የማቴዎስ ወንጌል 14

AMHNIVአማርኛ36 ጥቅሶች4:48 አዳምጥ
አዳምጥ 4:48 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በዚያን ጊዜ የአራተኛው ክፍል ገዥ የነበረው፣ ሄሮድስ ስለ ኢየሱስ ዝና ሰማ፤

2ባለሟሎቹንም፣ “እንዲህ ከሆነ መጥምቁ ዮሐንስ ከሞት ተነሥቶ መጥቶአል ማለት ነው፤ ይህ ሁሉ ድንቅ ታምራት በእርሱ የሚደረገውም ለዚህ ነው” አላቸው።

3ቀደም ሲል ሄሮድስ፣ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ ወህኒ አስገብቶት ነበር።

4ምክንያቱም ዮሐንስ፣ “እርሷን እንድታገባ ሕግ አይፈቅድልህም” ይለው ነበር።

5ሄሮድስም ዮሐንስን ሊገድለው ፈልጎ፣ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ይመለከተው ስለ ነበር ፈራ።

6ሄሮድስ የልደቱን ቀን ሲያከብር፣ የሄሮድያዳ ልጅ በዘፈን ደስ ስላሰኘችው፣

7የምትጠይቀውን ሁሉ ሊሰጣት በመሐላ ቃል ገባላት።

8ልጅቷም በእናቷ ተመክራ፣ “የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በሳሕን ላይ አድርገህ አሁኑኑ ስጠኝ” አለችው።

9በዚህ ጊዜ ንጉሡ አዘነ፤ ይሁን እንጂ ስለ መሐላውና ከእርሱ ጋር ስለ ነበሩ እንግዶች ሲል ጥያቄዋ እንዲፈጸምላት አዘዘ።

10ልኮም በወህኒ ውስጥ እንዳለ የዮሐንስን ራስ አስቈረጠ።

11የተቈረጠውንም ራስ በሳሕን ላይ አድርገው ለልጅቱ ሰጧት፤ ልጅቱም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች።

12የዮሐንስ ደቀ መዛሙርትም አስከሬኑን ወስደው ቀበሩት፤ ከዚያም ሄደው የሆነውን ለኢየሱስ ነገሩት።

13ኢየሱስ የሆነውን ነገር በሰማ ጊዜ፣ ከነበረበት ተነሥቶ ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራ በጀልባ ሄደ። ሕዝቡም ይህን ሰምተው፣ ከየከተማው በእግር ተከተሉት።

14ኢየሱስም ከጀልባው ሲወርድ ብዙ ሕዝብ አይቶ ራራላቸው፤ ሕመምተኞቻቸውንም ፈወሰላቸው።

15እየመሸ በመሄዱም ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው፣ “ይህ ስፍራ ምንም የማይገኝበት ምድረ በዳ ነው፤ ጊዜው እየመሸ ስለ ሆነ፣ ወደ መንደሮች ሄደው የሚበሉት ምግብ እንዲገዙ ሕዝቡን አሰናብት” አሉት።

16ኢየሱስ ግን፣ “መሄድ አያስፈልጋቸውም፤ የሚበሉትን እናንተ ስጧቸው” አላቸው።

17እነርሱም፣ “በዚህ ያለን አምስት እንጀራና ሁለት ዓሣ ብቻ ነው” አሉት።

18እርሱም፣ “እስቲ ያለውን ወደ እኔ አምጡት” አላቸው።

19ከዚያም ሕዝቡ በሣሩ ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፤ አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ዓይኑን ወደ ሰማይ በማቅናት አመስግኖና ባርኮ እንጀራውን ቈረሰ፤ ለደቀ መዛሙርቱም ሰጠ፤ እነርሱም ለሕዝቡ ሰጡ።

20ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ የተረፈውን ቍርስራሽ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ አነሡ።

21የበሉትም ከሴቶችና ከሕፃናት ሌላ አምስት ሺህ ወንዶች ያህሉ ነበር።

22ወዲያውኑ ደቀ መዛሙርቱ በጀልባ ተሳፍረው ወደ ማዶ እንዲቀድሙት አዘዛቸውና እርሱ ሕዝቡን ለማሰናበት ወደ ኋላ ቀረት አለ።

23ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላም ለመጸለይ ብቻውን ወደ ተራራ ወጣ፤ በጨለመም ጊዜ ብቻውን በዚያው ነበር፤

24በዚያ ጊዜ ጀልባዋ ባሕሩን ዘልቃ እየተጓዘች ሳለች ነፋስ ተነሥቶ በማዕበል ትንገላታ ጀመር።

25ከሌሊቱ በአራተኛው ክፍል ኢየሱስ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ደቀ መዛሙርቱ ወዳሉበት መጣ።

26ደቀ መዛሙርቱም በባሕሩ ላይ እየተራመደ ሲመጣ ባዩት ጊዜ ፈሩ፤ እነርሱም፣ “ምትሀት ነው!” በማለት በፍርሃት ጮኹ።

27ኢየሱስም ወዲያውኑ፣ “አይዞአችሁ፤ እኔ ነኝ አትፍሩ” አላቸው።

28ጴጥሮስም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንተ ከሆንህስ፣ በውሃው ላይ እየተራመድሁ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ” አለው።

29እርሱም፣ “ና” አለው። ጴጥሮስም፣ ከጀልባው ወርዶ በውሃው እየተራመደ ወደ ኢየሱስ አመራ።

30ነገር ግን የነፋሱን ኀይል ባየ ጊዜ ፈራ፤ መስጠምም ሲጀምር፣ “ጌታ ሆይ፤ አድነኝ!” ብሎ ጮኸ።

31ኢየሱስም ወዲያውኑ እጁን ዘርግቶ ያዘውና፣ “አንተ እምነት የጐደለህ፤ ለምን ተጠራጠርህ?” አለው።

32ኢየሱስና ጴጥሮስ ጀልባው ላይ እንደ ወጡ ነፋሱ ጸጥ አለ።

33ከዚያም በጀልባው ውስጥ የነበሩት፣ “በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብለው ሰገዱለት።

34ባሕሩን ከተሻገሩ በኋላ ጌንሴሬጥ ወደተባለ ቦታ ደረሱ።

35ነዋሪዎቹም ኢየሱስ መሆኑን ባወቁ ጊዜ፣ በዙሪያው ወዳለ አካባቢ ሁሉ መልእክት ላኩ፤ የታመሙትን ሁሉ ወደ እርሱ በማስመጣት፣

36በሽተኞቹ የልብሱን ጫፍ ብቻ ይነኩ ዘንድ እንዲፈቅድላቸው ለመኑት፤ የነኩትም ሁሉ ተፈወሱ።

ማብራሪያ

14:1-12 ሄሮድስ እንደ ሌሎች ደፋር በደለኞች ሊያራግፋቸው ያልቻላቸው የሕሊና ሽብርና ወቀሳዎች፣ የወደፊት ፍርድና ለእነርሱም የሚመጣባቸው የዘላለም መከራ ማስረጃዎችና ማስጠንቀቂያዎች ናቸው። ነገር ግን የእውነተኛ መለወጥ እውነት በሌለበት የሕሊና ውግዘት ሽብር ሊኖር ይችላል። ሰዎች ወንጌልን የመደገፍ አስመሳይነት እያሳዩ በክፋት ሲኖሩ፣ የራሳቸውን ማታለል ልንደግፍ አይገባም፤ ይልቁንም ዮሐንስ እንዳደረገው ሕሊናችንን ግልጽ ማድረግ አለብን። ዓለም ይህንን ባለጌነትና ጭፍን ቅንዓት ሊለው ይችላል። ሐሰተኛ አማኞች ወይም ፈሪ ክርስቲያኖች ደግሞ እንደ ሥነ-ምግባር ጉድለት ሊወቅሱት ይችላሉ፤ ነገር ግን እጅግ ኃይለኛ የሆኑ ጠላቶች እንኳን ጌታ መልካም ሆኖ ከፈቀደው በላይ ሊሄዱ አይችሉም። ሄሮድስ ዮሐንስን መግደል በሕዝቡ መካከል ዓመፅ ሊያስነሳ ይችላል ብሎ ፈርቶ ነበር፣ ይህም አልሆነም። ነገር ግን የራሱን ሕሊና በእርሱ ላይ እንደሚያነሳሳ በፍጹም አልፈራም ነበር፣ ይህም ሆኖበታል። ሰዎች ስለሚኮነኑበት የማያስፈራቸውን ነገር ከመሰቀል ይፈራሉ። ሥጋዊ ደስታና ጨዋታ የሚበዛባቸው ጊዜያትም በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ክፉ ሴራዎችን ለማካሄድ አመቺ ጊዜያት ናቸው። ሄሮድስ ከንቱ ጭፈራን በልግስና ይሸልማል፤ ነፍሱን ለማዳን የፈለገው የእግዚአብሔር ሰው ዋጋ ግን እስራትና ሞት ሆነ። ነገር ግን ከሄሮድስ ፍቃድ በስተጀርባ ለዮሐንስ እውነተኛ ጥላቻ ነበር፤ አለዚያ ከገባው ቃል ለመውጣት መንገዶችን ባገኘ ነበር። ከታች ያሉ እረኞች ሲመቱ፣ በጎች የሚሄዱበት ታላቅ እረኛ እስከ አላቸው ድረስ መበተን አያስፈልጋቸውም። በችግርና በኪሳራ ወደ ክርስቶስ መሳብ ከቶም ወደ እርሱ አለመምጣት ይሻላል።

14:13-21 ክርስቶስና ቃሉ ሲያፈገፍጉ፣ ከማናቸውም ዓለማዊ ጥቅሞች በፊት ለነፍሳችን የጸጋን መንገድ መፈለግ ለእኛ እጅግ መልካም ነው። የክርስቶስና የወንጌሉ መገኘት ምድረ በዳውን ታጋሽ ብቻ ሳይሆን፣ ተፈላጊም ያደርገዋል። ይህች አነስተኛ የኅብስት አቅርቦት፣ መላው ብዙኃን እስኪጠግቡ ድረስ በክርስቶስ በመፍጠር ኃይል ተበዛች። የሰዎችን ነፍስ ደህንነት በመፈለግ ላይ ሳለን፣ ለሰውነታቸውም በተመሳሳይ እዝነት ሊኖረን ይገባል። ሁልጊዜም በምግባችን ላይ በረከትን መለመንን እናስታውስ፤ ሁሉንም ብክነት ማስወገድንም እንማር፤ ምክንያቱም ቁጥብነት የልግስና ትክክለኛ ምንጭ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6