ትንቢተ ኢሳይያስ 2

AMHEVGአማርኛ22 ጥቅሶች3:22 አዳምጥ
አዳምጥ 3:22 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ቃል።

2በዘመኑም ፍጻሜ የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፥ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበሰባሉ።

3ሕግ ከጽዮን የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው፦ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በጎዳናውም እንሄዳለን፡ ይላሉ።

4በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፥ በብዙ አሕዛብም ላይ ይበይናል፤ ሰይፋቸውንም ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፤ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፥ ሰልፍም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም።

5እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ ኑ፥ በእግዚአብሔር ብርሃን እንሂድ።

6ሕዝብህን የያዕቆብን ቤት ትተሃልና፤ ይኸውም የምሥራቅን ሰዎች አመል ስለ ተሞሉ፥ እንደ ፍልስጥኤማውያንም ምዋርተኞች ስለ ሆኑ፥ ከባዕድ ልጆችም ጋር ስለ ተባበሩ ነው።

7ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፥ ለመዛግብቶቻቸውም ፍጻሜ የለውም፤ ምድራቸውም ደግሞ በፈረሶች ተሞልታለች፥ ለሠረገሎቻቸውም ፍጻሜ የለውም።

8ምድራቸው ደግሞ በጣዖታት ተሞልታለች፤ ጣቶቻቸውም ላደረጉት ለእጃቸው ሥራ ይሰግዳሉ።

9ታናሹም ሰው ዝቅ ብሎአል፥ ጨዋውም ተዋርዶአል፤ ኃጢአታቸውንም ይቅር አትበላቸው።

10ከእግዚአብሔር ማስደንገጥና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻ ግባ፥ በመሬትም ውስጥ ተሸሸግ።

11ከፍ ያለችውም የሰው ዓይን ትዋረዳለች፥ የሰዎችም ኵራት ትወድቃለች፥ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል።

12የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፥ እርሱም ይዋረዳል፤

13ደግሞም በረጅሙ ከፍ ባለው በሊባኖስ ዝግባ ሁሉ ላይ፥ በባሳንም ዛፍ ሁሉ ላይ፥

14በረጅሙም ተራራ ሁሉ ላይ፥ ከፍ ባለውም ኮረብታ ሁሉ ላይ፥

15በረጅሙም ግንብ ሁሉ ላይ፥ በተመሸገውም ቅጥር ሁሉ ላይ፥

16በተርሴስም መርከብ ሁሉ ላይ፥ በሚያማምሩ ጣዖታትም ሁሉ ላይ ይሆናል።

17ሰውም ሁሉ ይዋረዳል፥ የሰውም ኵራት ይወድቃል፥ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።

18ጣዖቶቻቸውም ሁሉ ፈጽመው ይጠፋሉ።

19እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ ሰዎች ከማስደንገጡና ከግርማው ክብሩ የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ምድር ንቃቃት ውስጥ ይገባሉ።

20በዚያን ቀን ሰው ይሰግድላቸው ዘንድ ያበጁአቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቹን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይጥላል።

21እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ ከማስደንገጡና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ተሰነጠቁ ዓለቶች ውስጥ ይገባሉ።

22እስትንፋሱ በአፍንጫው ውስጥ ያለበትን ሰው ተዉት፤ እርሱ ስለ ምን ይቈጠራል?

ማብራሪያ

2:1-9

የአሕዛብ መጠራት፣ የወንጌል መስፋፋት፣ እና ገና ሊመጣ ያለው ከዚያም የበለጠ ሰፊ ስብከት ተተንብየዋል። ክርስቲያኖች እርስ በርሳቸው ይጠናከሩ፣ እና እርስ በርሳቸው ይደጋገፉ። ሕዝቡን በመንፈሱና በቃሉ የሚያስተምረው እግዚአብሔር ነው። ክርስቶስ ሰላምን እንደሚያሰፍን ሁሉ ቅድስናንም ያስገኛል። ሰዎች ሁሉ እውነተኛ ክርስቲያኖች ቢሆኑ ኖሮ ጦርነት አይኖርም ነበር፤ ነገር ግን እነዚህ አባባሎች የሚያመለክቱት ነገር ገና በምድር ላይ አልተፈጸመም። ሌሎች ምንም ቢያደርጉ፣ እኛ ግን በዚህ ሰላም ብርሃን እንመላለስ። እውነተኛ ሃይማኖት ሲያድግ፣ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር ቤት በመውጣት እና ሌሎችንም አብረው እንዲሄዱ በማበረታታት ደስ እንደሚላቸው እናስታውስ። እግዚአብሔርን ከማያውቁት ጋር ራሳቸውን ደስ የሚያሰኙ ሰዎች አደጋ ላይ ናቸው፤ ምክንያቱም አብረናቸው የምንሆን የሰዎችን መንገድ በፍጥነት ለመከተል ስለምንማር ነው። እግዚአብሔርን የሚያስከፋው ብርና ወርቅ፣ ፈረሶችና ሠረገሎች መኖር አይደለም፤ ነገር ግን ያለ እነርሱ ደህና፣ ምቾት ያለው፣ እና ደስተኛ መሆን የማንችል ይመስል፣ በእነርሱም ሲሆን ደግሞ የግድ እንዲሁ መሆን ያለብን ይመ…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6