ትንቢተ ኢሳይያስ 30

AMHEVGአማርኛ33 ጥቅሶች6:21 አዳምጥ
አዳምጥ 6:21 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ለዓመፀኞች ልጆች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር፤ ከእኔ ዘንድ ያልሆነን ምክር ይመክራሉ፥ ኃጢአትንም በኃጢአት ላይ ይጨምሩ ዘንድ ከመንፈሴ ዘንድ ያልሆነውን ቃል ኪዳን ያደርጋሉ።

2ከአፌም ነገርን ሳይጠይቁ በፈርዖን ኃይል ይጸኑ ዘንድ በግብፅም ጥላ ይታመኑ ዘንድ ወደ ግብፅ እንዲወርዱ ይሄዳሉ።

3ስለዚህ የፈርዖን ኃይል እፍረት በግብፅም ጥላ መታመን ስድብ ይሆንባችኋል።

4አለቆች ምንም በጣኔዎስ ቢሆኑ፥ መልክተኞችም ምንም ወደ ሓኔስ ቢደርሱ፥

5ሁላቸው ይጠቅሙአቸው ዘንድ ስለማይችሉ፥ እፍረትና ስድብ እንጂ ረድኤትና ረብ ስለማይሆኑ ሕዝብ ያፍራሉ።

6በደቡብ ስላሉ እንስሶች የተነገረ ሸክም። ተባትና እንስት አንበሳ እፉኝትም ነዘር እባብም በሚወጡባት በመከራና በጭንቀት ምድር በኩል ብልጥግናቸውን በአህዮች ጫንቃ ላይ መዛግብቶቻቸውንም በግመሎች ሻኛ ላይ እየጫኑ ወደማይጠቅሙአቸው ሕዝብ ይሄዳሉ።

7የግብፅ እርዳታ ከንቱና ምናምን ነው፤ ስለዚህ ስሙን፦ በቤት የሚቀመጥ ረዓብ፡ ብዬ ጠርቼዋለሁ።

8አሁንም ሂድ፥ ለሚመጣውም ዘመን ለዘላለም እንዲሆን በሰሌዳ ላይ በመጽሐፍም ውስጥ ጻፍላቸው።

9ዓመፀኛ ወገንና የእግዚአብሔርን ሕግ ለመስማት የማይወድዱ የሐሰት ልጆች ናቸውና፤

10ባለ ራእዮችን፦ አትመልከቱ፡ ይላሉ፥ ነቢያትንም፦ ጣፋጩንና አታላዩን ነገር እንጂ ቅኑን ነገር አትንገሩን፤

11ከመንገድ ፈቀቅ በሉ፥ ከጐዳናውም ዘወር በሉ፥ የእስራኤልንም ቅዱስ ከእኛ ዘንድ አስወግዱ፡ ይሉአቸዋል።

12ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ ይህችን ቃል አቃልላችኋልና፥ በግፍና በጠማምነት ታምናችኋልና፥ በእርሱም ተደግፋችኋልና፥

13ስለዚህ ይህ በደል አዘብዝቦ ለመፍረስ እንደ ቀረበ፥ አፈራረሱም ፈጥኖ ድንገት እንደሚመጣ እንደ ረጅም ቅጥር ይሆንባችኋል።

14የሸክለኛ ማድጋ እንደሚሰበር ይሰብረዋል፥ ሳይራራም ያደቅቀዋል፤ ከስባሪውም እሳት ከማንደጃ የሚወስዱበት ወይም ውኃ ከጕድጓድ የሚቀዱበት ገል አይገኝም።

15የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፤ እናንተም እንቢ አላችሁ፥

16ነገር ግን፦ በፈረስ ላይ ትቀምጠን እንሸሻለን እንጂ እንዲህ አይሆንም፡ አላችሁ፥ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ደግሞም፦ በፈጣን ፈረስ ላይ እንቀመጣለን፡ አላችሁ፥ ስለዚህም የሚያሳድዱአችሁ ፈጣኖች ይሆናሉ።

17ከአንድ ሰው ዛቻ የተነሣ ሺህ ሰዎች ይሸሻሉ፤ እናንተም በተራራ ራስ ላይ እንዳለ ምሰሶ፥ በኮረብታም ላይ እንዳለ ምልክት ሆናችሁ እስክትቀሩ ድረስ፥ ከአምስት ሰዎች ዛቻ የተነሣ ትሸሻላችሁ።

18እግዚአብሔርም የፍርድ አምላክ ነውና ስለዚህ እግዚአብሔር ይራራላችሁ ዘንድ ይታገሣል፥ ይምራችሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።

19በኢየሩሳሌም ውስጥ በጽዮን የምትኖሩ ሕዝብ ሆይ፥ ከእንግዲህ ወዲህ አታለቅስም፤ በጩኸትም ድምፅ ይራራልሃል፥ በሰማህም ጊዜ ይመልስልሃል።

20ጌታም የጭንቀትን እንጀራና የመከራን ውኃ ቢሰጥህም አስተማሪህ እንግዲህ ከአንተ አይሰወርም፤ ዓይኖችህ ግን አስተማሪህን ያያሉ፥

21ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ ብትል ጆሮችህ በኋላህ፦ መንገዱ ይህች ናት፥ በእርስዋም ሂድ፡ የሚለውን ቃል ይሰማሉ።

22በብርም የተለበጡትን የተቀረጹትን ምስሎችህን በወርቅም የተለበጡትን ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎችህን ታረክሳለህ፤ እንደ ርኩስም ነገር ትጥላቸዋለህ፦ ወግዱ፡ ትላቸውማለህ።

23በምድርም ለተዘራው ዘርህ ዝናብ ይሰጣል፥ ከምድርም ፍሬ የሚወጣ እንጀራ ወፍራምና ብዙ ይሆናል። በዚያም ቀን ከብቶችህ በሰፊ መስክ ይሰማራሉ፤

24መሬትንም የሚያርሱ በሬዎችና አህዮች በመንሽና በወንፊት የነጻውን ጨው ጨው የሚለውን ገፈራ ይበላሉ።

25በታላቅም እልቂት ቀን ግንቦች በወደቁ ጊዜ በረጅሙ ተራራ ሁሉ ከፍ ባለውም ኮረብታ ሁሉ ላይ ወንዞችና የውኃ ፈሳሾች ይሆናሉ።

26እግዚአብሔርም የሕዝቡን ስብራት በጠገነ ዕለት፥ መቅሰፍቱ የቈሰለውንም በፈወሰ ዕለት፥ የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፥ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል።

27እነሆ፥ የእግዚአብሔር ስም ከሚነድድ ቍጣ ከሚትጐለጐልም ጢስ ጋር ከሩቅ ይመጣል፤ ከንፈሮቹም ቍጣን የሞሉ ናቸው፥ ምላሱም እንደምትበላ እሳት ናት፤

28እስትንፋሱም አሕዛብን በአጥፊ ወንፊት ሊነፋቸው እንደሚያጥለቀልቅ እስከ አንገትም እንደሚደርስ ወንዝ ነው፥ በሕዝብም መንጋጋ የሚያስት ልጓም ይሆናል።

29ዝማሬ በተቀደሰች የዐውደ ዓመት ሌሊት እንደሚሆን ዝማሬ ይሆንላችኋል፤ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ እስራኤል አምባ ይመጣ ዘንድ እንቢልታ ይዞ እንደሚሄድ ሰው የልብ ደስታ ይሆንላችኋል።

30እግዚአብሔርም ክቡር ድምፁን ያሰማል፥ የክንዱንም መውረድ በሚነድድ ቍጣውና በምትበላ እሳት ነበልባል በዐውሎ ነፋስም በወጨፎም በበረዶ ጠጠርም ይገልጣል።

31አሦርም በበትር ከመታው ከእግዚአብሔር ድምፅ የተነሣ ይደነግጣል።

32እግዚአብሔር በላዩ በሚያወርድበት የታዘዘበቱ የበትር ድብደባ ሁሉ በከበሮና በመሰንቆ ይሆናል፤ በጦርነትም ክንዱን አንሥቶ ይዋጋቸዋል።

33ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች፥ ለንጉሥም ተበጅታለች፤ ጥልቅና ሰፊም አድርጎአታል፤ እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የእግዚአብሔርም እስትንፋስ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል።

ማብራሪያ

30:1-7 የአይሁድ ሕዝብ ብዙ ጊዜ ስህተታቸውና ሞኝነታቸው፣ በአንድ በኩል ከጎረቤቶቻቸው መከራ ሲደርስባቸው፣ ወደ እግዚአብሔር ከመመልከት ይልቅ ከሌሎች እርዳታ መፈለጋቸው ነበር። ኃጢአት ላይ ኃጢአት በመጨመር የሚመጣውን አስከፊ መዘዝ ልናስወግድ አንችልም፣ ነገር ግን የክርስቶስን ጽድቅ መጠጊያችን በማድረግ እና የመንፈስ ቅዱስን ቅድሳት በመፈለግ ብቻ ነው። ሰዎች ሁልጊዜ የራሳቸውን ማስተዋል የመታመን ዝንባሌ ነበራቸው፣ ነገር ግን ይህ የሚያበቃው በእፍረታቸውና በመከራቸው ነው። በእግዚአብሔር አይታመኑም ነበር። የግብፃውያንን ድጋፍ ለማግኘት ብዙ ጥረት አደረጉ። በዚህ መንገድ የወጣው ሃብት ኪሳራ ሆነ። እግዚአብሔርን ትተው ሥጋዊ መታመኛዎቻቸውን የሚከተሉ ሰዎች ምን ዓይነት አደጋ ውስጥ እንደሚገቡ ተመልከቱ። ፈጣሪ ዘላለማዊ ዐለት ነው፤ ፍጥረት ግን የተሰበረ የሸንበቆ ዘንግ ነው። ከሰው ብዙ መጠበቅ የለብንም፤ ከእግዚአብሔር ደግሞ ብዙ መጠበቅ ይገባናል። ኃይላችን ተረጋግቶ መቀመጥ፣ በእግዚአብሔርና በቸርነቱ በትሕትና መታመን፣ እንዲሁም ፈቃዱን በጸጥታ መቀበል ነው።

30:8-18 አይሁድ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር በዓለም ላይ የነበሩት ብቸኛ የእርሱን ስም የሚጠራ ሕዝብ ነበሩ፤ ሆኖም ከእነርሱ መካከል ብዙዎቹ ዓመፀኞች ነበሩ። ብርሃን ነበራቸው፤ ነገር ግን ጨለማን ይበልጥ ወደዱ። ነቢያት በኃጢአት ፍላጎቶቻቸው ውስጥ ይገሥጿቸው ነበርና ፍርሃት ሳይሰማቸው እንዳይዘልቁ ያደርጓቸው ነበር፤ ይህንንም ተቃውመው ተቀበሉት። ነገር ግን ታማኝ አገልጋዮች ኃጢአተኞችን ከማንቃት ጽኑ ዓላማቸው አይገፉም። እግዚአብሔር የእስራኤል ቅዱስ ነው፤ ስለዚህ እርሱን እንዲህ አድርገው ያገኙታል። ቅዱስ ትእዛዛቱንና ኃጢአትን መጥላቱን መስማት አልፈለጉም ነበር፤ ከእንግዲህ ወዲህ በእነዚህ ነገሮች እንዳይገሰጹ ፈለጉ። ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል እንደናቁ ሁሉ፣ ኃጢአቶቻቸው ደኅንነታቸውን መሰረቱን ነቀሉት። ሁኔታቸው እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃ ይሰባበር ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV “Woe to the obstinate children,” declares the Lord, “to those who carry out plans that are not mine, forming an allianc… English BCV ንዓመፀኛታት ደቂ ወይለኦም! ይብል እግዚኣብሄር፤ “ካባይ ዘይኮነ ምኽሪ መኸሩ፤ ሓጢኣትውን ኣብ ልዕሊ ሓጢኣት ምእንቲ ኽውስኹ፥ ካብ መንፈሰይ ዘይኮነ ቓል ኪዳን ይተኣታተዉ። ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo, “Ijoollee ana didanii ka'aniif, warra akeeka isa akeeka koo hin ta'in qopheeffataniif, warra fedha koo duuba … Afaan Oromoo BCV GIZ አሌ ሎሙ ለውሉደ ዐላዋያን ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር ገበርክሙአ ምክረ ወአኮ በእንቲአየ ወተሠራዕክሙ ወአኮ በእንተ መንፈስየ፤ ከመ ትወስኩ ኀጢአተ በዲበ ኀጢአት። giz GAZGAZ Waaqayyo, “Ijoollee ana didanii ka'aniif, warra akeeka isa akeeka koo hin ta'in qopheeffataniif, warra fedha koo duuba … Afaan Oromoo BCV aksum ንዓመፀኛታት ደቂ ወይለኦም! ይብል እግዚኣብሄር፤ “ካባይ ዘይኮነ ምኽሪ መኸሩ፤ ሓጢኣትውን ኣብ ልዕሊ ሓጢኣት ምእንቲ ኽውስኹ፥ ካብ መንፈሰይ ዘይኮነ ቓል ኪዳን ይተኣታተዉ። ትግርኛ AMHNIV “ለዐመፀኞች ልጆች ወዮላቸው” ይላል እግዚአብሔር፤ “የእኔ ያልሆነውን ሐሳብ ይከተላሉ፤ ከመንፈሴ ያልሆነውን ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፤ በኀጢአት ላይ ኀጢአት ይጨምራሉ። አማርኛ SWAHSUV Ole wa watoto waasi; asema Bwana; watakao mashauri lakini hawayataki kwangu mimi; wajifunikao kifuniko lakini si cha ro… Kiswahili