ትንቢተ ኢሳይያስ 32

AMHNIVአማርኛ20 ጥቅሶች3:15 አዳምጥ
አዳምጥ 3:15 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እነሆ፤ ንጉሥ በጽድቅ ይነግሣል፤ ገዦችም በፍትሕ ይገዛሉ።

2እያንዳንዱ ሰው ከነፋስ መከለያ፣ ከወጀብም መጠጊያ ይሆናል። በበረሓም እንደ ውሃ ምንጭ፣ በተጠማም ምድር እንደ ትልቅ ቋጥኝ ጥላ ይሆናል።

3የሚያዩ ሰዎች ዐይን ከእንግዲህ አይጨፈንም፤ የሚሰሙም ጆሮዎች ነቅተው ያዳምጣሉ።

4የችኵል አእምሮ ያውቃል፤ ያስተውላልም፤ የተብታባም ምላስ የተፈታ ይሆናል፤ አጥርቶም ይናገራል።

5ከእንግዲህ ሰነፍ ጨዋ አይባልም፤ ጋጠወጥም አይከበርም።

6ሰነፍ ስንፍናን ይናገራል፤ አእምሮው ክፋትን ያውጠነጥናል፤ ፈሪሀ እግዚአብሔር የሌለበትን አድራጐት ይፈጽማል፤ በእግዚአብሔርም ላይ የስሕተት ቃል ይናገራል፤ ለተራበ ምግብ ይከለክላል፤ ለተጠማ ውሃ አይሰጥም።

7የጋጠወጥ ዘዴ ክፉ ነው፤ የችግረኛም አቤቱታ ትክክል ቢሆን፣ ድኻን በሐሰት ለማጥፋት፣ ክፋት ያውጠነጥናል።

8ጨዋ ግን ሐሳቡም ጨዋ ነው፤ በጨዋነት ምግባርም ጸንቶ ይገኛል።

9እናንት ትዕቢት የወጠራችሁ ሴቶች፣ ተነሡ፤ ድምፄን ስሙ፤ እናንት ተደላድላችሁ የምትኖሩ፣ ሴቶች ልጆች ሆይ፤ የምነግራችሁን አድምጡ።

10ዓመቱ ገና እንዳለፈ፣ ተደላድላችሁ የነበራችሁ ትንቀጠቀጣላችሁ፤ የወይን ተክል ፍሬ አይሰጥም፤ የፍራፍሬም ወቅት አይመጣም።

11እናንት ትዕቢት የወጠራችሁ ሴቶች ተንቀጥቀጡ፤ እናንት ተደላድላችሁ የምትኖሩ ሴቶች ልጆች፤ በፍርሀት ተርበትበቱ፤ ልብሳችሁን አውልቁ፣ ወገባችሁን በማቅ ታጠቁ።

12ስለ ለሙ መሬት ደረታችሁን ምቱ፤ ስለ ፍሬያማው የወይን ተክል ዕዘኑ፤

13ስለ ሕዝቤ ምድር፣ እሾኽና አሜከላ ስለ በቀለበት ምድር፣ ስለ ፈንጠዝያ ቤቶች ሁሉ፣ ስለዚህችም መፈንጫ ከተማ አልቅሱ።

14ዐምባ ምሽጉ ወና ይሆናል፤ ውካታ የበዛበት ከተማ ጭር ይላል፤ ምሽጉና ማማው ለዘላለሙ ዋሻ፣ የዱር አህያ መፈንጫ፣ የመንጋም መሰማሪያ ይሆናል፤

15ይህም የሚሆነው መንፈስ ከላይ እስኪፈስልን፣ ምድረ በዳው ለም መሬት፣ ለሙ መሬትም ጫካ እስኪመስል ድረስ ነው።

16በምድረ በዳ ፍትሕ ይሰፍናል፤ በለሙም መሬት ጽድቅ ይኖራል፤

17የጽድቅ ፍሬ ሰላም፣ የጽድቅ ውጤትም ጸጥታና ለዘላለም መታመን ይሆናል።

18ሕዝቤ ሰላማዊ በሆነ መኖሪያ፣ በሚያስተማምን ቤት፣ ጸጥ ባለም ስፍራ ዐርፎ ይኖራል።

19ደኑ በበረዶ ቢመታ፣ ከተማውም ፈጽሞ ቢወድም፣

20በየወንዙ ዳር ዘር የምትዘሩ፣ በሬዎቻችሁንና አህዮቻችሁን በነጻነት የምታሰማሩ፣ ምንኛ የተባረካችሁ ናችሁ።

ማብራሪያ

32:1-8 ክርስቶስ ጻድቅ ንጉሣችን እና እውነተኛ ደቀ መዛሙርቱ እዚህ በግልጽ የሚጠቀሱት ናቸው። የመንፈሱ መጽናናቶችና ጸጋዎች በዚህ ደረቅ ምድር እንደ ወንዞች ውኃ ናቸው፤ በበረሃ ለሚደክመው መንገደኛ ጥላና መጠጊያ የሚሰጠው ተንጠልጣይ ዓለት እንደሚያሳርፍ፣ እንዲሁ ኃይሉ፣ እውነቱ፣ እና ፍቅሩ አማኙን ወደ ሰማይ በሚያደርገው ጉዞ በሚደክምባት ምድር ውስጥ እውነተኛ ጥበቃንና እረፍትን ብቻ ይሰጡታል። ክርስቶስ ማዕበሉን ራሱ ተሸከመ፣ ከእኛ ለመጠበቅ። ተንቀጥቃጩ ኃጢአተኛ ወደ እርሱ ለመጠጊያ ይሽሽ፤ እርሱ ብቻውን በፈተና ሁሉ ውስጥ ሊጠብቀንና ሊያሳርፈን ይችላልና። ኃጢአተኞች በኃጢአት ምን ያህል እንደሚታገሉ ተመልከት፤ በላዩ ላይ ይደክማሉ፣ ልባቸውም በእርሱ ላይ ተተክሏል፣ በብልሃትም ክፋትን ይሠራሉ፤ ነገር ግን ይህ የእኛ መጽናናት ነው፣ እግዚአብሔር ከሚፈቅደው በላይ ምንም ክፋት ማድ…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6