ትንቢተ አብድዩ 1

AMHEVGአማርኛ21 ጥቅሶች3:47 አዳምጥ
አዳምጥ 3:47 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የአብድዩ ራእይ። ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶምያስ እንዲህ ይላል፦ “ከእግዚአብሔር ዘንድ ወሬ ሰምተናል፤ መልእክተኛ ወደ አሕዛብ ተልኮ፦ ተነሡ፥ በላይዋም በሰልፍ እንነሣ፡” ብሎአል።

2እነሆ፥ በአሕዛብ ዘንድ ታናሽ አድርጌሃለሁ፤ አንተ እጅግ ተንቀሃል።

3በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ የምትኖር፥ ማደሪያህንም ከፍ ከፍ ያደረግህ፥ በልብህም፦ “ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው?” የምትል አንተ ሆይ፥ የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል።

4እንደ ንስር መጥቀህ ብትወጣ፥ ቤትህም በከዋክብት መካከል ቢሆን፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

5ሌቦች ቢመጡብህ ወይም ወንበዴዎች በሌሊት ቢመጡ፥ የሚበቃቸውን የሚሰርቁ አይደሉምን? ወይንንም የሚቈርጡ ወደ አንተ ቢመጡ ቃርሚያ አያስቀሩምን?

6አንተ ግን ምንኛ ጠፋህ! ዔሳው ምንኛ ተመረመረ! የተሸሸገበት ነገር ምንኛ ተፈለገ!

7የተማማልሃቸው ሰዎች ሁሉ ወደ ዳርቻህ ሰደዱህ፤ የታመንሃቸው ሰዎች አታለሉህ፥ አሸነፉህም፤ በበታችህም አሽክላ ዘረጉብህ፥ እነርሱም ማስተዋል የላቸውም።

8በዚያ ቀን ከኤዶምያስ ጥበበኞችን፥ ከዔሳውም ተራራ ማስተዋልን አላጠፋምን? ይላል እግዚአብሔር።

9ቴማን ሆይ፥ ሰዎች ሁሉ ከዔሳው ተራራ በመገደል ይጠፉ ዘንድ ኃያላንህ ይደነግጣሉ።

10በወንድምህ በያዕቆብ ላይ ስለ ተደረገ ግፍ እፍረት ይከድንሃል፥ ለዘላለምም ትጠፋለህ።

11በፊቱ አንጻር በቆምህ ቀን፥ አሕዛብ ጭፍራውን በማረኩበት፥ እንግዶችም በበሩ በገቡበት፥ በኢየሩሳሌምም ዕጣ በተጣጣሉበት ቀን አንተ ደግሞ ከእነርሱ እንደ አንዱ ነበርህ።

12ነገር ግን በመከራው ቀን ወንድምህን ትመለከት ዘንድ፥ በጥፋታቸውም ቀን በይሁዳ ልጆች ላይ ደስ ይልህ ዘንድ፥ በጭንቀትም ቀን በትዕቢት ትናገር ዘንድ አይገባህም ነበር።

13በጥፋታቸውም ቀን በሕዝቤ በር ትገባ ዘንድ፥ በጥፋታቸውም ቀን መከራቸውን ትመለከት ዘንድ፥ በጥፋታቸውም ቀን በሀብታቸው ላይ እጅህን ትዘረጋ ዘንድ አይገባህም ነበር።

14የሸሹትንም ለመግደል በመንታ መንገድ ላይ ትቆም ዘንድ፥ በጭንቀትም ቀን ከእርሱ የቀሩትን አሳልፈህ ትሰጥ ዘንድ አይገባህም ነበር።

15የእግዚአብሔር ቀን በአሕዛብ ሁሉ ላይ ቀርቦአልና፤ አንተ እንዳደረግኸው እንዲሁ ይደረግብሃል፥ ፍዳህም በራስህ ላይ ይመለሳል።

16በቅዱስ ተራራዬ ላይ እንደ ጠጣችሁ እንዲሁ አሕዛብ ሁሉ ዘወትር ይጠጣሉ፤ አዎን ይጠጣሉ፥ ይጨልጡማል፥ እንዳልሆኑም ይሆናሉ።

17ነገር ግን በጽዮን ተራራ ላይ የሚያመልጡ ይሆናሉ፥ እርሱም ቅዱስ ይሆናል፤ የያዕቆብም ቤት ሰዎች ርስታቸውን ይወርሳሉ።

18እግዚአብሔርም ተናግሮአልና የያዕቆብ ቤት እሳት፥ የዮሴፍ ቤት ነበልባልም፥ የዔሳው ቤት ገለባ ይሆናሉ፤ እነርሱንም ያቃጥሉአቸዋል ይበሉአቸውማል፤ ከዔሳውም ቤት ቅሬታ የለውም።

19የደቡብም ሰዎች የዔሳውን ተራራ፥ የቈላውም ሰዎች ፍልስጥዔማውያንን ይወርሳሉ፤ የኤፍሬምንም አገር የሰማርያንም አገር ይወርሳሉ፤ ብንያምም ገለዓድን ይወርሳል።

20ይህም የእስራኤል ልጆች የጭፍራቸው ምርኮ የከነዓንን ስፍራ ሁሉ እስከ ሰራጵታ ድረስ ይወርሳል፤ በስፋራድም የሚኖሩ የኢየሩሳሌም ምርኮኞች የደቡብን ከተሞች ይወርሳሉ።

21በዔሳውም ተራራ ላይ ይፈርዱ ዘንድ አዳኞች ወደ ጽዮን ተራራ ላይ ይወጣሉ፤ መንግሥቱም ለእግዚአብሔር ይሆናል።

ማብራሪያ

፩፡፩-፲፮ ይህ ትንቢት በኤዶም ላይ ነው። ጥፋቱ፣ የአባታቸው የዔሳው መገለል እንደነበረው ሁሉ፣ ምሳሌያዊ ይመስላል፤ እንዲሁም የወንጌል ቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ጥፋትንም ያመለክታል። የዚያን ጦርነት የድል ትንቢት ተመልከቱ፤ ኤዶም ይበዘበዛል፣ ይወድቃልም። የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ሁሉ በእነሱ በሚተማመኑባቸው ነገሮች ሁሉ ተስፋ ይቆርጣሉ። እግዚአብሔር ራሳቸውን ከፍ የሚያደርጉና የሚያወድሱትን በቀላሉ ዝቅ ማድረግ ይችላል፤ እርሱም ያደርገዋል። ሥጋዊ መዘናጋት ሰዎችን ለጥፋት ያበስላል፣ ጥፋቱም ሲመጣ የበለጠ ያከፋዋል። በምድር ላይ ያለው ሀብት ሌቦች ሰብረው ገብተው እንዳይሰርቁት አጥብቆ መቀመጥ አይችልም፤ ስለዚህም ለራሳችን በሰማይ ሀብት ማከማቸት ጥበብ ነው። በሥጋ የሚታመኑ ሁሉ በእነርሱ ላይ ያስታጥቁታል። የቃል ኪዳናችን አምላክ ፈጽሞ አያታልለንም፤ ነገር ግን ከእነርሱ ጋር በምንተባበርባቸው ሰዎች ላይ ብንታመን፣ ለእኛ ቁስልና ውርደት ሊሆንብን ይችላል። ከኃጢአት ለመራቅ ማስተዋላቸውን የማይጠቀሙትን ሰዎች፣ ከአደጋ ለመራቅ የሚያስችል ማስተዋልን እግዚአብሔር በጽድቅ ይነፍጋቸዋል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 5

ENGNIV The vision of Obadiah. This is what the Sovereign Lord says about Edom– We have heard a message from the Lord: An envoy… English BCV ኣብድዩ ዝረኣዮ ራእይ። ጐይታ እግዚኣብሄር ብዛዕባ ኤዶምያስ ከምዙይ ይብል፦ ካብ እግዚኣብሄር ወረ ሰሚዕና ኢና፤ እቲ ልኡኽውን ናብ ኣህዛብ ተልኢኹ፥ “ተስኡ፥ ኣብ ልዕሊኣ ብሰልፊ ንለዓል፥ … ትግርኛ GAZBIB Mul'anni Waaqayyo gooftaan waa'ee biyya Edoomiif Obaadiiyaatti mul'ise kanatti fufee jira; ergamaan tokko gara saba biy… Afaan Oromoo BCV GIZ ራእይ ዘርእየ ዓብድዩ፤ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር በእንተ ኤዶምያስ፦ ሰሚዐ ሰማዕኩ እምኀበ እግዚአብሔር ወፈነወ ማዕገተ ላዕለ ሕዝብ ተንሥኡ ወንትነሣእ ላዕሌሃ ወንትቃተላ። giz GAZGAZ Mul'anni Waaqayyo gooftaan waa'ee biyya Edoomiif Obaadiiyaatti mul'ise kanatti fufee jira; ergamaan tokko gara saba biy… Afaan Oromoo BCV aksum ኣብድዩ ዝረኣዮ ራእይ። ጐይታ እግዚኣብሄር ብዛዕባ ኤዶምያስ ከምዙይ ይብል፦ ካብ እግዚኣብሄር ወረ ሰሚዕና ኢና፤ እቲ ልኡኽውን ናብ ኣህዛብ ተልኢኹ፥ “ተስኡ፥ ኣብ ልዕሊኣ ብሰልፊ ንለዓል፥ … ትግርኛ AMHNIV ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት ሰምተናል፤ መልእክተኛውም ወደ አሕዛብ ተልኮ እንዲህ ብሎአል፤ “ተነሡ፤ እርሷን ለመውጋት እንውጣ።” አማርኛ ENGESV The vision of Obadiah. Thus says the Lord GOD concerning Edom: We have heard a report from the LORD, and a messenger ha… English