ትንቢተ ኢሳይያስ 27

AMHNIVአማርኛ13 ጥቅሶች2:46 አዳምጥ
አዳምጥ 2:46 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በዚያ ቀን እግዚአብሔር፣ ተወርዋሪውን እባብ ሌዋታንን፣ የሚጠቀለለውን ዘንዶ ሌዋታንን በብርቱ፣ በታላቁና በኀይለኛ ሰይፍ ይቀጣዋል፤ የባሕሩንም ግዙፍ አውሬ ይቈራርጠዋል።

2በዚያን ቀን እንዲህ ይባላል፤ “ለመልካሙ የወይን ቦታ ዘምሩለት፤

3እኔ እግዚአብሔር ጠባቂው ነኝ፤ ዘወትር ውሃ አጠጣዋለሁ፤ ስለዚህ ማንም አይጐዳውም፣ ቀንና ሌሊት እጠብቀዋለሁ፤

4እኔ አልቈጣም። እሾኽና ኵርንችት ምነው በተነሡብኝ! ለውጊያ በወጣሁባቸው፣ አንድ ላይ ባቃጠልኋቸው!

5አለዚያ ይምጡና መሸሸጊያቸው ያድርጉኝ፤ ከእኔ ጋር ሰላም ይፍጠሩ፤ አዎን፤ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርጉ።”

6በሚመጡት ቀናት ያዕቆብ ሥር ይሰዳል፤ እስራኤልም ያቈጠቍጣል፤ ያብባልም፤ በፍሬያቸውም ምድርን ሁሉ ይሞላሉ።

7የመቷትን እንደ መታቸው፣ እግዚአብሔር እርሷንስ መታትን? የገደሏትን እንደ ገደላቸው፣ እርሷስ ተገደለችን?

8በጦርነትና በስደት ተፋለምሃት፤ የምሥራቅ ነፋስ እንደሚነፍስበት ቀን፣ በብርቱ ዐውሎ ነፋስ አሳደድሃት።

9ያዕቆብ የመሠዊያ ድንጋዮችን፣ እንደ ኖራ ድንጋይ ፈጭቶ ሲያደቃቸው፣ የአሼራን ዐምድና የዕጣን መሠዊያዎችን፣ ከቦታቸው ነቅሎ ሲጥል፣ በዚያን ጊዜ በደሉ ይሰረይለታል፤ ይህም ኀጢአቱን የማስወገዱ ሙሉ ፍሬ ይሆናል።

10የተመሸገባት ከተማ ባዶዋን ቀርታለች፤ እንደ ምድረ በዳም የተተወች ስፍራ ሆናለች፤ ጥጆች በዚያ ይሰማራሉ፤ እዚያም ይተኛሉ፤ ቅርንጫፎቿንም ልጠው ይበላሉ።

11ጫፎቿ ሲደርቁ ይሰበራሉ፤ ሴቶችም መጥተው ይማግዷቸዋል። ማስተዋል የሌለው ሕዝብ ስለ ሆነ፣ ፈጣሪው አይራራለትም፤ ያበጀውም አይምረውም።

12በዚያ ቀን ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝ፤ እግዚአብሔር እህሉን ይወቃል፤ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፤ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።

13በዚያ ቀን ታላቅ መለከት ይነፋል፤ በአሦር የጠፉትና በግብፅ የተሰደዱትም መጥተው፣ በተቀደሰው ተራራ በኢየሩሳሌም እግዚአብሔርን ያመልካሉ።

ማብራሪያ

27:1-5 ጌታ ኢየሱስ በብርቱ ሰይፉ፥ በሞቱ ኃይልና የወንጌሉ ስብከት የሞትን ስልጣን የነበረውን እርሱንም ዲያብሎስን፥ ያንን አሮጌውን እባብ ያጠፋልና፥ አሁንም እያጠፋው ነው። ዓለም ፍሬ የለሽ፥ የማይረባ ምድረ በዳ ነው። ቤተ ክርስቲያን ግን የወይን አትክልት ስፍራ ናት፤ ብዙ እንክብካቤ የሚደረግላት፥ ውድ ፍሬዎችም የሚሰበሰቡባት ስፍራ። እግዚአብሔር በመከራና በስደት ሌሊትም ሆነ፥ በሰላምና በብልጽግና ቀን ይጠብቃታል። የኋለኞቹ ፈተናዎች አደገኝነታቸው ከቀደሙት የማያንስ ነው። እግዚአብሔር ደግሞ የዚህን የወይን አትክልት ስፍራ ፍሬያማነት ይንከባከባል። የመለኮታዊ ጸጋ የማያቋርጥ ውኃ ማጠጣት ያስፈልገናል። እነዚህ በማንኛውም ጊዜ ከተወሰዱ፥ እንጠወልጋለን፥ ከንቱም እንሆናለን። እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ ከሕዝቡ ጋር ቢከራከርም፥ በጸጋ ግን ከእነርሱ ጋር ለመታረቅ ይጠብቃል። እውነት ነው፥ ከወይን ፋንታ እሾህና አሜከላ ሲያገኝ፥ እነርሱም እርሱን ሲቃወሙት፥ ይረግጣቸዋል፥ ያቃጥላቸዋል። የወንጌል ትምህርት ማጠቃለያ እነሆ፥ ቤተ ክርስቲያን ዘወትር ውኃ የምትጠጣበት። ኃጢአት ወደ ዓለም ከገባችበት ጊዜ አንስቶ፥ በእግዚአብሔር በኩል ጽድቅ የሆነ ክርክር ነበረ፤ በሰው በኩል ግን እጅግ ዓመፀኛ ነበር። በጸጋ የተሞላ ጥሪ እነሆ ቀርቧል። ይቅር ባይ ምሕረት የጌታችን ኃይል ይባላልና፤ ያንን እንጨብጥ። የተሰቀለው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ኃይል ነው። በሕያው እምነት የእርሱን ኃይል እንጨብጥ፤ እርሱም ለተቸገሩት ኃይል ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በዚያም ቀን እግዚአብሔር ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን ጠማማውንም እባብ ሌዋታንን በጠንካራ በታላቅም በብርቱም ሰይፍ ይቀጣል፥ በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድላል። አማርኛ ENGNIV In that day, the Lord will punish with his sword, his fierce, great and powerful sword, Leviathan the gliding serpent, … English BCV በታ መዓልቲ እቲኣ እግዚኣብሄር በቲ ዓቢይን ሓያልን ሰይፉ ገይሩ፥ ነቲ ቕልጡፍ ተመን ንሌዋታን፥ ነቲ ዝጠዋወ ተመን ንሌዋታን ክቐፅዖ፥ ነቲ ኣብ ባሕሪ ዘሎ ገበል ከዓ ኽቐትሎ እዩ። ትግርኛ GAZBIB Yeroo sanatti Waaqayyo billaa isaa isa sodaachisaadhaan, isa qaramaadhaa fi jabaadhaan lewaataan bofa isa murxuxxifamu,… Afaan Oromoo BCV GIZ ውእተ አሚረ ያመጽእ እግዚአብሔር መጥባሕተ ቅዱሰ ወዐቢየ ወጽኑዐ ላዕለ ከይሲ ወላዕለ አርዌ ምድር ዘይጐይይ ኀበ ከይሲ ወአርዌ ምድር የአኪ ወይቀትሎ ለከይሲ ዘውስተ ባሕር። giz GAZGAZ Yeroo sanatti Waaqayyo billaa isaa isa sodaachisaadhaan, isa qaramaadhaa fi jabaadhaan lewaataan bofa isa murxuxxifamu,… Afaan Oromoo BCV aksum በታ መዓልቲ እቲኣ እግዚኣብሄር በቲ ዓቢይን ሓያልን ሰይፉ ገይሩ፥ ነቲ ቕልጡፍ ተመን ንሌዋታን፥ ነቲ ዝጠዋወ ተመን ንሌዋታን ክቐፅዖ፥ ነቲ ኣብ ባሕሪ ዘሎ ገበል ከዓ ኽቐትሎ እዩ። ትግርኛ SWAHSUV Katika siku hiyo Bwana, kwa upanga wake ulio mkali, ulio mkubwa, ulio na nguvu, atamwadhibu lewiathani, nyoka yule mwep… Kiswahili