ትንቢተ ኢሳይያስ 2

AMHNIVአማርኛ22 ጥቅሶች3:40 አዳምጥ
አዳምጥ 3:40 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ይህ ነው፤

2በዘመኑም ፍጻሜ፣ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተራራ ከተራሮች ከፍ ብሎ ይመሠረታል፤ ከኰረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ወደዚያ ይጐርፋሉ።

3ብዙ ሕዝቦችም መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤ በጐዳናውም እንሄዳለን።” ሕግ ከጽዮን፣ የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።

4እርሱ በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤ የብዙ ሰዎችን አለመግባባት ያስወግዳል። እነርሱም ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጋሉ። ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ ጦርነትንም ከእንግዲህ አይማሩም።

5እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ ኑ፤ በእግዚአብሔር ብርሃን እንመላለስ።

6የያዕቆብ ቤት የሆነውን፣ ሕዝብህን ትተሃል፤ እነርሱ በምሥራቅ ሰዎች ከንቱ አምልኮ ተሞልተዋልና፤ እንደ ፍልስጥኤማውያን ያሟርታሉ፤ ከባዕዳን ጋር አገና ይማታሉ።

7ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፤ ሀብታቸውም ልክ የለውም። ምድራቸው በፈረሶች ተሞልታለች፤ የሠረገሎቻቸውም ብዛት ልክ የለውም።

8ምድራቸው በጣዖታት ተሞልታለች፤ ጣቶቻቸው ላበጇቸው፣ ለእጆቻቸው ሥራ ይሰግዳሉ።

9ሰው ዝቅ ብሎአል፤ የሰው ልጅም ተዋርዶአል፤ ስለዚህ በደላቸውን ይቅር አትበል።

10ከእግዚአብሔር አስፈሪነት ከግርማው ሽሽ፤ ወደ ዐለቶች ሂድ፤ በመሬትም ውስጥ ተሸሸግ።

11የእብሪተኛ ሰው ዐይን ይሰበራል፤ የሰዎችም ትዕቢት ይዋረዳል፤ በዚያን ቀን እግዚአብሔር ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል።

12የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እብሪተኛውንና ትዕቢተኛውን ሁሉ፣ የተኵራራውን በሙሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው።

13ረዥምና ከፍ ከፍ ያሉትን የሊባኖስ ዝግባዎች ሁሉ፣ የባሳንን የወርካ ዛፎች ሁሉ፣

14ታላላቁን ተራራ ሁሉ፣ ከፍ ያለው ኰረብታ ሁሉ፣

15ረጃጅሙን ግንብ ሁሉ፣ የተመሸገውን ቅጥር ሁሉ፣

16የተርሴስን መርከቦች ሁሉ፣ የክብር ጀልባዎችን ሁሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው።

17የሰው እብሪት ይዋረዳል፤ የሰውም ኵራት ይወድቃል፤ በዚያን ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል፤

18ጣዖቶች ሁሉ ፈጽሞ ይወድማሉ።

19እግዚአብሔር ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፣ ሰዎች ከአስፈሪነቱ ከግርማውም የተነሣ፣ ወደ ዐለት ዋሻ ወደ መሬትም ጒድጓድ ለመሸሸግ ይሮጣሉ።

20በዚያን ቀን ሰዎች ሊያመልኳቸው ያበጇቸውን፣ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይወረውራሉ።

21እግዚአብሔር ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፣ ሰዎች ከአስፈሪነቱ እንዲሁም ከግርማው የተነሣ፣ ወደ ድንጋይ ዋሻ፣ ወደ ዐለት ስንጣቂ ሮጠው ይገባሉ።

22እስትንፋስ አፍንጫው ላይ ባለች በሰው አትታመኑ፤ ከቶ ምን የሚበጅ ነገር አለው!

ማብራሪያ

2:1-9

የአሕዛብ መጠራት፣ የወንጌል መስፋፋት፣ እና ገና ሊመጣ ያለው ከዚያም የበለጠ ሰፊ ስብከት ተተንብየዋል። ክርስቲያኖች እርስ በርሳቸው ይጠናከሩ፣ እና እርስ በርሳቸው ይደጋገፉ። ሕዝቡን በመንፈሱና በቃሉ የሚያስተምረው እግዚአብሔር ነው። ክርስቶስ ሰላምን እንደሚያሰፍን ሁሉ ቅድስናንም ያስገኛል። ሰዎች ሁሉ እውነተኛ ክርስቲያኖች ቢሆኑ ኖሮ ጦርነት አይኖርም ነበር፤ ነገር ግን እነዚህ አባባሎች የሚያመለክቱት ነገር ገና በምድር ላይ አልተፈጸመም። ሌሎች ምንም ቢያደርጉ፣ እኛ ግን በዚህ ሰላም ብርሃን እንመላለስ። እውነተኛ ሃይማኖት ሲያድግ፣ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር ቤት በመውጣት እና ሌሎችንም አብረው እንዲሄዱ በማበረታታት ደስ እንደሚላቸው እናስታውስ። እግዚአብሔርን ከማያውቁት ጋር ራሳቸውን ደስ የሚያሰኙ ሰዎች አደጋ ላይ ናቸው፤ ምክንያቱም አብረናቸው የምንሆን የሰዎችን መንገድ በፍጥነት ለመከተል ስለምንማር ነው። እግዚአብሔርን የሚያስከፋው ብርና ወርቅ፣ ፈረሶችና ሠረገሎች መኖር አይደለም፤ ነገር ግን ያለ እነርሱ ደህና፣ ምቾት ያለው፣ እና ደስተኛ መሆን የማንችል ይመስል፣ በእነርሱም ሲሆን ደግሞ የግድ እንዲሁ መሆን ያለብን ይመ…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6