ትንቢተ ኤርምያስ 3

AMHNIVአማርኛ25 ጥቅሶች5:50 አዳምጥ
አዳምጥ 5:50 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“ሰው ሚስቱን ቢፈታ፣ እርሷም ሄዳ ሌላ ሰው ብታገባ፣ ወደ እርሷ ይመለሳልን? ምድሪቱስ ፈጽማ አትረክስምን? አንቺ ግን ከብዙ ወዳጆችሽ ጋር አመንዝረሻል፤ ታዲያ አሁን ወደ እኔ መመለስ ትፈልጊያለሽን?” ይላል እግዚአብሔር።

2“እስቲ ቀና ብለሽ ጭር ያሉትን ኰረብቶች ተመልከቺ፣ በርኵሰት ያልተጋደምሽበት ቦታ ይገኛልን? በበረሓ፣ እንደ ተቀመጠ ዘላን ዐረብ፣ በየመንገዱ ዳር ተቀምጠሽ ወዳጆችሽን ጠበቅሽ። በዝሙትሽና በክፋትሽ፣ ምድሪቱን አረከስሽ።

3ስለዚህ ካፊያ ተከለከለ፤ ኋለኛው ዝናብም ጠፋ። አንቺ ግን አሁንም የጋለሞታ ገጽታ አለብሽ፤ ዐይንሽን በዕፍረት አልሰብር ብለሻል።

4አሁንም ወደ እኔ ተጣርተሽ፣ ‘አባቴ፣ የልጅነት ወዳጄ፣

5ሁል ጊዜ ትቈጣለህን? ቍጣህስ ለዘላለም ነውን?’ አላልሽኝም? የምትናገሪው እንዲህ ነው፤ ይሁን እንጂ የቻልሽውን ክፋት ሁሉ ታደርጊያለሽ።”

6እግዚአብሔር በንጉሥ ኢዮስያስ ዘመን እንዲህ አለኝ፤ “ከዳተኛዪቱ እስራኤል ያደረገችውን አየህን? ከፍ ወዳለው ኰረብታ ሁሉ ወጥታ፣ ወደ ለመለመው ዛፍ ሥር ሁሉ ሄዳ በዚያ አመነዘረች።

7ይህን ሁሉ ካደረገች በኋላ፣ ወደ እኔ ትመለሳለች ብዬ ነበር፤ ሆኖም አልተመለሰችም፤ ከሓዲዋ እኅቷ ይሁዳም ይህን አየች።

8ለከዳተኛ ዪቱ እስራኤል ስለ ምንዝርናዋ ሁሉ የፍች ወረቀቷን ሰጥቼ አባረርኋት። ከሓዲዋ እኅቷ ይሁዳም ይህን አይታ እንዳልፈራች አየሁ፤ ወጥታም አመነዘረች።

9በቅሌቷም ምድሪቱን አረከሰች፤ ከድንጋይና ከግንድ ጋር አመነዘረች፤

10ይህም ሁሉ ሆኖ ከሓዲዋ እኅቷ ይሁዳ ወደ እኔ የተመለሰችው በማስመሰል እንጂ በሙሉ ልቧ አልነበረም” ይላል እግዚአብሔር።

11እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “ከከሓዲዋ ይሁዳ ይልቅ ከዳተኛዪቱ እስራኤል ጻድቅ ሆና ተገኘች።

12ሂድና ይህን መልእክት ወደ ሰሜን እንዲህ ብለህ ተናገር፤ “ ‘ከዳተኛዪቱ እስራኤል ሆይ፤ ተመለሽ’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘እኔ መሓሪ ስለ ሆንሁ፣ ከእንግዲህ በቍጣ ዐይን አላይሽም’ ይላል እግዚአብሔር። ‘ለዘላለም አልቈጣም።

13በአምላክሽ በእግዚአብሔር ላይ በማመፅሽ፣ ክብርሽንም ለእንግዶች አማልክት፣ በየለምለሙ ዛፍ ሥር አሳልፈሽ በመስጠት፣ ለእኔ ባለመታዘዝሽ፣ በደለኛ መሆንሽን ይህን አንድ ነገር ብቻ እመኚ’ ” ይላል እግዚአብሔር።

14“ከዳተኛ ልጆች ሆይ፤ እኔ ባለቤታችሁ ነኝና ተመለሱ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ከአንድ ከተማ አንድ፣ ከአንድ ነገድ ሁለት መርጫችሁ ወደ ጽዮን አመጣችኋለሁ።

15እንደ ልቤም የሆኑ፣ በዕውቀትና በማስተዋል የሚመሯችሁን እረኞች እሰጣችኋለሁ።

16ቍጥራችሁ በምድሪቱ እጅግ በሚበዛበት ጊዜም ይላል እግዚአብሔር፤ “በዚያ ዘመን፣ ‘የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት’ ብለው ከእንግዲህ አይጠሩም፤ ትዝ አይላቸውም፤ አያስታውሱትምም፤ አይጠፋም፤ ሌላም አይሠራም።

17በዚያ ጊዜ ኢየሩሳሌምን፣ ‘የእግዚአብሔር ዙፋን’ ብለው ይጠሯታል፤ መንግሥታትም ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም ለማክበር በኢየሩሳሌም ይሰበሰባሉ፤ የክፉ ልባቸውንም እልኸኝነት ከእንግዲህ አይከተሉም።

18በዚያን ዘመን የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት በአንድነት ሆነው ከሰሜን ምድር ለአባቶቻቸው ርስት አድርጌ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይመጣሉ።

19“እኔም፣ “ ‘የተመረጠችውን ምድር፣ የትኛውም ሕዝብ ያላገኘውን የተዋበች ርስት ልሰጥሽ፣ እንደ ወንዶች ልጆቼ ምንኛ በደስታ ልቍጠርሽ” አልሁ፤ ‘አባቴ’ ብለሽ የምትጠሪኝ፣ እኔንም ከመከተል ዘወር የማትይ መስሎኝ ነበር።

20የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ለባሏ ታማኝ እንዳልሆነች ሚስት፣ ስታታልሉኝ ኖራችኋል፤” ይላል እግዚአብሔር።

21እግዚአብሔር አምላካቸውን በመርሳት፣ መንገዳቸውን አጣመዋልና፣ የእስራኤል ሕዝብ ጩኸት፣ አሳዛኝ ልቅሶ ባድማ ከሆኑት ኰረብታዎች ተሰማ።

22“እናንት ከዳተኞች ልጆች ተመለሱ፤ ከዳተኝነታችሁን እፈውሳለሁ።” “አንተ እግዚአብሔር አምላካችን ነህና፤ አዎን፤ ወደ አንተ እንመጣለን።

23በእርግጥ በኰረብቶች ላይ፣ እንዲሁም በተራሮች ላይ፣ ሆ! ብለን መውጣታችን መታለል ነው፤ በእርግጥ የእስራኤል መዳን፣ በአምላካችን በእግዚአብሔር ነው።

24ከለጋ ዕድሜአችን ጀምሮ፣ የአባቶቻችንን የድካም ፍሬዎች፣ በጎቻቸውንና ከብቶቻቸውን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን፣ ነውረኛ ጣዖቶች በሏቸው።

25እንግዲህ ዕፍረታችንን ተከናንበን እንተኛ፤ ውርደታችንም ይሸፍነን፤ እኛም አባቶቻችንም፣ እግዚአብሔር አምላካችንን በድለናልና፤ ከልጅነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ አምላካችንን እግዚአብሔርን አልታዘዝንም።”

ማብራሪያ

3:1-5

በንስሐ ውስጥ፣ የሠራናቸውን ኃጢአቶችና እነዚያ ኃጢአቶች የተፈጸሙባቸውን ስፍራዎችና ኅብረቶች ማሰላሰል መልካም ነው። ጌታ እንዴት በርኅራኄ እንደገሠጻቸው! ንስሐ ገብዎችን ሲቀበል እርሱ አምላክ ነው እንጂ ሰው አይደለም። እስካሁን የተናገርከውን ወይም የሠራኸውን ሁሉ ትተህ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ወደ እኔ አትመለስምን? ይህ የእግዚአብሔር ጸጋ አያሸንፍህምን? ይቅርታ አሁን ታውጇልና፣ ጥቅሙን አትቀበልምን? በእርሱ ዘንድ ወደሚመለስ አባካኝ ልጅ እንደ አባት ርኅሩኅ ምሕረትን እንደሚያገኙ ተስፋ ያደርጋሉ። የወጣትነታቸው መሪ አድርገው ወደ እርሱ ይመጣሉ፤ ወጣትነት መሪ ያስፈልገዋል። ንስሐ የሚገቡ ኃጢአተኞች እግዚአብሔር ቍጣውን እስከ መጨረሻው እንደማያቆይ በመተማመን ራሳቸውን ሊያበረታቱ ይችላሉ። በየዘመኑ ያሉ የእግዚአብሔር ምሕረቶች ሁሉ ማበረታቻ ይሰጣሉ። ጌታን አባታቸውና የወጣትነታቸው መሪ አድርጎ ከመያዝ የበለጠ ለወጣቶች ምን የተሻለ ነገር አለ? ወላጆችም ይህንን በረከት በትጋት እንዲፈልጉ ልጆቻቸውን በየዕለቱ ይምሯቸው።

3:6-11 ከሃይማኖታዊ እምነት የራቁትን ወንጀሎች እና የሚያስከትለውን ውጤት ብናስተውል፣ ክፉ መንገዶችን ለመሸሽ የበቂ ምክንያት እናያለን። በኃጢአታቸው ከጠፉት ሰዎች ይበልጥ ወንጀለኛ ሆኖ መገኘት አስፈሪ ነው። ይሁን እንጂ፣ ሌሎች ከእነርሱ ይበልጥ ክፉዎች እንደነበሩ ማወቃቸው በዘላለም ቅጣት ውስጥ ትንሽ ማጽናኛ ይሆናል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በሰው ዘንድ፦ ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ ከእርሱም ዘንድ ሄዳ ሌላ ወንድ ብታገባ፥ በውኑ ደግሞ ወደ እርሱ ትመለሳለችን? ያች ሴት እጅግ የረከሰች አይደለችምን? ይባላል። አንቺ ከብዙ ውሽሞች ጋር … አማርኛ ENGNIV “If a man divorces his wife and she leaves him and marries another man, should he return to her again? Would not the la… English BCV ከምቲ ዝበሃል፦ “ሰብኣይ ንሰበይቱ እንተ ፈትሓ እሞ፥ ንሳ ኻብኡ ኸይዳ ኻልእ ሰብኣይ እንተእተወት፥ ብሓቂ እቲ ቐዳማይ ሰብኣይ መሊሱዶ ኸእትዋ ይኽእል? እታ ሰበይቲ እቲኣ የመና ዝረኸሰትዶ … ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo,“Namni tokko haadha manaa isaa yoo baase, isheenis baatee nama biraatti erga heerumtee, namichi deebisee ishee… Afaan Oromoo BCV GIZ አመ ሰደዳ ብእሲ ለብእሲቱ ወወጽአት እምኀቤሁ ወአውሰበት ካልአ ብእሴ ትገብእኑ ኅቤሁ እንከ ዳግመ? አኮኑ እንከ ትረኵስ ይእቲ ብእሲት? ወአንቲኒ ዘመውኪ በብዙኅን ኖሎት ወተመየጢ ኀቤየ፤ ይ… giz GAZGAZ Waaqayyo,“Namni tokko haadha manaa isaa yoo baase, isheenis baatee nama biraatti erga heerumtee, namichi deebisee ishee… Afaan Oromoo BCV aksum ከምቲ ዝበሃል፦ “ሰብኣይ ንሰበይቱ እንተ ፈትሓ እሞ፥ ንሳ ኻብኡ ኸይዳ ኻልእ ሰብኣይ እንተእተወት፥ ብሓቂ እቲ ቐዳማይ ሰብኣይ መሊሱዶ ኸእትዋ ይኽእል? እታ ሰበይቲ እቲኣ የመና ዝረኸሰትዶ … ትግርኛ SWAHSUV Watu husema, Mtu akimwacha mkewe, naye akienda zake, akawa mke wa mtu mwingine, je! Mtu huyo atamrudia tena? Je! Nchi h… Kiswahili