዳናችን አምላክ ፈጽሞ አያታልለንም፤ ነገር ግን ከእነርሱ ጋር በምንተባበርባቸው ሰዎች ላይ ብንታመን፣ ለእኛ ቁስልና ውርደት ሊሆንብን ይችላል። ከኃጢአት ለመራቅ ማስተዋላቸውን የማይጠቀሙትን ሰዎች፣ ከአደጋ ለመራቅ የሚያስችል ማስተዋልን እግዚአብሔር በጽድቅ ይነፍጋቸዋል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 5

AMHEVG የአብድዩ ራእይ። ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶምያስ እንዲህ ይላል፦ “ከእግዚአብሔር ዘንድ ወሬ ሰምተናል፤ መልእክተኛ ወደ አሕዛብ ተልኮ፦ ተነሡ፥ በላይዋም በሰልፍ እንነሣ፡” ብሎአል። አማርኛ ENGNIV The vision of Obadiah. This is what the Sovereign Lord says about Edom– We have heard a message from the Lord: An envoy… English BCV ኣብድዩ ዝረኣዮ ራእይ። ጐይታ እግዚኣብሄር ብዛዕባ ኤዶምያስ ከምዙይ ይብል፦ ካብ እግዚኣብሄር ወረ ሰሚዕና ኢና፤ እቲ ልኡኽውን ናብ ኣህዛብ ተልኢኹ፥ “ተስኡ፥ ኣብ ልዕሊኣ ብሰልፊ ንለዓል፥ … ትግርኛ GAZBIB Mul'anni Waaqayyo gooftaan waa'ee biyya Edoomiif Obaadiiyaatti mul'ise kanatti fufee jira; ergamaan tokko gara saba biy… Afaan Oromoo BCV GIZ ራእይ ዘርእየ ዓብድዩ፤ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር በእንተ ኤዶምያስ፦ ሰሚዐ ሰማዕኩ እምኀበ እግዚአብሔር ወፈነወ ማዕገተ ላዕለ ሕዝብ ተንሥኡ ወንትነሣእ ላዕሌሃ ወንትቃተላ። giz GAZGAZ Mul'anni Waaqayyo gooftaan waa'ee biyya Edoomiif Obaadiiyaatti mul'ise kanatti fufee jira; ergamaan tokko gara saba biy… Afaan Oromoo BCV aksum ኣብድዩ ዝረኣዮ ራእይ። ጐይታ እግዚኣብሄር ብዛዕባ ኤዶምያስ ከምዙይ ይብል፦ ካብ እግዚኣብሄር ወረ ሰሚዕና ኢና፤ እቲ ልኡኽውን ናብ ኣህዛብ ተልኢኹ፥ “ተስኡ፥ ኣብ ልዕሊኣ ብሰልፊ ንለዓል፥ … ትግርኛ ENGESV The vision of Obadiah. Thus says the Lord GOD concerning Edom: We have heard a report from the LORD, and a messenger ha… English