የሉቃስ ወንጌል 6

AMHEVGአማርኛ48 ጥቅሶች6:41 አዳምጥ
አዳምጥ 6:41 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በሰንበትም በእርሻ መካከል ያልፍ ነበር ደቀ መዛሙርቱም እሸት ይቀጥፉ በእጃቸውም እያሹ ይበሉ ነበር።

2ከፈሪሳውያን ግን አንዳንዶቹ፦ “በሰንበት ሊደረግ ያልተፈቀደውን ስለ ምን ታደርጋላችሁ?” አሉአቸው።

3ኢየሱስም ለእነርሱ መልሶ እንዲህ አለ፦ “ዳዊት በተራበ ጊዜ እርሱ አብረውት ከነበሩ ጋር ያደረገውን፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ ከካህናት ብቻ በቀር መብላቱ ያልተፈቀደውን የመሥዋዕትን እንጀራ ይዞ እንደ በላ፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት ደግሞ እንደ ሰጣቸው ይህን አላነበባችሁምን?

5የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነው፡” አላቸውም።

6በሌላው ሰንበትም ወደ ምኵራብ ገብቶ አስተማረ፤ በዚያም ቀኝ እጁ የሰለለች ሰው ነበረ፤

7ጻፎችና ፈሪሳውያንም መክሰሻ ሊያገኙበት በሰንበት ይፈውስ እንደ ሆነ ይጠባበቁት ነበር።

8እርሱ ግን አሳባቸውን አውቆ እጁ የሰለለችውን ሰው፦ “ተነሣና በመካከል ቁም፡ አለው፤” ተነሥቶም ቆመ።

9ኢየሱስም፦ “እጠይቃችኋለሁ፤ በሰንበት በጎ ማድረግ ተፈቅዶአልን ወይስ ክፉ? ነፍስ ማዳንን ወይስ መግደል?” አላቸው።

10ሁላቸውንም ዙሪያውን አየና ሰውዬውን፦ “እጅህን ዘርጋ” አለው። እርሱም እንዲህ አደረገ፥ እጁም እንደ ሁለተኛይቱ ዳነች።

11እነርሱም ቍጣ ሞላባቸው፥ በኢየሱስም ምን እንዲያደርጉበት እርስ በርሳቸው ተባባሉ።

12በነዚህም ወራት ይጸልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፥ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ።

13በነጋም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን ጠራ፥ ከእነርሱም አሥራ ሁለት መረጠ ደግሞም ሐዋርያት ብሎ ሰየማቸው፤

14እነርሱም፥ ጴጥሮስ ብሎ እንደ ገና የሰየመው ስምዖን፥ ወንድሙም እንድርያስ፥ ያዕቆብም ዮሐንስም፥ ፊልጶስም በርተሎሜዎስም፥

15ማቴዎስም ቶማስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም ቀናተኛ የሚባለው ስምዖንም፥

16የያዕቆብ ይሁዳም፥ አሳልፎ የሰጠውም የአስቆሮቱ ይሁዳ ናቸው።

17ከእነርሱም ጋር ወርዶ በተካከለ ስፍራ ቆመ፥ ከደቀ መዛሙርቱም ወገን ብዙ ሕዝብ ነበረ፥ ደግሞም ሊሰሙትና ከደዌአቸው ሊፈወሱ ከይሁዳ ሁሉ ከኢየሩሳሌምም ከጢሮስና ከሲዶና ባሕር ዳርም የመጡ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤

18ከርኵሳንም መናፍስት ይሠቃዩ የነበሩት ተፈወሱ፤

19ከእርሱም ኃይል ወጥቶ ሁሉን ይፈውስ ነበርና ሕዝቡ ሁሉ ሊዳስሱት ይሹ ነበር።

20እርሱም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዓይኑን አነሣ፥ እንዲህም አላቸው፦ “እናንተ ድሆች ብፁዓን ናችሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት የእናንተ ነውና።

21እናንተ አሁን የምትራቡ ብፁዓን ናችሁ፥ ትጠግባላችሁና። እናንተ አሁን የምታለቅሱ ብፁዓን ናችሁ፥ ትስቃላችሁና።

22ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ፥ ብፁዓን ናችሁ።

23እነሆ፥ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና።

24“ነገር ግን እናንተ ባለ ጠጎች ወዮላችሁ፥ መጽናናታችሁን ተቀብላችኋልና።

25እናንተ አሁን የጠገባችሁ ወዮላችሁ፥ ትራባላችሁና። እናንተ አሁን የምትስቁ ወዮላችሁ፥ ታዝናላችሁና ታለቅሱማላችሁ።

26ሰዎች ሁሉ መልካም ሲናገሩላችሁ፥ ወዮላችሁ፤ አባቶቻቸው ለሐሰተኞች ነቢያት እንዲሁ ያደርጉላቸው ነበርና።”

27“ነገር ግን ለእናንተ ለምትሰሙ እላችኋለሁ፥ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ ለሚጠሉአችሁ መልካም አድርጉ፥

28የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ስለሚበድሉአችሁም ጸልዩ።

29“ጕንጭህን ለሚመታህ ደግሞ ሁለተኛውን ስጠው፥ መጐናጸፊያህንም ለሚወስድ እጀ ጠባብህን ደግሞ አትከልክለው።

30ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፥ ገንዘብህንም የሚወስድ እንዲመልስ አትጠይቀው።

31“ሰዎችም ሊያደርጉላችሁ እንደምትወዱ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው።

32የሚወዱአችሁንማ ብትወዱ፥ ምን ምስጋና አላችሁ? ኃጢአተኞች ደግሞ የሚወዱአቸውን ይወዳሉና።

33“መልካምም ለሚያደርጉላችሁ መልካም ብታደርጉ፥ ምን ምስጋና አላችሁ? ኃጢአተኞች ደግሞ ያን ያደርጋሉና።

34እንድትወስዱባቸው ተስፋ ለምታደርጉአቸው ብታበድሩ፥ ምን ምስጋና አላችሁ? ኃጢአተኞች ደግሞ በትክክል እንዲቀበሉ ለኃጢአተኞች ያበድራሉ።

35“ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካም አድርጉ፤ ምንም ተስፋ ሳታደርጉም አበድሩ፥ ዋጋችሁም ታላቅ ይሆናል፥ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፥ እርሱ ለማያመሰግኑ ለክፉዎችም ቸር ነውና።

36አባታችሁ ርኅሩኅ እንደ ሆነ ርኅሩኆች ሁኑ።

37“አትፍረዱ አይፈረድባችሁምም፤ አትኰንኑ አትኰነኑምም። ይቅር በሉ ይቅርም ትባላላችሁ።

38ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል።”

39ምሳሌም አላቸው፦ “ዕውር ዕውርን ሊመራ ይችላልን? ሁለቱ በጕድጓድ አይወድቁምን?

40ደቀ መዝሙር ከመምህሩ አይበልጥም፤ ፈጽሞ የተማረ ሁሉ ግን እንደ መምህሩ ይሆናል።

41“በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለ ምን ታያለህ፥ በራስህ ዓይን ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም?

42በዓይንህ ያለውን ምሰሶ ራስህ ሳታይ፥ እንዴት ወንድምህን፦ ወንድሜ ሆይ፥ በዓይንህ ያለውን ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ ልትል ትችላለህ? አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ ከዚያም በኋላ በወንድምህ ዓይን ያለውን ጉድፍ ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።”

43“ክፉ ፍሬ የሚያደርግ መልካም ዛፍ የለምና፥ እንዲሁም መልካም ፍሬ የሚያደርግ ክፉ ዛፍ የለም።

44ዛፍ ሁሉ ከፍሬው ይታወቃልና፤ ከእሾህ በለስ አይለቅሙም፥ ከአጣጥ ቍጥቋጦም ወይን አይቈርጡም።

45በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፉ ይናገራልና መልካም ሰው ከልብ መልካም መዝገብ መልካሙን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከልብ ክፉ መዝገብ ክፉውን ያወጣል።

46“ስለ ምን፦ ‘ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥’ ትሉኛላችሁ፥ የምለውንም አታደርጉም?

47ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ ቃሌንም ሰምቶ የሚያደርገው፥ ማንን እንዲመስል አሳያችኋለሁ።

48ቤት ሲሠራ አጥልቆ የቆፈረ በዓለት ላይም የመሠረተ ሰውን ይመስላል፤ ጐርፍም በመጣ ጊዜ ወንዙ ያን ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ ሊያናውጠው አልቻለም።

49ሰምቶ የማያደርገው ግን ያለ መሠረት በምድር ላይ ቤቱን የሠራ ሰውን ይመስላል፤ ወንዙም ገፋው ወዲያውም ወደቀ የዚያ ቤት አወዳደቅም ታላቅ ሆነ።”

ማብራሪያ

6:1-5 ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን በሰንበት ቀን ለራሳቸው አስፈላጊ በሆነው ሥራ ውስጥ ያጸድቃል፤ እርሱም በራባቸው ጊዜ የእህል እሸት መንቀል ነበር። ነገር ግን ይህን ነጻነት ኃጢአት ለመሥራት እንደተፈቀደልን አድርገን እንዳንስት መጠንቀቅ አለብን። ክርስቶስ ቀኑ የእርሱ እንደሆነ እንድናውቅና እንድናስታውስ ይፈልጋል፤ ስለዚህም በአገልግሎቱ ሊውልና ለክብሩም መሆን አለበት።

6:6-11 ክርስቶስ የጸጋውን ዓላማዎች ለመፈጸም አልተሸማቀቀም አልፈራምም ነበር። ምንም እንኳ ጠላቶቹ በዚህ ምክንያት በእርሱ ላይ ሰበብ እንደሚያገኙ ያውቅ የነበረ ቢሆንም፣ ድሃውን ሰው ፈወሰ። በማንኛውም ተቃውሞ ምክንያት ከግዴታችንም ሆነ ከጠቃሚ አገልግሎታችን እንዳንዘናጋ። የሰው ልጆች እንዲህ ክፉዎች መሆናቸው እጅግ ሊያስገርመን ይገባል።

6:12-19 ግማሽ ሰዓት በማሰላሰልና በስውር ጸሎት ለማሳለፍ ብዙ ጊዜ እንደ ትልቅ ነገር እንቆጥረዋለን፤ ክርስቶስ ግን በእነዚህ ተግባራት ሙሉ ሌሊቶችን አሳልፏል። እግዚአብሔርን በምናገለግልበት ጊዜ፣ ትልቁ ጥንቃቄያችን ጊዜን አለማባከን ሳይሆን፣ የአንዱን መልካም ተግባር ፍጻሜ የሌላው መጀመሪያ ማድረግ መሆን አለበት። አስራ ሁለቱ ሐዋርያት እዚህ ተጠርተዋል፤ እንዲህ ያለ ልዩ ክብር ያገኘ ሰው አልነበረም፣ ሆኖም ከእነርሱ አንዱ ጋኔን ያደረበት ነበር፣ ከዳተኛም ሆኖ ተገኘ። በአቅራቢያቸው እውነተኛ ስብከት የሌላቸው ሰዎች፣ ያለእሱ ከመሆን ይልቅ ሩቅ ቢጓዙ ይሻላቸዋል። የክርስቶስን ቃል ለመስማት ሩቅ መሄድ፣ እንዲሁም ለዚህ ሲባል ከሌሎች ሥራዎች ጊዜ መለየት በእርግጥም ዋጋው የሚመጥን ነው። በእርሱ እንዲፈወሱ መጡ፥ እርሱም ፈወሳቸው። በክርስቶስ ዘንድ የጸጋ ሙላትና የመፈወስ ኃይል አለ፤ ይህ ደግሞ ከእርሱ ለመውጣት የተዘጋጀ ሲሆን፣ ለሁሉም የሚበቃ፥ ለእያንዳንዱም የሚበቃ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6