የማቴዎስ ወንጌል 25

AMHNIVአማርኛ46 ጥቅሶች6:49 አዳምጥ
አዳምጥ 6:49 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማይ መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ ዐሥር ልጃገረዶችን ትመስላለች።

2ከእነርሱም አምስቱ ልጃገረዶች ዝንጉዎች፣ አምስቱ ደግሞ አስተዋዮች ነበሩ፤

3ዝንጉዎቹ መብራት ይዘው መጠባበቂያ ዘይት አልያዙም ነበር።

4አስተዋዮቹ ግን ከመብራታቸው ጋር መጠባበቂያ ዘይት በማሰሮ ይዘው ነበር።

5ሙሽራው በዘገየ ጊዜ፣ ሁሉም እንቅልፍ ተጫጫናቸውና ተኙ።

6“እኩለ ሌሊት ላይ፣ ‘ሙሽራው እየመጣ ነው፤ ወጥታችሁ ተቀበሉት!’ የሚል ጥሪ ተሰማ።

7“በዚህ ጊዜ ልጃገረዶቹ ሁሉ ተነሥተው መብራቶቻቸውን እየተረኰሱ መዘጋጀት ያዙ።

8ዝንጉዎቹ አስተዋዮቹን፣ ‘መብራታችን ሊጠፋብን ስለ ሆነ፣ ከዘይታችሁ ስጡን’ አሏቸው።

9“አስተዋዮቹ ልጃገረዶች ግን መልሰው፣ ‘ያለን ዘይት ለእኛም ለእናንተም ላይበቃ ስለሚችል፣ ሄዳችሁ ከሻጮች ለራሳችሁ ግዙ’ አሏቸው።

10“ዘይት ሊገዙ እንደሄዱ፣ ሙሽራው መጣ፤ ተዘጋጅተው የነበሩት ልጃገረዶችም ወደ ሰርጉ ግብዣ አብረውት ገቡ፤ በሩም ተዘጋ።

11“ዘግየት ብለው ሌሎቹ ልጃገረዶች መጥተው፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤ በሩን ክፈትልን’ አሉ።

12“እርሱ ግን መልሶ፣ ‘እውነት እላችኋለሁ፣ አላውቃችሁም’ አላቸው።

13“እንግዲህ ቀኑን ወይም ሰዓቱን ስለማታውቁ ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ።

14“የእግዚአብሔር መንግሥት አገልጋዮቹን ጠርቶ ያለውን ንብረት በዐደራ በመስጠት ወደ ሌላ አገር ሊሄድ የተነሣ አንድ ሰውን ትመስላለች፤

15ለእያንዳንዱ እንደ ችሎታው በመደልደል ለአንዱ አምስት ታላንት፣ ለሌላው ሁለት፣ ለሌላው ደግሞ አንድ ታላንት ሰጥቶ ጒዞውን ቀጠለ።

16አምስት ታላንት የተቀበለው ሰውዬ ወዲያው በገንዘቡ ንግድ ጀምሮ አምስት ታላንት አተረፈ፤

17እንዲሁም ሁለት ታላንት የተቀበለው ሁለት አተረፈ፤

18አንድ ታላንት የተቀበለው ግን መሬት ቈፍሮ የጌታውን ገንዘብ ደበቀ።

19“የአገልጋዮቹም ጌታ ከብዙ ጊዜ በኋላ ከሄደበት ተመልሶ የሰጣቸውን ገንዘብ ተሳሰበ።

20አምስት ታላንት የተቀበለውም፣ ሌላ አምስት ተጨማሪ ታላንት ይዞ በመቅረብ፣ ‘ጌታ ሆይ! አምስት ታላንት ዐደራ ሰጥተኸኝ ነበር፤ ይኸውልህ አምስት ተጨማሪ ታላንት አትርፌአለሁ’ አለው።

21“ጌታውም፣ ‘ደግ አድርገሃል፤ አንተ መልካም ታማኝ አገልጋይ፤ በትንሽ ነገር ላይ ታማኝ ስለ ሆንህ በብዙ ነገር ላይ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ አለው።

22“እንዲሁም ሁለት ታላንት የተቀበለው አገልጋይ ቀርቦ፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ሁለት ታላንት ሰጥተኸኝ ነበር፤ ይኸው ሁለት ተጨማሪ ታላንት አትርፌአለሁ’ አለው።

23“ጌታውም፣ ‘ደግ አድርገሃል፤ አንተ መልካም ታማኝ አገልጋይ፤ በትንሽ ነገር ላይ ታማኝ ስለ ሆንህ በብዙ ነገር ላይ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ አለው።

24“አንድ ታላንት የተቀበለው አገልጋይ ቀርቦ፣ ‘ጌታ ሆይ፤ አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን ዐውቃለሁ፤

25ስለዚህ ፈራሁህ፤ ሄጄም መሬት ቈፍሬ ታላንትህን ጕድጓድ ውስጥ ደበቅሁት፤ ገንዘብህ ይኸውልህ’ አለው።

26“ጌታውም መልሶ፣ ‘አንተ ክፉ፣ ሰነፍ አገልጋይ፤ ካልዘራሁበት የማጭድ፣ ካልበተንሁበትም የምሰበስብ መሆኔን ታውቅ ኖሮአል?

27ታዲያ፣ በምመለስበት ጊዜ ገንዘቤን ከነወለዱ እንዳገኘው ለለዋጮች መስጠት ይገባህ ነበር።

28“ ‘በሉ እንግዲህ ታላንቱን ወስዳችሁ ዐሥር ታላንት ላለው ስጡ፤

29ላለው ይጨመርለታል፤ የተትረፈረፈም ይኖረዋል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።

30ይህን የማይረባ አገልጋይ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጥታችሁ ጣሉት’ አለ።

31“የሰው ልጅ ከመላአክቱ ሁሉ ጋር በክብሩ ሲመጣ፣ በክብሩ ዙፋን ላይ ይቀመጣል፤

32ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እርሱም፣ እረኛ በጎችን ከፍየሎች እንደሚለይ፣ ሕዝቡን አንዱን ከሌላው ይለያል፤

33በጎቹን በቀኙ፣ ፍየሎቹን ግን በግራው ያቆማቸዋል።

34“በዚያን ጊዜ ንጉሡ በቀኙ በኩል ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንት አባቴ የባረካችሁ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ፤

35ምክንያቱም ተርቤ አብልታችሁኛል፤ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛል፤ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛል፤

36ታርዤ አልብሳችሁኛል፤ ታምሜ አስታምማችሁኛል፤ ታስሬ ጠይቃችሁኛል።’

37“ጻድቃንም መልሰው እንዲህ ይሉታል፤ ‘ጌታ ሆይ፤ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህ? ወይም ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?

38እንግዳ ሆነህ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ?

39እንዲሁም ታመህ ወይም ታስረህ አይተን መቼ ጠየቅንህ?’

40“ንጉሡም መልሶ፣ ‘እውነት እላችኋለሁ፣ ከእነዚህ አነስተኛ ከሆኑት ወንድሞቼ ለአንዱ ያደረጋችሁት፣ ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው’ ይላቸዋል።

41“ከዚያም በግራው በኩል ላሉት ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ፤ ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው የዘላለም እሳት ከእኔ ተለይታችሁ ሂዱ፤

42ምክንያቱም ተርቤ አላበላችሁኝም፤ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝም፤

43እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝም፤ ታርዤ አላለበሳችሁኝም፤ ታምሜና ታስሬ አልጠየቃችሁኝም።’

44“እነርሱም መልሰው፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ተርበህ ወይም ተጠምተህ፣ እንግዳ ሆነህ ወይም ታርዘህ፣ ታመህ ወይም ታስረህ ዐይተን መቼ አልደረስንልህም’ ይሉታል።

45“በዚያን ጊዜ እርሱም መልሶ፣ ‘እውነት እላችኋለሁ፣ ከእነዚህ አነስተኛ ከሆኑት ወንድሞቼ ለአንዱ አለማድረጋችሁ፣ ለእኔ እንዳላደረጋችሁት ነው’ ይላቸዋል።

46“እነዚህም ወደ ዘላለም ፍርድ፣ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።”

ማብራሪያ

25:1-13 የዐሥርቱ ደናግል ምሳሌ ሁኔታዎች ከይሁዳውያን የጋብቻ ወጎች የተወሰዱ ሲሆኑ፣ የክርስቶስን ታላቅ የመምጣት ቀን ያብራራሉ። የክርስትናን ማንነት ተመልከቱ። እኛ ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን፣ ክርስቶስን ለማገልገል፣ እርሱን ለማክበር እንዲሁም እርሱንም ለመምጣት ለመጠባበቅ እንመሰክራለን።

ቅን ክርስቲያኖች አስተዋይ ደናግል ሲሆኑ፣ ግብዞች ደግሞ ሰነፎች ናቸው። በነፍሳቸው ጉዳይ አስተዋይ ወይም ሰነፍ የሆኑት እነርሱ በእውነትም አስተዋይ ወይም ሰነፍ ናቸው። ብዙዎች በእጃቸው የመመስከር መብራት አላቸው፣ ነገር ግን በልባቸው ውስጥ በዚህ በዓለም ውስጥ ባሉት አገልግሎቶችና ፈተናዎች ውስጥ ሊያሻግራቸው የሚችል የጸና ዕውቀትና የጸና ውሳኔ የላቸውም። ልቦቻቸውም በአዲስ በሚፈጥረው በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የተቀደሰ ዝንባሌ አልተሞሉም።

ብርሃናችን በጎ ሥራን በማድረግ በሰዎች ፊት ሊበራ ይገባል፤ ነገር ግን በልብ ውስጥ በክርስቶስ ላይ ያለ እምነትና ለእግዚአብሔርና ለወንድሞቻችን ያለ ፍቅር የጸናና ንቁ መርህ ከሌለ ይህ ለረጅም ጊዜ የሚቀጥል አይሆንም። ሁሉም አንቀላፉና ተኙ። መዘግየቱ የእነዚህ የመሰከሩ ሰዎች እውነተኛ ወይም የሚመስል ለውጥ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ክርስቶስ መምጣት ድረስ፣ በሞት ሊወስዳቸው ወይም ዓለምን ሊፈርድባት ድረስ ያለውን ጊዜ ያመለክታል።

ክርስቶስ ጊዜያችንን ቢያልፍም፣ የተወሰነውን ጊዜ ግን አያልፍም። አስተዋይ ደናግል መብራቶቻቸውን በርተው አቆዩ፣ ነገር ግን ራሳቸውን ንቁ አላደረጉም። በጣም ብዙ እውነተኛ ክርስቲያኖች ይዘናጋሉ፣ አንድ የቸልተኝነት ደረጃ ለሌላው በር ይከፍታል። ራሳቸውን እንዲያንቀላፉ የሚፈቅዱ ሰዎች ከእንቅልፍ እምብዛም አይድኑም፤ ስለዚህ ለመንፈሳዊ መዳከም መጀመሪያ ተጠንቀቁ። አስደንጋጭ ጥሪ ተሰጠ። እርሱን ልትቀበሉ ውጡ፣ ዝግጁ ለሆኑት የተሰጠ ጥሪ ነው። የክርስቶስ መቃረብ ማስታወቂያና እርሱን ለመገናኘት የተሰጠው ጥሪ ያነቃቃል። ለሞት በጣም የተዘጋጁት እንኳን በእውነት ለመዘጋጀት የሚያስፈልጋቸው ሥራ አላቸው፣ 2Pe 3:14።

ይህ የፍለጋና የመመርመር ቀን ይሆናል፤ በዚያን ጊዜ እንዴት እንደምንገኝ ማሰብ የእኛ ጉዳይ ነው። አንዳንዶች መብራቶቻቸው እየጠፉ ሲሄዱ ዘይት አስፈለጋቸው። እውነተኛውን ጸጋ የጎደላቸው በእርግጥ አንድ ቀን ወይም ሌላ ቀን የጸጋ እጦት ያገኙታል። ውጫዊ የሆነ ሃይማኖታዊ መግለጫ ሰውን በዚህ ዓለም ሊያበራው ይችላል፣ ነገር ግን የሞት ጥላ ሸለቆ እርጥበት እንደዚህ ያለውን ብርሃን ያጠፋል።

ሕይወትን ለመኖር ግድ የሌላቸው፣ ነገር ግን የጻድቃንን ሞት ለመሞት የሚፈልጉ አሉ። ነገር ግን የሚድኑ ሰዎች የራሳቸው ጸጋ ሊኖራቸው ይገባል፤ ብዙ ጸጋ ያላቸውም እንኳ የሚተርፋቸው የለም። ምርጦቹም ከክርስቶስ ብዙ ያስፈልጋቸዋል። ድሃው የተረበሸች ነፍስ በሕመም አልጋዋ ላይ ሆና፣ በፍርሃት ግራ በመጋባት፣ ንስሐና ጸሎት ስታደርግ፣ ሞት ይመጣል፣ ፍርድ ይመጣል፣ ሥራው ሳይሠራ ይቀራል፣ ድሃው ኃጢአተኛም ለዘላለም ይጠፋል። ይህ የሚመጣው ማቃጠል በሚገባን ጊዜ ዘይት ለመግዛት ከመፈለግ፣ መጠቀም በሚገባን ጊዜ ደግሞ ጸጋ ለማግኘት ከመፈለግ የተነሳ ነው።

በዚህ ዓለም ለሰማይ የተዘጋጁት እነርሱ ብቻ ከዚህ በኋላ ወደ ሰማይ ይገባሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6