ትንቢተ ኤርምያስ 30

AMHNIVአማርኛ24 ጥቅሶች4:44 አዳምጥ
አዳምጥ 4:44 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፤

2“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የነገርሁህን ቃል ሁሉ በመጽሐፍ ጻፈው።

3እነሆ፣ ሕዝቤን እስራኤልንና ይሁዳን’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር የምመልስበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ እነርሱም ይወርሷታል’ ይላል እግዚአብሔር።”

4እግዚአብሔር ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤

5“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘የፍርሀትና የሽብር ጩኸት ተሰምቶአል፤ ሰላምም የለም።

6እስቲ ጠይቁ፤ ተመልከቱም፤ ወንድ መውለድ ይችላል? ታዲያ ወንድ ሁሉ ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ እጁን በሆዱ ላይ አድርጎ፣ የሰውስ ሁሉ ፊት ጠቍሮ የማየው ለምንድን ነው?

7ያ ቀን ምንኛ አስጨናቂ ይሆናል! እንደዚያም ያለ አይኖርም፤ ለያዕቆብ የመከራ ጊዜ ነው፤ ነገር ግን ይተርፋል።

8“ ‘በዚያን ቀን’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ‘በጫንቃቸው ላይ ያለውን ቀንበር እሰብራለሁ፤ እስራታቸውንም እበጥሳለሁ፤ ከእንግዲህ ባዕዳን አይገዙአቸውም።

9ነገር ግን ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር፣ ለማስነሣላቸውም ለንጉሣቸው፣ ለዳዊት ይገዛሉ።

10“ ‘ስለዚህ፤ አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፤ አትፍራ፤ እስራኤል ሆይ፤ አትደንግጥ፤’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘አንተን ከሩቅ አገር፣ ዘርህንም ከተማረኩበት ምድር እታደጋለሁ፤ ያዕቆብ ተመልሶ በሰላምና በርጋታ ይቀመጣል፣ የሚያስፈራውም አይኖርም።

11እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ አድንሃለሁም፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘በአሕዛብ መካከል በትኜሃለሁ፤ እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፤ አንተን ግን ሙሉ በሙሉ አላጠፋህም፤ በመጠኑ እቀጣሃለሁ እንጂ፣ ያለ ቅጣት አልተውህም።

12“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ስብራትህ የማይጠገን፣ ቍስልህም የማይድን ነው።

13የሚሟገትልህ ሰው የለም፤ ለቍስልህ መድኃኒት አይኖርም፤ ፈውስም አታገኝም።

14ወዳጆችህ ሁሉ ረስተውሃል፤ ስለ አንተም ግድ የላቸውም። ጠላት እንደሚመታ መታሁህ፤ እንደ ጨካኝም ቀጣሁህ፤ በደልህ ታላቅ፣ ኀጢአትህም ብዙ ነውና።

15ፈውስ ለማይገኝለት ሕመምህ፣ ስለቍስልህ ለምን ትጮኻለህ? በደልህ ታላቅ፣ ኀጢአትህም ብዙ ስለ ሆነ፣ እነዚህን ሁሉ አድርጌብሃለሁና።

16“ ‘ነገር ግን አሟጠው የበሉህ ሁሉ እንደዚያው ይበላሉ፤ ጠላቶችህ ሁሉ ለምርኮ ዐልፈው ይሰጣሉ፤ የሚዘርፉህ ይዘረፋሉ፤ የሚበዘብዙህም ሁሉ ይበዘበዛሉ።

17አንተን ግን መልሼ ጤነኛ አደርግሃለሁ፤ ቍስልህንም እፈውሳለሁ፤’ ይላል እግዚአብሔር። “ ‘የተናቀች፣ ማንም የማይፈልጋት ጽዮን” ብለውሃልና።’

18“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘እነሆ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ፤ ለማደሪያውም እራራለሁ፤ ከተማዪቱ በፍርስራሿ ጒብታ ላይ ትሠራለች፤ ቤተ መንግሥቱም በቀድሞ ቦታው ይቆማል።

19ከእነርሱም የምስጋና መዝሙር፣ የእልልታ ድምፅ ይሰማል። እኔ አበዛቸዋለሁ፤ ቍጥራቸውም አይቀንስም፣ አከብራቸዋለሁ፤ የተናቁም አይሆኑም።

20ልጆቻቸው እንደ ቀድሞው ይሆናሉ፤ ማኅበረ ሰቡም በፊቴ የጸና ይሆናል፤ የሚጨቍኗቸውን ሁሉ እቀጣለሁ።

21መሪያቸው ከራሳቸው ወገን ይሆናል፤ ገዣቸውም ከመካከላቸው ይነሣል፤ ወደ እኔ አቀርበዋለሁ፤ እርሱም ይቀርበኛል፤ አለዚያማ ደፍሮ፣ ወደ እኔ የሚቀርብ ማን ነው? ይላል እግዚአብሔር።

22“ ‘ስለዚህ እናንተ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ።’ ”

23እነሆ፣ የእግዚአብሔር ማዕበል፣ በቍጣ ይነሣል፤ የሚገለባብጥም ዐውሎ ነፋስ፣ በክፉዎች ዐናት ላይ ይወርዳል።

24የልቡን ሐሳብ ሳይፈጽም፣ የእግዚአብሔር ቍጣ፣ እንዲሁ አይመለስም፤ በሚመጡትም ዘመናት፣ ይህን ታስተውላላችሁ።

ማብራሪያ

30:1-11 ኤርምያስ እግዚአብሔር የነገረውን እንዲጽፍ ተነገረው። እነዚህ ቃላት መንፈስ ቅዱስ የሚያስተምራቸው ናቸው። እነዚህ እግዚአብሔር እንዲጻፉ ያዘዛቸው ቃላት ናቸው፤ በእርሱ ትእዛዝ የተጻፉ ተስፋዎችም በእውነት የእርሱ ቃል ናቸው። ሕዝቡ አሁን ያሉበትንና ሊገቡበት የነበረውን መከራ እንዲጽፍ ነበረበት። ለእነዚህ መከራዎች መልካም ፍጻሜ ይደረግላቸዋል። የቤተ ክርስቲያን መከራዎች ለረጅም ጊዜ ሊቆዩ ቢችሉም፣ ሁልጊዜ አይቆዩም። አይሁድም እንደገና ይመለሳሉ። መሲሑን፣ ክርስቶስን፣ የዳዊት ልጅ የሆነውን ነገሥታቸውን ይታዘዙታል (ወይም ይሰሙታል)። የአይሁድ ከባቢሎን መዳን በትንቢቱ ውስጥ ተጠቁሟል፤ ነገር ግን የእስራኤልና የይሁዳ ወደ ነገሥታቸው ክርስቶስ ሲመለሱ የሚኖራቸው መመለስና የደስታ ሁኔታ፣ እንዲሁም ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት የአሕዛብ መከራ ትንቢት ተነግሮላቸዋል። ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ማክበር አለባቸው፣ በእርሱም በእግዚአብሔር አገልግሎትና አምልኮ ውስጥ መግባት አለባቸው። ቸር የሆነው ጌታችን የአማኙን ኃጢአት ይቅር ይላል፣ የኃጢአትንና የሰይጣንን ቀንበርም ይሰብራል፤ እርሱም እግዚአብሔርን ያለ ፍርሃት፣ በጽድቅና በእውነተኛ ቅድስና በእርሱ ፊት በቀሪው የሕይወቱ ዘመን ሁሉ፣ የነገሥታችን የክርስቶስ ቤዛነት የተገኘለት ተገዥ ሆኖ…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6