ትንቢተ ኤርምያስ 8

AMHNIVአማርኛ22 ጥቅሶች5:22 አዳምጥ
አዳምጥ 5:22 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“ ‘በዚያን ጊዜ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ የይሁዳን ነገሥታትና መኳንንት ዐፅም፣ የካህናትና የነቢያት ዐፅም፣ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ዐፅም ከየመቃብራቸው ይወጣል።

2በወደዷቸውና በአገለገሏቸው እንዲሁም በተከተሏቸው፣ ባማከሯቸውና ባመለኳቸው በፀሓይ፣ በጨረቃና በሰማያት ከዋክብት ሁሉ ፊት ይሰጣል፤ አይሰበሰብም ወይም አይቀበርም፤ ነገር ግን እንደተጣለ ጒድፍ በምድር ላይ ይበተናል።

3ከዚህ ክፉ ሕዝብ የተረፉት ሁሉ፣ ባሳደድኋቸው ስፍራ ሁሉ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ፤ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።’

4“እንዲህ በላቸው፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ሰዎች ቢውድቁ፣ እንደ ገና ከወደቁበት አይነሡምን? ሰው ተሳስቶ ወደ ኋላ ቢሄድ፣ ከስሕተቱ አይመለስምን?

5ታዲያ፣ ይህ ሕዝብ ለምን ፊቱን አዙሮ ወደ ኋላ ይሄዳል? ለምንስ ኢየሩሳሌም ዘወትር ወደ ኋላ ትመለሳለች? ተንኰልን የሙጥኝ ብለው ይዘዋል፤ ሊመለሱም ፈቃደኛ አይደሉም።

6እኔ በጥንቃቄ አደመጥኋቸው፤ ትክክለኛ የሆነውን ግን አይናገሩም። ማንም ስለ ክፋቱ ንስሓ የገባ የለም፤ “ምን አድርጌአለሁ?” ይላል። ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ፈረስ፣ እያንዳንዱ በራሱ መንገድ ይሄዳል።

7ሽመላ እንኳ በሰማይ፣ የተወሰነ ጊዜዋን ታውቃለች፣ ዋኖስ፣ ጨረባና ዋርዳም፣ የሚሰደዱበትን ጊዜ ያውቃሉ፤ ሕዝቤ ግን፣ የእግዚአብሔርን ሥርዐት አላወቀም።

8“ ‘የጸሓፊዎቻችሁ ሐሰተኛ ብርዕ ሐሰት እያስተናገደ እንዴት፣ “ዐዋቂዎች ነን፣ የእግዚአብሔር ሕግ አለን” ትላላችሁ?

9ጥበበኞች ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉ፤ በወጥመድም ይያዛሉ። የእግዚአብሔርን ቃል ተቃውመው፣ ምን ዐይነት ጥበብ ይኖራቸዋል?

10ስለዚህ ሚስቶቻቸውንም ለሌሎች ወንዶች እሰጣለሁ፤ ዕርሻዎቻቸውንም ለባዕዳን እሰጣለሁ፤ ከታናሹ እስከ ታላቁ ድረስ፣ ሁሉም ተገቢ ላልሆነ ጥቅም ይስገበገባሉ፤ ነቢያትና ካህናትም እንዲሁ፤ ሁሉም ያጭበረብራሉ።

11የሕዝቤን ቍስል ብርቱ እንዳይደለ በመቍጠር፣ የተሟላ ፈውስ ሳይኖር እንዲሁ ያክማሉ፤ ሰላም ሳይኖር፣ “ሰላም፣ ሰላም” ይላሉ።

12ርኵሰት ሲፈጽሙ ዐፍረው ነበርን? የለም! በጭራሽ አላፈሩም፤ ኀፍረት ምን እንደሆነም አያውቁም። ስለዚህ ከወደቁት ጋር ይወድቃሉ፤ በምቀጣቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፤” ይላል እግዚአብሔር።

13“ ‘ያመረቱትን ሁሉ እወስድባቸዋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በወይን ተክል ላይ የወይን ፍሬ አይኖርም፤ በበለስ ዛፍ ላይ የበለስ ፍሬ አይገኝም፤ ቅጠሎቻቸውም ይረግፋሉ። የሰጠኋቸው በሙሉ፣ ከእነርሱ ይወሰድባቸዋል።’ ”

14“ለምን እዚህ እንቀመጣለን? በአንድነት ተሰብሰቡ! ወደ ተመሸጉት ከተሞች እንሽሽ፤ በዚያም እንጥፋ! በእርሱ ላይ ኀጢአትን ስላደረግን፣ እግዚአብሔር አምላካችን እንድንጠፋ አድርጎናል፤ የተመረዘ ውሃ እንድንጠጣ ሰጥቶናል።

15ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ መልካም ነገር ግን አልመጣም፤ የፈውስ ጊዜን ተመኘን፤ ነገር ግን ሽብር ብቻ ሆነብን።

16የጠላት ፈረሶች ፉርፉርታ፣ ከዳን ይሰማል፤ በድንጒላ ፈረሶቻቸው ማሽካካት፣ መላዋ ምድር ተንቀጠቀጠች። ምድሪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣ ከተማዪቱንና በውስጧ የሚኖሩትን ሁሉ፣ ሊውጡ መጡ።

17“እነሆ፤ በመካከላችሁ መርዘኛ እባቦችን፣ የአስማተኛ ብልኀት የማይገታቸው እፉኝቶችን እሰዳለሁ፤ እነርሱም ይነድፉአችኋል፤” ይላል እግዚአብሔር።

18በሐዘኔ የምታጽናናኝ ሆይ፤ ልቤ በውስጤ ዝላለች።

19እንዲህ የሚለውን የሕዝቤን ጩኸት፣ ከሩቅ ምድር ስማ፦ እግዚአብሔር በጽዮን የለምን? ንጉሥዋስ በዚያ አይኖርምን?” “በተቀረጹ ምስሎቻቸው፣ እንዲሁም ከንቱ በሆኑ ባዕዳን ለምን አስቈጡኝ?”

20“መከሩ ዐለፈ፤ በጋው አበቃ፤ እኛም አልዳንም።”

21ሕዝቤ ሲቈስል፣ እኔም ቈሰልሁ፤ አለቀስሁ፤ ድንጋጤ ያዘኝ።

22በገለዓድ የሚቀባ መድኀኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም አልነበረምን? ለሕዝቤ ቍስል፣ ለምን ፈውስ አልተገኘም?

ማብራሪያ

8:1-3 የሞተ ሰውነት ምንም እውነተኛ ጉዳት ሊደርስበት ባይችልም፣ የክፉዎች ቅሬታ መዋረድ ግን በሕይወት ያሉትን ሊያስደነግጥ ይችላል፤ ይህም የመለኮታዊ ፍትህና ቅጣት ከመቃብር በላይ እንደሚዘረጋ ያስታውሰናል። እዚህ በምድር ላይ ምንም ቢደርስብን፣ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችንን እናዋርድ፣ ምህረቱንም እንሻ።

8:4-13 ይህን ውድመት ያመጣው ምንድን ነው? 1. ሕዝቡ ምክንያትን አልሰሙም ነበር፤ በነፍሳቸው ጉዳይ በተለመደ ጥንቃቄ አላደረጉም ነበር። ኃጢአት መመለስ ነው፤ እርሱም ወደ ሕይወት ከሚያመራው መንገድ ወደ ጥፋት ወደሚያመራው መመለስ ነው። 2. የህሊናን ማስጠንቀቂያ አልሰሙም ነበር። ወደ ንስሐ የመጀመሪያውን እርምጃ አልወሰዱም ነበር። እውነተኛ ንስሐ የሚጀምረው ምን እንዳደረግን በጥልቀት በመመርመርና የበደልን መሆኑን ከምናውቅበት እምነት በመነሳት ነው። 3. የእግዚአብሔርን የአደራረስ መንገዶች አልሰሙም ነበር፤ በእነሱም ውስጥ የእግዚአብሔርን ድምፅ አልተረዱም ነበር፣ ቁጥር 7።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በዚያን ዘመን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የይሁዳን ነገሥታት አጥንትና የመኳንንቶቹን አጥንት፥ የካህናቱን አጥንትና የነቢያቱን አጥንት፥ የኢየሩሳሌምንም ሰዎች አጥንት ከመቃብራቸው ያወጣሉ። አማርኛ ENGNIV “ ‘At that time, declares the Lord, the bones of the kings and officials of Judah, the bones of the priests and prophet… English BCV “በቲ ጊዜ እቱይ ነዕፅምቲ ነገስታት ይሁዳን፥ ነዕፅምቲ መኳንንቲ ይሁዳን ነዕፅምቲ ኻህናትን ነዕፅምቲ ነቢያትን፥ ነዕፅምቲ ህዝቢ ኢየሩሳሌምን፥ ካብ መቓብሮም ከውፅእዎ እዮም፤ ይብል እግዚኣብ… ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo,“Yeroo sanatti lafeen mootota Yihudaa, lafeen gurguddoota ishee, lafeen luboota ishee, lafeen raajota ishee fi… Afaan Oromoo BCV GIZ ይእተ አሚረ ይቤ እግዚአብሔር፡ ያወጽኡ አዕጽምተ ነገሥተ ይሁዳ ወአዕጽምተ መላእክቲሆሙ፡ ወአዕጽምተ ካህናት ወአዕጽምተ ነቢያት ወአዕጽምቲሆሙ ለእለ ይነብሩ ውስጥ ኢየሩሳሌም እምነ መቃብሪሆሙ። giz GAZGAZ Waaqayyo,“Yeroo sanatti lafeen mootota Yihudaa, lafeen gurguddoota ishee, lafeen luboota ishee, lafeen raajota ishee fi… Afaan Oromoo BCV aksum “በቲ ጊዜ እቱይ ነዕፅምቲ ነገስታት ይሁዳን፥ ነዕፅምቲ መኳንንቲ ይሁዳን ነዕፅምቲ ኻህናትን ነዕፅምቲ ነቢያትን፥ ነዕፅምቲ ህዝቢ ኢየሩሳሌምን፥ ካብ መቓብሮም ከውፅእዎ እዮም፤ ይብል እግዚኣብ… ትግርኛ SWAHSUV Wakati ule, asema Bwana, watatoa mifupa ya wafalme wa Yuda, na mifupa ya wakuu wake, na mifupa ya makuhani, na mifupa y… Kiswahili