ትንቢተ ዮናስ 3

AMHNIVአማርኛ10 ጥቅሶች1:49 አዳምጥ
አዳምጥ 1:49 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የእግዚአብሔርም ቃል ለሁለተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል ወደ ዮናስ መጣ፤

2“ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሄደህ የምነግርህን መልእክት ስበክላት።”

3ዮናስም የእግዚአብሔርን ቃል ታዘዘ፤ ወደ ነነዌም ሄደ። በዚህ ጊዜ ነነዌ ታላቅ ከተማ ነበረች፤ እርሷንም ከዳር እስከ ዳር ለመጐብኘት ሦስት ቀን ያስፈልግ ነበር።

4ዮናስም ወደ ከተማዪቱ ገብቶ የመጀመሪያውን ቀን ከተጓዘ በኋላ “ነነዌ በአርባ ቀን ውስጥ ትገለበጣለች” ብሎ ዐወጀ።

5የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ጾምንም ዐወጁ፤ ሰዎቹም ሁሉ ከትልቁ እስከ ትንሹ ማቅ ለበሱ።

6ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ በደረሰ ጊዜ፣ ከዙፋኑ ወረደ፤ ልብሱንም አወለቀ፤ ማቅም ለብሶ በዐመድ ላይ ተቀመጠ።

7ከዚያም እንዲህ ሲል በነነዌ ዐዋጅ አስነገረ፤ “ከንጉሡና ከመሳፍንቱ የወጣ ዐዋጅ፤ ማንም ሰው ወይም እንስሳ፣ የከብት መንጋም ሆነ የበግ መንጋ፣ ምንም ነገር አይቅመስ፤ አይብላ፤ ውሃም አይጠጣ።

8ነገር ግን ሰውም እንስሳም ማቅ ይልበስ፤ ሁሉም አጥብቆ ወደ እግዚአብሔር ይጩኽ፤ ሰዎችም ሁሉ ክፉ መንገዳቸውንና የግፍ ሥራቸውን ይተዉ።

9እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ራርቶ ከጽኑ ቍጣው ይመለስም እንደሆነ ማን ያውቃል?”

10እግዚአብሔርም ምን እንዳደረጉና ከክፉ መንገዳቸውም እንዴት እንደ ተመለሱ ባየ ጊዜ ራራላቸው፤ በእነርሱም ላይ ሊያመጣ ያሰበውን ጥፋት አላደረገም።

ማብራሪያ

3:1-4 እግዚአብሔር ዮናስን እንደገና በአገልግሎቱ ተጠቀመበት። እርሱ እኛን መጠቀም ከእኛ ጋር በሰላም መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ነው። ዮናስ ቀድሞ እንዳመፀው አሁን ግን ባለመታዘዝ አልተገኘም። ትዕዛዙን ከመስማት ለመሸሽ አልሞከረም፤ ለመታዘዝም አልተቃወመም። የንስሐን ምንነት እዚህ ተመልከቱ፤ እርሱም የአእምሮአችንና የመንገዳችን ለውጥ፣ ወደ ሥራችንና ወደ ግዴታችንም መመለስ ነው። እንዲሁም የመከራ ጥቅም፤ ስፍራቸውን የተዉትን ወደ ስፍራቸው ይመልሳቸዋል። የመለኮታዊ ጸጋን ኃይል እዩ፤ መከራ በራሱ ሰዎችን ከእግዚአብሔር የሚያርቅ እንጂ ወደ እርሱ የሚያቀርብ አይደለምና። የእግዚአብሔር አገልጋዮች እርሱ በላካቸው ስፍራ መሄድ፣ በጠራቸው ጊዜ መምጣት፣ እና ያዘዛቸውን ማድረግ አለባቸው፤ እኛም የጌታ ቃል ያዘዘውን ሁሉ ማድረግ ይገባናል። ዮናስ መልእክቱን በታማኝነትና በድፍረት አደረሰ። ዮናስ በእነርሱ ላይ ያለውን የእግዚአብሔርን ቁጣ ለማሳየት ከዚህ በላይ ተናገረም አልተናገረም፣ ወይም ደግሞ እነዚህን ቃላት ደጋግሞ ብቻ እንደተናገረ ባይታወቅም፣ የመልእክቱ ዋና ይዘት ግን ይህ ነበር። አርባ ቀን ጻድቅ እግዚአብሔር ፍርዱን ለማዘግየት ረዥም ጊዜ ነው፤ ሆኖም ግን ጻድቅ ላልሆነ ሕዝብ ንስሐ ለመግባትና ራሱን ለማደስ ትንሽ ጊዜ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6